TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar ከያሎ እና ጎሊና ወረዳዎች ተፈናቅለው " ጋሊኮማ ጤና ጣቢያ እና ትምህርት ቤት " ተጠልለው በነበሩ ዜጎች ላይ ህወሓት ጥቃት መፈፀሙን የአፋር ክልል መግለፁ ይታወቃል። ክልሉ ህወሓት በፈፀመው ጥቃት 107 ህጻናት፣ 89 ሴቶች እና 44 አዛውንቶች በአጠቃላይ የ240 ሰዎች መገደላቸውን የመጀመሪያ ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል። @tikvahethiopia
#Afar
ከቀናት በፊት የአፋር ክልላዊ መንግስት በክልሉ ውስጥ ባጋጠመው ጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ተጠልለውበት በነበረው ትምህርት ቤትና የጤና ተቋም ላይ ህወሓት በተፈጸመው ጥቃት ከ100 በላይ ህጻናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
በጥቃቱ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ እጥረት ባለበት አካባቢ ላይ የነበረ የምግብ እርዳታ አቅርቦት በህወሓት ኃይሎች መውደሙን የክልሉ መንግሥት ማሳወቁ ይታወሳል።
ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) በአፋር ክልል ውስጥ በተፈፀመው ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል መባሉ እጅጉን እንዳስደነገጠው ገልጿል።
ድርጅቱ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት ስለተደሉ ሰዎች የተሰማውን የገለጸው ዛሬ ከኒው ዮርክ በዋና ዳይሬክተሯ ሔኔሪታ ፎሬ በኩል ባወጣው መግለጫ ነው።
ድርጅቱ በአፋር ክልል በተፈፀመው ጥቃት እና ጉዳት በመግለጫው ላይ ቢያነሳም ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመው አልገለፀም።
UNICEF በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ እየተስፋፋ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። "ከምንም በላይ ደግሞ ሁሉም ወገኖች ህጻናትን ከጉዳት ለመጠበቅ የተቻለቻውን ሁሉ እንዲያደርጉ" ጠይቋል።
@tikvahethiopia

#Alert🚨
በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች እያሻቀበ ነው።
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,610 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 440 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አራት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 56 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ከሀሰተኛ መረጃ እራሳችሁን ጠብቁ !
ኢትዮጵያ በአሜሪካ ዋሽንግቶን ዲሲ የሚገኘውን የኤምባሲዋን ዘጋች በሚል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይህንን ያሳወቀው በቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኩል ነው።
ከሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ " ኢትዮጵያ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘዉ ኤምባሲዋን ዘጋች ፤ በኤምባሲዉ የሚሰሩ ዲፕሎማቶቿን ጠራች" የሚሉ የተለያዩ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።
በዚህ ጉዳይ ቃላቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ቃላቸው የሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ የኤምባሲውን መዘጋት በተመለከተ የተጋራው መረጃ "ዉሸት ነዉ" ብለዋል።
ዲፕሎማቶች ተጠርተዋል ለሚለዉም "ዲፕሎማት ለስራ ይጠራል፣ ይሄዳል። ይሄ ኖርማል ነው፣ ምንም አዲስ ነገር አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።

#EthiopianAirlinesCargo
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዕቃ ጭነት (cargo) አገልግሎት ዘርፍ የላቀ ውጤት ካስመዘገቡ 25 ምርጥ የአለማችን አየር መንገዶች ውስጥ ገባ።
ይህን መረጃ አየር መንገዱ የዓለም የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ያወጣው ስታትስቲካዊ መረጃ ዋቢ አድርጎ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በዓለም አቀፍ የካርጎ አገልግሎት የ21ኛ ደረጃን እንደያዘ የተገለፀ ሲሆን አየር መንገዱ በመደበኛ ካርጎ ቶን ኪሎ ሜትር (Cargo Tonne Kilometers) 3 ሚሊዮን 3 መቶ 93 ሺህ አስመዝግቧል፤ በመደበኛ የጭነት በረራዎች 623 ሺህ ቶን በማጓጓዝ 19ኛ ደረጃን ይዟል።
Via IATA World Transport Statistics / Ethiopian Airlines

Photo
ከታሰሩ 16 ጋዜጠኞች 10ሩ ተፈተዋል።
በአፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ ከታሰሩ 16 ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች መካከል 10ሩ ትላንት ረፋድ ላይ በዋስ መፈታታቸው ተሰምቷል።
ከእስረኞቹ መካከል የ14ቱ ጠበቃ የሆኑት አቶ ታደለ ገ/መድህን አስር ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች መፈታታቸውን አረጋግጠው፤ ሆኖም አሁንም ፦
- ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ፣
- ጋዜጠኛ አበባ ባዩ፣
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና ጋዜጠኛ ፋኑኤል ክንፉ የተባሉት የኢትዮ ፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞች በእስር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከእስር የተፈቱት 10ሩ እስረኞች ትላንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ገደማ አዲስ አበባ መግባታቸውን የታወቀ ሲሆን ከእስር ከተፈቱት ውስጥ በአውሎ ሚዲያ በጋዜጠኝነት፣ በግራፊክስ ኤዲቲንግ ባለሙያነት እና በሰው ሃይል አስተዳደር ክፍል የሚሰሩት ፋና ነጋሽ፣ ምህረት ገብረክርስቶስ፣ ፍቅርተ የኑስ እና ዊንታና በርሄ ይገኙበታብ።
ተጠርጣሪዎቹ ትላንት ሰኞ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው ቢሆንም፤ በችሎት ሳይቀርቡ ከምሳ ሰዓት በፊት ከእስር መለቀቃቸውን ተናግረዋል።
የመረጃ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ

"...የዓለም አቀፉ ማህበረሠብ መርጦ አልቃሽ ነው" - አቶ ገአስ አህመድ
የአፋር ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ከትግራይ ወደ አፋር የተስፋፋው ውጊያ የሚያደርሰው ሞት ጥፋትና የህዝቦች መፈናቀል ትኩረት አልተሰጠውም ብሏል።
የድርጅቱ ፕሬዝዳንት አቶ ገአስ አህመድ ለጀርመን ድምፅ በሰጡት ቃል ፥ በአፋር ስለሚፈጸመው ጥቃትና ስለሚደርሰው ጥፋት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታን መርጧል ሲሉ ኮንነዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
"ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፋር ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር አንድም ቀን ሲዘግቡ አልታየም" ያሉት አቶ ገአዝ "አሁንም የአፋር ህዝብ ሮሮ እያሰማ ነው በራሱ ሀገር ላይ በሰላም እንዳይኖር እየተደረገ ነው ያለው የፌዴራል መንግስትም ትኩረት መስጥት አለበት" ብለዋል።
ከቀናት በፊት በአብዛኛው ህጻናት ፣ ሴቶችና አቅደ ደካሞች በተጠሉለበት አፋር ክልል በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ላይ በደረሰ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ200 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸው ፥ ከዚህ በተጨማሪ 30 ሺ ኩንታል የሚገመት እህል መውደሙን ይህንን የፈፀመውም ህወሓት መሆኑን የአፋር ክልል መንግስት ማሳወቁ አይዘነጋም።

#BREAKING
በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው የህወሓት ቡድን ላይ “ብርቱና የማያዳግም” እርምጃ እንዲወሰድ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አቅጣጫ ሰጠ።
መንግስት “ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይል” ባለው አሸባሪው የሕወሐት ኃይል እና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ ብርቱና የማያዳግም እንዲወሰድ አቅጣጫ ሰጥቷል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ፣ የክልል ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች የማያዳግም ክንዳቸውን እንዲያሳርፉ አቅጣጫ ተቀምጧል። ከጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸው ኢትዮጵያውያን ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሓት እየከፈተ ያለው ጥቃት ሕዝባዊ መልክ እንዲይዝ በማድረጉ ያንኑ ለመመከት ሕዝባዊ ምላሽ እንደሚያሻው ገልጿል።
"ውጊያው የትግራይን ሕዝብ ምሽግ ካደረገው እኩይ ኃይል ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር አይደለም ፤ እናም ስንፋለም መጠቀሚያ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ብሎም መላዋ ኢትዮጵያን ከአሸባሪው ቡድን ነጻ ለማውጣትና የሀገራችንን ሰላምና አንድነት ለማስከበር ነው" ብሏል የፌዴራል መንግስት።
የፌዳራል መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር 2013 ዓ/ም የተናጠል የተኩስ አቁም አድርጌያለሁ ብሎ ፀጥታ ኃይሉን ከትግራይ ክልል እንዳስወጣ መግለፁ አይዘነጋም።
#PMOffice

#ATTENTION
የደሴ ከተማ አስተዳደር ለከተማው ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባል በሰዓት የተገደበ የተሽከርካሪና የሰው የእንቅስቃሴ ገደብ መቀመጡን አሳውቋል።
ገደቡ ከሰሜን ውሎ ተፈናቅለው ወደ ከተማይቱ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ነው ተብሏል።
በዚህም መሰረት ፦
1ኛ. መላው የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው።
2ኛ. ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗና።
3ኛ. የሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ተወስኗል።
ውሳኔው ከዛሬ ነሀሴ 04/2013 ጀምሮ በከተማው ተግባራዊ ይደረጋል።

#Bahirdar
በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል።
እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት ከከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ጽ/ቤት፣ ከፖሊስና መሰል የህግና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በሌሊት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ተጠያቂነት ባለው አሰራር ታቅፈውና ለቁጥጥር እንዲያመች በቁጥር ተወስነው እንዲሰሩ መደረጉን የየማህበራቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረት ከስምንት የባጃጃ ማህበራት ውስጥ በስነ-ምግባር እና ለማህበረሰቡ ቅንና ታማኝ አገልግሎት ከሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መካከል 120ዎችን በመመልመልና ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋት 11፡00 ድረስ በሁሉም ቀበሌዎች እየተንቀሳቀሱ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።
ይህ ለከተማው ሰላምና፣ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል የሚደረግ በመሆኑ የተመደቡ ባጃጆች ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የማህበራቸውን ስምና አንፀባራቂ የደንብ ልብስ እንዲጠቀሙ፣ በዚያው ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር በኩል ለሚደረገው ተግባር ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡
ለዚህ ከተመደቡ ውጭ ማነኛውም ባጃጅ ከ3 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደሌለበትና ይህን ውሳኔ ተላልፎ የተገኘ የባጃጅ አሽከርካሪ ካለ በህግ ይጠየቃል ተብሏል።
የተመደቡት 120 ባጃጆች ያለምንም ዋጋ ጭማሪና ያለ አድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲሰሩ በሚሰጡት አገልግሎትም እጥረት ካለ እየተገመገመ እንደሚስተካከል ከ #ባህርዳር_ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Bahirdar በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ። ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል። እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት…
ባህር ዳር ማሳሰቢያ ፡-
ማታ ማታ አገልግሎት የሚሰጡ የባጃጆች ቁጥር #ከዛሬ ጀምሮ እንዲወሰን ተደርጓል።
ይህ የሆነ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ነው ተብሏል።
ማንኛውም የከተማው ነዋሪም ሆነ ማንኛውም እንግዳ በሌሊት የመንቀሳቀስ ጉዳይ ከገጠመው እና ባጃጅ ከፈለገ ከሚፈልገው ቦታ እንዲላክለት ማድረግ ይችላል።
የባህር ዳር ነዋሪዎች ሆኑ እንግዶች ችግር የሚፈጥሩ ባጃጆች ካጋጠማቸው ወይም የባጃጅ አገልግሎት ከፈለጉ ፣ በዚህ ጉዳይ የሚያስተባብሩ አካላትን እገዛ ከፈለጉ በማንኛውም ሰዓት በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች 0583205744 ፣ 0582206396፣ 0918029715 እና 0918249974 መደወል ይችላሉ ተብሏል።
ፎቶ : ፋይል

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 882 ሰዎች የኮቪድ-19 ሲገኝባቸው የ10 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት ከዕለት ወደዕለት እያየለ መጥቷል።
ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 7518 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 882 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

#Afar #Amhara
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ/ም በአፋር ክልል ጉሊና ወረዳ ፣ ጋሊኮማ ቀበሌ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እማ ትምህርት ቤቶች ላይ በደረሰው ጥቃት በርካታ ቁጥር ያላቸው ህፃናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መገደላቸው ሪፖርት ከተደረገ በኃላ ፥ በአሁን ወቅት ለተጎጂዎች የህክምና እርዳታ በሚደረግባቸው አካባቢዎች የክትትል ቡድን ማሰማራቱን አሳውቋል።
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ግጭት ባገረሸባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ ክትትል እያደረገ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በግጭት ሳቢያ አደጋ ውስጥ የወደቁ የሲቪል ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ መባባሱ በእጅጉ እንደሚያሳስበው አሳውቋል።
በግጭቱ ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት እና የፀጥታ ኃይሎች በሀገራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎችና በጦርነት ህግና መርሆች የተጣለባቸውን ግዴታ እንዲያከብሩ በድጋሚ በጥብቅ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ ሲቪል ሰዎች እና ታሪካዊ ቅርሶችን ጨምሮ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ዒላማ መደረግ የለባቸውም ያለ ሲሆን ህፃናት እና ተጋላጭ ማህበረሰቦች በማንኛውም ጊዜ ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚግባ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው ሲል አስገንዝቧል።

#RayaUniversity
በራያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት እንደሚወጡ ይጠበቃል።
በዩኒቨርሲቲው ውስጥ 1 ሺህ የሚጠጉ የሌሎች ክልሎች ተወላጅ ተማሪዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
በትምህርት ላይ የቆዩት የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ ረቡዕ ነሐሴ 05/2013 ዓ.ም የሴሚስተር ፈተናቸውን በማጠናቀቅ እንደሚወጡ የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተናግረዋል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት በ2 ዙር ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ይታወቃል።
በተመሳሳይ በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የነበሩ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም እንደወጡ ይታወሳል።
በትግራይ ክልል የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት በትኩረት እየሠራ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል።
ከትግራይ ክልል የተመለሱ ተማሪዎች ቀጣይ እጣ ፈንታቸውን በተመለከተ ሚኒስቴሩ ከተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር እየሠራ መሆኑን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ መግለፁ አይዘነጋም።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በኩል መከታተል ትችላላችሁ : t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahuniversity

በደቡብ ወሎ ዞን አንዳንድ የምዕራብ ወረዳዎች እና በሌሎች የሰሜን ወሎ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የኔቶርክ አገልግሎት መስራት መጀመሩ ተገልጿል።
ከኔትወርክ መጥፋት ውጭ መቅደላ ተንታ ደላንታ እንዲሁም ሌሎችም የደቡብ ወሎ ወረዳዎች ፍፁም ሰላም መሆናቸውን ተገልጿል።
ነዋሪዎች ሽብረተኛ ተብሎ በተፈረጀው "ህወሓት" ፕሮፓጋንዳ ውዥንብር ውስጥ ሳይገቡ አካባቢያቸውን በንቃት ሊጠብቁ ይገባል ሲል የመቅደላ ወረዳ መልዕክት አስተላልፏል።

"... ከመርሳ፣ ከወልዲያ እና ከውርጌሳ አካባቢ በርካታ ሰው በስፋት እየመጣ ነው፤ እሱን እየለየን ወደ ማረፊያ ቦታ እየገቡ ነው" - አቶ አበበ ገ/መስቀል (የደሴ ከንቲባ)
እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰሜን ወሎ ወደ ደሴ ከተማ መግባታቸውን የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ተናገሩ።
አቶ አበበ ይህንን ያሳወቁት #ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።
ቀደም ብሎ ከ4 አስከ 5 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ደሴ ከተማ ገብተው ነበር ያሉት አቶ አበበ ከትናንት ጀምሮ ግን በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ከተማዋ እየገቡ መሆኑን አስረድተዋል።
አቶ አበበ ፥ "ከመርሳ፣ ከወልዲያ እና ከውርጌሳ አካባቢ በርካታ ሰው በስፋት እየመጣ ነው፤ እሱን እየለየን ወደ ማረፊያ ቦታ እየገቡ ነው። ትክክለኛውን ቁጥር ለጊዜ ባላውቀውም ከ10 አስከ 15ሺህ የሚገመት ሕዝብ እየገባ ነው ያለው" ሲሉ ለዜና ማሰራጫው ተናግረዋል።
በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ ደሴ እየገባ በመሆኑ በሕዝቡ ጥያቄ መሠረት የሰዓት እላፊ መታወጁን አሳውቀዋል።
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል በተለይ የሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ሳምንታት የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው በመስጋት ወደ ደሴ ከተማ እየገቡ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

#Dessise
የደሴ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ ዜጎች ጊዜያዊ ማረፊያ አዘጋጅቷል።
1ኛ. ቅዳሜ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ አንድ ":- ከወልድያ እና ከጉባላፍቶ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።
2ኛ.ዳዉዶ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሁለት":- ከባላ፡ከራያ አላማጣ እና ከኮረም አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።
3ኛ. ካራጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሶስት" ከመርሳ እና ከሀብሩ ወረዳ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።
4ኛ. አድስ ፋና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማረፊያ "ጣቢያ አራት" ቆቦ ከተማና ከራያ ቆቦ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ እንዲሆን ተወስኗል።
ከተማ አስተዳደሩ በክፍለ ከተማ እና በቀበሌ ደረጃ መላ ህዝቡ፣ አመራሩ፣ በጎፍቃደኛ ወጣቶች አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ለተፈናቃዮች እንደሚያደርጉላቸው እምነት እንዳለው ገልጿል።
ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለውን የተፈናቃይ ቁጥር በመገንዘብ ልዩ እገዛ ለማድረግ ከወዲሁ ፍቃደኝነታቸውን በመግለፅ ወደተግባር ለገቡት የከተማድ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ምስጋና ቀርቧል።

"... አጠቃላይ ነገሩን ህዝባዊ ስላደረገው (ህወሓት) እኛም ህዝባዊ አድርገን ርብርብ እየተደረገ ነው" - አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ወረዳዎች ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው "የህወሓት ቡድን" መስፋፋቱን ተከትሎ የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እጅግ ከፍተኛ በሆነ ህዝባዊ ንቅናቄ አካባቢውን እየተቆጣጠረና እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልጿል።
አስተዳደሩ ወደ ግንባር አካባቢ የደረሰ ኃይል እንዳለም አመልክቷል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ትላንት ምሽት በፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት ቃል እሳቸው የሚያስተዳድሩትን ዞን በሚያጎራብቱ የሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች ህወሓት በመድረሱ እና እንደ አንድ ግንባር እየመጣም በመሆኑ የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመመከት ህዝቡን በማነቃነቅ እና የፀጥታ መዋቅሩን በመጠቀም (ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ) ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ህወሓት ነገሩን ሁሉ ህዝባዊ እንዳደረገው ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው የቡድኑን እንቅስቃሴ ለመግታ በህዝባዊ እንቅስቃሴ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ፥ "የህዝባችንን ክብር ለማስጠበቅ እና የምትበተን ሀገር እንደማትኖር ይልቁንም ጠንካራ ኢትዮጵያ እንደምትገነባ ለማሳየት የሚያስችል መስዋእትነት መክፍል አለብን ብለን ህዝባችንም ይህን ተገንዝቦ ፤ ለህዝባችን ጥሪ አድርገን ወንድ የተባለ ሁሉ ለዚህ የሚሰለፍበት ሁኔታ እንዲኖር በማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው" ብለዋል።
በአሁን ሰዓት ዞኑ ውስጥ ምንም አይነት ነገር እንደሌለ ያነሱት አቶ ቀለመወርቅ እንቅስቃሴው ህዝባዊ መሆኑና ግንባር የደረሰም ኃይል እንዳለ እና ትግል ውስጥ የገባበት ሁኔታ መኖሩን አሳውቀዋል።