TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ICRC ወደ ትግራይ ህገወጥ ገንዘብ እና ቁስ አዘዋውሯል ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከላይ በምስሉ የሚታየው ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ የዓለም አቅፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ወደ ትግራይ ሲያስገባ አፋር ላይ በተደረገ በፍተሻ መያዙን የሚገልፁ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ICRC ዛሬ በዚሁ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ትክክለኛ እንዳልሆነ ገልጿል።

ምስሉ የዓለም አቅፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ 5 ተሽከርካሪዎች ባካተተው ኮንቮይ ከሁለት ሳምንት በፊት በአፋር ክልል በነበረው ፍተሻ ወቀት የተነሳ መሆኑን አሳውቋል።

በምስሉ የሚታየው ቁስ በሙሉ የአስቸኳት ጊዜ እርዳታ እና የህክምና ቁሶችንም የሚያካትት ሲሆን የሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግስት አካላት በቅድሚያ እንዲያውቋቸው ተደርገውና ፍቃድ ተገኝቶባቸው የተጓጓዙ ናቸው ብሏል።

ቁሳቁሶቹና ገንዘቡ ድርጅቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያደርገው ለሚሰጠው የሰብዓዊ አገልግሎት ተግባር የሚውል መሆኑን ገልጾ ሁሉም ቁሳቁሶች መቐለ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ መድረሱን አመልክቷል።

ICRC ጥሬ ገንዘብ ያጓጓዘው የባንክ አገልግሎት ባለመኖሩ መሆኑንም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

በ1,500 ሜትር ወንዶች የግማሽ ፍፃሜ በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለው አትሌታችን ታደሰ ለሚ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ለ ፍፃሜው ማለፍ #ሳይችል ቀርቷል።

በ1,500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር የመጀመሪያውን አምስት ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ አትሌቶች በቀጥታ ለፍፃሜው ውድድር የሚያልፉ ይሆናል።

የ1,500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ከ ቀኑ 8:40 ላይ የሚካሄድ ይሆናል።

*ፈጣን ሰዓት የሚያስመዘግቡ 2 አትሌቶች የ ፍፃሜ ውድድሩን የሚቀላቀሉ ይሆናል።

@tikvahethsport
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

በ1,500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ በ ሁለተኛው ምድብ የተካፈለው አትሌታችን ሳሙኤል አባተ አስራ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜው ማለፍ #ሳይችል ቀርቷል።

በሁለተኛው ምድብ አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው አቤል ኪፕሳንግ የኦሎምፒክ ሪከርድን የግሉ ማድረግ ችሏል።

የ1,500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀን 8:40 ላይ የሚካሄድ ይሆናል ።

@tikvahethsport
#ዝግጅት_ጥቆማ

ልባም ህይወት !

በኒውሮ ሊንጉስቲክ ፕሮግራሚንግ ፕሪክቲሼኔር የሚሰጥ - "መጥፎ እና ጥሩ ሀሳብ ወደ አእምሮአችን እንዴት ይመጣል?"

ፕሮግራሙ ሀምሌ 30/2013 ዓ/ም ከምሽት 12 እስከ 1:45 የሚካሄድ ሲሆን ፕሮግራሙ በነፃ የሚሰጥ ነው።

በስልክ ቁጥር 0911624348 ወይም 0911280510 ስም በቴክስት በመላክ ቦታ መያዝ እንደሚቻል አዘጋጆቹ ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

22 ወደ መገናኛ በሚወስደው መንግድ ብሉ በርድ ሆቴል አጠገብ ነው ፕሮግራሙ የሚካሄደው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የUSAID አስተዳዳሪ የሆኑት ሳማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ሲሉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ስለሳማንታ ፓወር ጉብኝት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ሳማንታ “ሰብዓዊነት አሳስቦኝ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት" ሲሉ መናገራቸውን እንደሚወራው "መንግስት ለመቀየር እንዳልመጡ ፤ ይልቁንም ሰብዓዊነት እንደሚያሳስባቸው” መናገራቸውን ገልፀዋል።

ሲመጡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይን እና ምክትላቸውን አቶ ደመቀን ለማግኘት አቅደው የነበሩት ሰማንታ ፓወር 2ቱንም ሳያገኟቸው ቀርተዋል። በዚህ ጉዳይ አስተያየታቸውን የሰጡት አምባሳደር ዲና ፥ “በነበረባቸው የስራ ጫና (ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ)” ምክንያት ፍላጎታቸው ተሳክቶ ሳያገኟቸው ቀርተዋል ብለዋል።

ምንም እንኳን እነሱን ማግኘት ባይችሉም ከእርሳቸው ተቋም ተግባር ጋር በሚገናኙ ስራዎች ዙሪያ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናትን እንደሚያገኙ ተነግሯቸው አግኝተዋል ሲሉ አክለዋል።

ሳማንታ ፓወር ካገኟቸው ባለስልጣናት መካከል ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሚገኙበት ሲሆን "ህወሃት" የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ ረግጦ መውጣቱን ለሳማንታ መናገራቸውን ገልፀዋል።

ፓወር፥ “አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በጣም ዋጋ ትሰጣለች” ያሉ ሲሆን ጉዳዩ እዚህ ደረጃ መድረስ አልነበረበትም ስለማለታቸውም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ድርድርና ውይይትን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር ዲና ምናልባት በመጪው መስከረም ወር መጨረሻ በሚመሰረተው አዲስ መንግስት ሁሉን አቀፍ (All inclusive) ውይይት እንደሚደረግና ምናልባት የህወሓት አባል የነበሩ ሰዎች ወደዚህ ውይይት ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
የተፈናቃዮች ጥሪ :

በወልዲያ ከተማ በአምስት መጠለያ ጣቢያዎች ከራያ ቆቦ እና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎች ይገኛሉ።

በወልድያ ከተማ የሚገኙት ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን #አሚኮ ዘግቧል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ሁሉም እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ወልዲያ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች የከተማው ህዝብ ላደረገላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ የሚደረግላቸው የሰበዓዊ ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የወልድያ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሙሀመድ ያሲን የከተማዋ ነዋሪዎችና ወጣቶች ተፈናቃዬቹን ለመደገፍ ላደረጉት ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባው ባለሀብቶችና የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ህወሓት በአፋር እና አማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ከ225 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው በሁለቱ ክልል መንግስታት መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#ድሬፖሊስ : በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ ፖሊስ ከዚህ ቁም ይጠቀምበት የነበረውን የደንብ ልብስ በአዲስ የደንብ ልብስ መቀየሩን በይፋ አስተዋውቋል።

አዲሱ የደንብ ልብስ ፦
- የተቋሙን ቁመና በሚገልፅ መልኩ በጥናት የቀለም (ከለር) ልዩነት የተደረገበት
- አዲሱ የተቋሙ አርማ ያረፈበት
- ቀደም ብሎ አባላት ያነሱት የነበረውን የጥራትና ተያያዥ ችግሮችን የፈታ እንደሆነ ተገልጿል።

የፎቶ ባለቤት : ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
ዛሬ ህወሓት ወልድያን የመያዝ ሙከራ አድርጎ መክሸፉ ተሰማ።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የ "ህወሓት" ቡድን ዛሬ ሐምሌ 29/2013 ማለዳ ላይ ከተማይቱን ለመያዝ ሙከራ አድርጎ እንደነበር በመጠቆም ነገር ግን ሙከራው በከባድ ቅጣት ከሽፏል ብሏል።

ከተማ አስተዳደሩ የወልዲያ ማህበረሰብ "ህወሓት" ምኞቱም ጥረቱም እስከ መጨረሻው እስኪመክን ለሚደረገው ትግል ታሪክዊና ወቅታዊ ድሉን አጠናክሮ ይቀጥል ሲልም በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳስቧል።

በአሁን ሰዓት የከተማው አመራር ከወጣቱ ጋር በከተማዋ ትግሉን እያበረታቱ ይገኛሉም ብሏል።

በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች ስለመቀጠላቸው የሚገልፁ የታመኑ ሪፖርቶች እየደረሱን ይገኛል።

ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት እስካሁን ከ2 መቶ ሺ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በርካታ ንብረት መዘረፉን፣ የንፁሃን ግድያ መፈፀሙንም የክልሉ መንግስት እያሳወቀ ይገኛል።

@tikvahethiopoa
"...ሱዳን የኢትዮጵያ መንግሥትን እና ህወሓትን ለማሸማገል ከማሰቧ በፊት ጦሯን ከኢትዮጵያ ማስወጣት እና መታመን አለባት።" - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም

ሱዳን የኢትዮጵያ መንግሥትን ከህወሓት ጋር ለማሸማገል ሀሳብ እንዳላት ዛሬ በሱዳን ሚዲያዎች ተነግሯል።

ዛሬ ከሰዓት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር።

ቢልለኔ ስዩም በዚህ ወቅት ሱዳን መንግሥትን እና ህወሓትን ለማሸማገል / ለማደራደር ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ታዓማኒነት እንደማታሟላ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት ቢልለኔ የሱዳን ባለስልጣናት የካርቱም እና የአዲስ አበባ ግንኙነት እንዲሻክር ባደረጉበት በዚህ ወቅት ሱዳን ታማኝ አደራዳሪ ልትሆን እንደማትችል አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ለማደራደር በቅድሚያ እነዚህ ነገሮች መፈታት እና መስተካከል እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

ቢልለኔ በኢትዮጵየ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ህወሃት ከመንግስት ጋር ለመደራደር ሰባት ቅድመ ሁኔታ ማቅረቡን በተመለከተም መንግስት እና ህወሃት እኩል ቁመና ላይ እንዳሉ ተደርጎ መታሰብ እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

ቀርበዋል የተባሉት ቅድመ ሁኔታዎችም በ #ሽብር_ከተፈረጀ ቡድን መቅረብ የማይገባቸው መሆናቸውን ገልጸው፤ መንግስት ያወጀውን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ህወሃት በቅድሚያ መቀበል እንደነበረበትም ገልጸዋል።

የመረጃ ባለቤት : አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#Alert🚨

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት #እየጨመረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ትላንት ለ5,916 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎ 511 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 9ቱ (9%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ትላንት በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከ68 ቀናት በኋላ የመጀመሪያው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል። በትላንትናው ዕለት ብቻ 8 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ቁጥር ከ47 ቀናት በኋላ ከፍተኛው የሞት ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

ወደ #ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 25 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 308 ግለሰቦች አሁን ላይ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፤ ይህም ከ53 ቀናት በኋላ ከፍተኛው ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

አሁንም ይህ ወረርሽኝ ችላ ሊባል የሚገባው ጉዳይ አንዳልሆነ ያስገነዘበው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወረርሽኙ የብዙዎችን ህይወት እየነጠቀ ብዙዎችን ደግሞ አካላዊ እና ማህበረሰባዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ይገኛል ብሏል።

@tikvahethiopia
"...ዛሬ 7 ሰዓት አካባቢ ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" - አቶ ማንደፍሮ ታደሰ (የላሊበላ ከተማ ምክትል ከንቲባ)

(በቢቢሲ እና ሮይተርስ)

ህወሓት ወደ ላሊበላ ከተማ መግባቱ ታወቀ።

የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ሀሙስ (7:00 ሰዓት አካባቢ) ወደ ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩ ሲነገር መቆቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ዛሬ ደግሞ ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው ገብተዋል።

የከተማዋ ም/ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬ 7 ሰዓት አካባቢ "ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" ሲሉ አረጋግጠዋል።

አቶ ማንደፍሮ የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ሲገቡ ምንም አይነት ውጊያ ሆነ ተኩስ እንዳልነበረ ተናግረዋል።

የህወሓት ታጣቂ "ከተማዋን ይዞታል" በሚል በርካታ ለደኅንነታቸው የሰጉ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እወጡ መሆናቸውን ምክትል ከንቲባው ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የተኩስ ድምጽ እንደማይሰማ የተናገሩት ም/ከንቲባው፤ "የህወሓት ታጣቂዎች በከተማዋ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችን ያወድማሉ የሚል ስጋት መፈጠሩን" ተናግረዋል።

እሳቸው በአሁን ሰዓት ከላሊበላ ከተማ ውጪ እንደሚገኙ የተናገሩ ሲሆን "ከፌደራል እና ከክልል መንግሥት ጋር ኃይል እንዲገባ እና ቅርስ እንዲታደግ ጥረት እየተደረገ ነው" ብለዋል።

የመላው ዓለም ሕዝብ ቅርስ ስለሆነ የዚህ ቅርስ ደኅንነት እንዲረጋገጥ ግፊት መደረግ አለበት" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
"...በላልይበላ በኩል ውጊያ ሸሽቶ የገባው ኃይል ከፊሉ እፈረጠጠ ለመውጣት እየሸሸ ነው" - የአማራ ክልል መንግስት

የአማራ ክልል መንግስት በኮሚኒኬሽን ክፍሉ በኩል ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው የአውደውጊያ ውሎ ፦
- በሳንቃ፣
- በአለውሃ እና በሀራ የነበረውን በሽብረተኛነት የተፈረጀው የህወሓት ቡድን ፥ "በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እና በጀግናው የወሎ ህዝብ የሥጋ ጭቃ ሁኗል ብሏል" የክልሉ መንግስት።

የአማራ ክልል መንግስት ፥ "ከአለውሃ ሸሽቶ ወደ ላሊበላ እና አካባቢው የፈረጠጠው የእሳት ራት የሆነው ቡድንም እጣ ፋንታው ከዛሬዎቹ የሳት ራቶች የተለየ አይሆንም" ሲልም ገልጿል።

በላል ይበላ በኩል ውጊያ ሸሽቶ የገባው ኃይል ከፊሉ እፈረጠጠ ለመውጣት እየሸሸ ነው የሚለው የአማራ ክልል ይህ ኃይል እንዳይወጣ ወጥመድ የተዘጋጀለት እንደሆነ ገልጾ በፀጥታ ኃይሉ በቅርብ ክትትል ውስጥ እንዳለም አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሰሜን ጎንደር በኩል የህወሓት ቡድን ተገቢውን ቅጣት እያገኘና እየተደመሰሰ እንደሆነም የአማራ ክልል መንግስት በመግለጫው አስፍሯል።

መላ ህዝቡ በህወሓት ቡድን እና ለቡድኑ በሚላላኩ አካላት አሉቧልታ ሊረበሽ አይገባም ሲልም መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ዛሬ 7 ሰዓት አካባቢ ገነተ ማርያም ተብሎ በሚጠራው በኩል ወደ ከተማዋ ገብተዋል" - አቶ ማንደፍሮ ታደሰ (የላሊበላ ከተማ ምክትል ከንቲባ) (በቢቢሲ እና ሮይተርስ) ህወሓት ወደ ላሊበላ ከተማ መግባቱ ታወቀ። የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች ዛሬ ሀሙስ (7:00 ሰዓት አካባቢ) ወደ ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች የታጣቂዎች…
#Lalibela

የህወሓት ኃይሎች በላሊበላ ከተማ በሚገኙ 3 ትምህርት ቤቶች ካምፖችን ሰርተው መቀመጣቸውን ቃላቸውን ለአል ዓይን ድረገፅ የሰጡ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

አሁን ላይ በከተማ ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ አለመኖሩንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

የከተማይቱ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶች በስጋት ምክንያት ከተማውን ለቀው መሸሻቸውን ጠቁመዋል።

በአካባቢው የነበረው የጸጥታ ሃይል ቀደም ብሎ ከተማውን ለቆ መውጣቱን የገጹትት የላሊበላ ነዋሪዎች የህወሓት ሃይሎች ሲገቡ ምንም አይነት ተኩስ ሆነ ጦርነት እንዳልተካሄደ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Alert🚨

በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 7,598 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 687 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሶስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 157 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
"... የተፈናቃዮች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመምጣቱ የሚደረጉት ድጋፎች በቂ አይደሉም" - አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን (የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)

በጦርነት ምክንያት ከሐምሌ 5 አንስቶ ከ "ሰሜን ወሎ ዞን" የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ150 ሺ በላይ ነው።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን ለአሐዱ ሬድዮ 94.3 በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው በተባባሰው ጦርነት ሳቢያ ንብረቶች መዘረፋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን ፥ ታጣቂ ኃይሎች በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ቦታዎች በመግባት ጦርነት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀው በዚህም ከዞኑ የተለያዩ አከባቢዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ150 ሺህ በላይ መድረሱን አሳውቀዋል።

ተፈናቃዮቹ ገሚሶቹ ቤተሰቦቻቸው ጋር የተቀሩት ደግሞ ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ከአደጋ መከላከልና ዝግጁነት የመጡ የተለያዩ አካላት ተፈናቃዮችን ለመርዳት እያደራጇቸው ቢሆንም ጦርነቱ እየቀጠለ በመሆኑ የተፈናቃዮች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመምጣቱ የሚደረጉት ድጋፎች በቂ አለመሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በተለይም አሁን ወቅቱ ክረምት በመሆኑ አርሶ-አደሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የእርሻ ስራቸውን የሚያከናውኑበት የነበረ ቢሆንም በተፈጠረው ድንገተኛ ጦርነት ምክንያት ስራዎች ሊሰሩ አለመቻላቸውን ዋና አስተዳዳሪው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አክለው ፥ እንደ ዞኑ ያለው የደህንነት ጉዳይ አሳሳቢ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላቶች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርጉ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
"ፆም ጣፋጭ ናት ፍሬዋም ጣፋጭ ነው"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፆመ ፍልሰታን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ፆም ጣፋጭ ናት ፍሬዋም ጣፋጭ ነው" ያሉት ቅዱስነታቸው ፤ በሱባኤው በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት እንዳይጎዳ ጥንቃቄ በማድረግ ስለ ሀገር በመጸለይ በንሥሐ እና በፍቅር ማሳለፍ ይገባል ብለዋል።

* የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia