#TikvahFamily
የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በ https://t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x (ቲክቫህ ስፖርት) መከታተል ትችላላችሁ።
@tikvahethsport

#ውድ_ቤተሰቦቻችን_ጥንቃቄያችሁን_አጠናክሩ😷
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,458 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 9,292 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,458 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 12 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
ወደፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን በአሁን ሰዓት 580 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ላይ ናቸው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
"...ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" - ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ትላንት በካቡል ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ንግግር አድርገዋል። የሽብር ጥቃቱን ለፈጸሙትም ሆነ አሜሪካን ለመጉዳት የሚመኙ አካላትን ጠንከር ባለ ንግግራቸው አስጠንቅቀዋል። ባይደን ፥ "ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን…
#Update
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሰውን ፍንዳታ ጀርባ ባለው ቡድን ውስጥ ዕቅድ የሚያወጣ ነው የተባለ ግለሰብ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) አማካይነት እንደገደለ አስታወቀ።
ISIS-K የተባለው ቡድን የISIS ክንፍ ሲሆን በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ባደሰው ጥቃት ወደ 170 የሚጠጉ ሰዎች ሞተዋል።
ከተገደሉት ሰዎች መካከል 13ቱ አሜሪካውያን ወታደሮች ናቸው።
የማዕከላዊ ዕዝ አባል ካፒቴን ቢል ኧርባን እንዳሉት፤ ፍንዳታ ላደረሰው ቡድን እቅድ የሚነድፈውን ሰው ለመግደል የድሮን ጥቃት የተሰነዘረው #ናንጋሀር በተባለ የአፍጋኒስታን ግዛት ውስጥ ነው።
ኢላማው የISIS አባላት እንደነበሩና ንጹሀን ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ተገልጿል።
ሪፐር የተባለው ድሮን ከመካከለኛው ምሥራቅ ተወንጭፎ የISIS አባሉ መኪና ውስጥ ከሌላ የISIS አባል ጋር ሳለ መትቶታል።
በናንጋሀር ግዛት በርካታ የISIS-K አባላይ እንደመሸጉ ይነገራል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲው ልዑል ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።
የሳዑዲው ልዑል በውይይቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ እድገትና ብልጽግና ለጠ/ሚ ዐቢይ ደግሞ ስኬትን ተመኝተዋል።
በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ምንጭ፡ Saudi Gazette

#SaudiArabia
በጄዳ የሹሜሲ ዲፖርቴሽን ማዕከል ከገቡ በኃላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያውቃቸው ቤተሰብ ፣ ዘመድ እና ጎደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።
ከዚህ በታች የሟቾች ስም አስክሬናቸው የሚገኝበት ሆስፒታል የተገለፀ ሲሆን የምታውቋቸው ሰዎች በቢሮ ቁጥር 13 ቀርባችሁ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጄዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አሳውቋል።
- ሂክመት መሀመድ (የአስክሬን መገኛ👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ከዲጃ ማህመድ (የአስክሬን መገኛ👉ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ሮዳስ ሙሉ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ጀማል ከማል (የአስክሬን መገኛ 👉 ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል)
- ቢንያም ምሩፅ ሃጎስ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- የኢንዲያ ተማም /ህፃን ልጅ/ (የአስክሬን መገኛ 👉 ሰግር ሆስፒታል)
- መሃሪ ኃይሌ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሱልጣን ሙሀመድ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- በህታ ነጋሲ አፈወርቂ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
- ሰለሞን ሀዱሽ ተካ (የአስክሬን መገኛ 👉 ንጉስ አብዱላአዚዝ ሆስፒታል)
በዚሁ አጋጣሚ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዳግም የተጀመረ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያሉ ዜጎች በርካታ በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

ብሊንከን እንዲከሰሱ ተጠየቀ።
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን የገቡትን የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስበር ባለመቻላቸው እንዲከሰሱ ተጠይቋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዲከሰሱ የጠየቁት የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ምክር ቤት የገቡ አባላት መሆናቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
አንቶኒ ብሊንከን ወደ ኃላፊነት ሲመጡ የገቡትን ቃል ማሳካት እንዳልቻሉ የገለጹት አባላቱ በዚህም ምክንያት መከሰስ አለባቸው በሚል የሀገሪቱን ሕጎች እየጠቀሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ብዙ ሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በብሊንከን ላይ ጥያቄ ቢኖራቸውም የሚሪላንድ ተወካዩ አንዲ ሃሪስ እና የደቡብ ካሮላይና ተወካዩ ራልፍ ኖርማን ግን የሕግ አንቀጾችን ሳይቀር እያጣቀሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒትሩ መከሰስ እንዳለባቸው መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
የአፍጋኒስታን ጉዳይ እንዲሻሻል መሰራት ቢገባውም ይህንን ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ መቅሰፍት መድረሱን የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡
የአፍጋኒስታንን ጉዳይ ማስተካከል በፕሬዝዳንት ባይደን ትከሻ ላይ የወደቀ ቢሆንም በዋናነት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የማማከር ኃላፊነት ነበረባቸው ተብሏል፡፡
ከትናንት በስቲያ በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ሃሚድ ካርዛይ ዓለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ውጭ ላይ በተከሰተው ፍንዳታ 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው እና ምስቅልቅል የበዛበት ወታደሮችን የማስወጣት ተግባርም አንቶኒ ብሊንከንን ሊያስጠይቅ እንደሚችል የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በሚጠበቅባቸው ልክ አለማማከራቸው እና አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያላትን ብሐየራዊ ጥቅም በተገቢ ሁኔታ ማሳወቅ አለመቻላቸው ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-08-28
(አል ዓይን ኒውስ)

#CIA #USA #CHINA
የኮሮና ቫይረስ መነሻው ምንድነው ? መደምደሚያ ያላገኘው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ እንደቀጠለ ነው።
የአሜሪካ ብሔራዊ የስለላ ቢሮ ዳይሬክተር ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስ "ከቻይና ቤተ ሙከራ ያፈተለከ ነው ወይስ በተፈጥሮ የተከሰተ ነው" በሚለው ላይ ለ2 ተከፍሏል።
ነገር ግን ይህ የአገሪቱን 18 የስለላ ኤጀንሲዎች የሚቆጣጠረው ተቋም ኮሮናቫይረስ ባዮሎጂካል የጦር መሣሪያ እንዳልሆነ መደምደሚያ ላይ ደርሷል ሲል ቢቢሲ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የCIA ሪፖርት ከመውጣቱ ቀደም ብሎ ሪፖርቱን "ፀረ ሳይንስ" በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ይህ ከዳይሬክተሩ ጽሕፈት ቤት የወጣው ሪፖርት የደኅንነቱ ማኅበረሰብ በኮሮናቫይረስ መነሻ ላይ አሁንም የተከፋፈለ አቋም መያዙን ገልጿል።
"ሁሉም ኤጀንሲዎች በቫይረሱ ከተበከለ እንስሳ ጋር በተፈጠረ ተፈጥሯዊ ንክኪ ወይም ከቤተ ሙከራ ጋር በተያያዘ ክስተት አምልጦ ይሆናል በሚሉት በሁለቱም ግምቶች ይስማማሉ" ሲል ሪፖርቱ አስነብቧል።
በሪፖርቱ ላይ ስማቸው ያልተጠቀሰ የስለላ ተቋማት፤ ኮሮና ቫይረስን ከሚሸከም እንስሳ ወይም ከቫይረሱ ጋር ቅርበት ካለው ሌላ ቫይረስ ካለበት እንስሳ ጋር በተፈጠረ ንክኪ ቫይረሱ ወደ ሰዎች ተላልፎ ይሆናል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን በዚህ መደምደሚያ ላይ ዝቅተኛ እምነት እንዳለቸው ተጠቅሷል።
አንድ የስለላ ድርጅት ከ10 ዓመታት በላይ የኮሮና ቫይረስን በተለይም በለሊት ወፎች ላይ ሲያጠና በቆየው የዉሃን የቫይረሶች የምርምር ተቋም ውስጥ የመጀመሪያው የሰዎች ንክኪ ተፈጥሯል የሚል የተሻለ እምነት ማሳደሩ ተጠቅሷል።
የቢቢሲን ዘገባ ያንብቡ : telegra.ph/BBC-08-28

የቤት ኪራይ ጭማሪ ለ90 ቀናት ታገደ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ ቀናት ክልከላው ሊራዘም ይችላል::
ደንቡን በመተላለፍ ጭማሪ የተደረገበት ተከራይ አቤቱታውን በፅሑፍ ለወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በማቅረብ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚቻልበት ሥርዓት በደንቡ ተደንግጓል፡፡
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል::

'የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ'
በደብረ ማርቆስ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ከዛሬ ጀምሮ ማሻሻያ ተድረጎበታል።
ነሐሴ 22/2013ዓም በአገራዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሰዓት ዕላፊ ገደብን ጨምሮ በከተማዋ በተቋቋመው የፀጥታ ግብረ ሃይል የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸው ይታወቃል።
ከተላለፋት ውሳኔዎች መካከልም የሰዓት ዕላፊ ገደብ አንዱ ነው።
ሌሎች ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው #የሰዓት_ዕላፊ_ገደቡ ማሻሻያ ተደርጎበታል።
በዚህ መሰረት ጠዋት ከ12ሰዓት በፊት መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ምሽት 2ሰዓት የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ግን ወደ ምሽት 3 ሰዓት የተሻሻለ መሆኑን የፀጥታ ግብረ ሃይል ኮሚቴው አስታውቋል።

#AddisAbaba
• 1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ።
• 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸውን ተሰርዟል።
• ከ64 በላይ በወንጀል ተከሰዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ በነበሩ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ በወንጀል እንዲጠየቁ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
በዚሁ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ መግለጫ ሰጥተዋል።
በከተማዋ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲሠሩ የነበሩ ፦
- 1 ሺህ 886 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስድቦባቸዋል።
- ከንግድ ህግ ውጪ ሲሰሩ በተገኙ 657 ድርጅቶች የንግድ ፈቃዳቸው የመሠረዝ እርምጃ ተወስዷል።
- ከ64 ላይ የሚሆኑ በወንጀል እንዲከሠሡ መደረጉን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ 369 መጋዘኖችን የመፈተሽ ስራ መሰራቱን እና በ20 መጋዘኖች ከፍተኛ የምርት ክምችት በመገኘቱ ታሽገዋል፤ የተከማቹት ምርቶችም ለተጠቃሚ እንዲደርስ ተደርጓል።
በነዚህ መጋዝኖችም ከፍተኛ መጠን ያለው የግንባታ ዕቃዎች በተለይም፦
- ፌሮ ብረት፣
- የምግብ ሸቀጦች፣
- ጨው፣
- በርበሬ፣
- ዘይት፣
- ጥራጥሬ የመሣሠሉት ክምችት የተገኘ ከመሆኑም ባሻገር ለጤና ደህንነት ጠንቅ የሆኑ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የጁስ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
አቶ አብዱልፈታ በመግለጫቸው ፥ አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው ስግብግብ ነጋዴዎች ትክክለኛ ባልሆነ የመስፈሪያ መሣሪያዎች ምርቶችን እየሸጡ መሆኑ ተደርሶበት ሲሠሩበት የነበሩ 19 የመስፈሪያ መሣሪያዎች ተሠብስበው እንዲወገዱ መደረጉን አሳውቀዋል። #AAPS

#Tokyo2020
የሀገሯን ስም ከፍ ያደረገችው አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ...
ሀገራችን ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ በኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በአትሌት ትዕግስት ገዛሃኝ በ T13 1,500 ሜትር ውድድር በ 4:23:24 በሆነ ሰአት (የግሏን ምርጥ ሰአት) በመግባት አግኝታለች ።
አትሌት ትዕግስት ለራሷና ለሀገሯ በሴቶች ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ታላቅ ገድል ፈፅማለች ።
የመረጃ ባለቤት ፦ ዮናስ ገብረማርያም

Congratulations !
የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዛሬ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ ባካሄደው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ስርዐት 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ 448ቱ በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም ሰባቱ በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆኑ ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 31ዱ ሴቶች ናቸው።
#ወራቤ_ዩኒቨርሲቲ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡
#ኦዳቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 354 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው 3ኛ ዙር የምረቃ ስነስርዐት የተመረቁ ተማሪዎች፤ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን የተከታተሉ ናቸው።
#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመርቋል።
3ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆች በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብሮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች 428ቱ ሴቶች ናቸው።
በሌላ በኩል ፦
የተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።
ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ግሬት ኮሌጅና ኤልኤም ኢንተርናሽናል የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።
Source : @tikvahuniversity

#ALERT🚨
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,906 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 9,112 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,906 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 13 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ከትላትናው በ7 ጨምሮ ዛሬ 587 ደርሷል።