TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው " ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል። የተባበሩት…
የዘር ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፈው የፖሊስ መኮንን ከዓመታት በኃላ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል በተከሰሰ አንድ የቀድሞ የሩዋንዳ ፖሊስ መኮንን ላይ የዕድሜ ልክ እሥራት መፍረዱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ)ን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

ስሙ ፊሊፔ ሄትጌኪማና የተባለው ሩዋንዳዊው የፖሊስ መኮንን ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት በተፈጸመው የጅምላ ፍጅት ወቅት የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋግጧል።

የፖሊስ መኮንኑ ወንጀሉን የፈፀመው በፈረንጆቹ 1994 በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ወቅት ነው።

በወቅቱ የሁቱ ታጣቂዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎችን መግደላቸው ይታወሳል።

የፈረንሳይ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ግለሰቡ እሱ ራሱ የሰዎችን ነብስ ከማጥፋቱም በላይ #ሌሎች ግድያ እንዲፈፅሙ #ያነሳሳ ነበር።

ፊሊፔ በጅምላ ግድያው ወቅት ኒያንዛ በተሰኘችው የደቡብ ሩዋንዳ አካባቢ የፖሊስ መኮንን ሆኖ ያገለግል ነበር።

ነገር ግን የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ካቆመ በኋላ ወደ #ፈረንሳይ አቅንቶ ለአስርታት ማንነቱ ደብቆ ሲኖር ቆይቷል።

ግለሰቡ ፈረንሳይ ከገባ በኋላ መጀመሪያ የስደተኛ ወረቀት አግኝቶ፤ ቀጥሎ ደግሞ ፊሊፔ ማኒዬ በተሰኘ ስም ዜግነት ተሰጥቶት ኖሯል።

ፈረንሳይ ውስጥ ሳለ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥበቃ ሆኖ ሲያገልግል ከቆየ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2017 ወደ #ካሜሩን ያቀናል።

ሰውዬው ይህን ያደረገው አንድ ሰው እሱ ላይ ቅሬታ እንዳለው ድምፁን ካሰማ በኋላ ነው።

ፊሊፔ በቁጥጥር ሥር የዋለው በካሜሩኗ ዋና ከተማ ያውንዴ ውስጥ ሲሆን ከዚያም ወደ ፈረንሳይ እንዲሄድ ተደርግ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል ቆይቷል።

በመጨረሻም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

በሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ሆነው የተገኙ ግለቦች ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ሲሰጣቸው ፊሊፔ አምስተኛው ነው።

በሚቀጥለው ዓመት 30ኛ ዓመቱን የሚይዘው እና በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሺህ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎች አሁን ድረስ ጉዳያቸው አልተዘጋም።

ከወር በፊት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረ የቀድሞ የፖሊስ አባል (ፉልጌንሴ ካይሼማ) ከ22 ዓመታት ሽሽት በኃላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙ ይታወሳል።

ግለሰቡ በተያዘበት ወቅት የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፤ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ ፤ ከሩብ ምዕተ አመታት በኃላም ቢሆን እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች ከፍትህና ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

@tikvahethiopia