TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...ሱዳን የኢትዮጵያ መንግሥትን እና ህወሓትን ለማሸማገል ከማሰቧ በፊት ጦሯን ከኢትዮጵያ ማስወጣት እና መታመን አለባት።" - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም

ሱዳን የኢትዮጵያ መንግሥትን ከህወሓት ጋር ለማሸማገል ሀሳብ እንዳላት ዛሬ በሱዳን ሚዲያዎች ተነግሯል።

ዛሬ ከሰዓት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።

ቢልለኔ ስዩም በዚህ ወቅት ሱዳን መንግሥትን እና ህወሓትን ለማሸማገል / ለማደራደር ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ታዓማኒነት እንደማታሟላ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት ቢልለኔ የሱዳን ባለስልጣናት የካርቱም እና የአዲስ አበባ ግንኙነት እንዲሻክር ባደረጉበት በዚህ ወቅት ሱዳን ታማኝ አደራዳሪ ልትሆን እንደማትችል አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ለማደራደር በቅድሚያ እነዚህ ነገሮች መፈታት እና መስተካከል እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

ቢልለኔ በኢትዮጵየ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ህወሃት ከመንግስት ጋር ለመደራደር ሰባት ቅድመ ሁኔታ ማቅረቡን በተመለከተም መንግስት እና ህወሃት እኩል ቁመና ላይ እንዳሉ ተደርጎ መታሰብ እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

ቀርበዋል የተባሉት ቅድመ ሁኔታዎችም በ #ሽብር_ከተፈረጀ ቡድን መቅረብ የማይገባቸው መሆናቸውን ገልጸው፤ መንግስት ያወጀውን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ህወሃት በቅድሚያ መቀበል እንደነበረበትም ገልጸዋል።

የመረጃ ባለቤት : አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia