TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የውሸት መረጃ⬆️በዛሬው ዕለት በአምቦ በነበረው የተማሪዎች ምርቃት ፕሮግራም ላይ ቦምብ ሊጥል ሲል እጅ ከፍንጅ ተያዘ የተባለው ወጣት ወሬ ሀሰት ነው፡፡ ልጁ የተያዘው በኪስ አውላቂነት ተጠርጥሮ መሆኑን #ጃዋር_መሀመድ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል።

•ወዳጆቼ በተቻለ መጠን የሚደርሱንን መረጃዎች እንደወረዱ ከመቀበል፣ ሼር ከማድረግ፣ ሰዎች ላይ ከመፍረድ፣ ይልቅ ቀድመን እውነታውን ልናጣራ ይገባል፡፡

*አንዳንዶች የልጁ ብሄር ይሄ ነው እያሉም ሲፅፉ ነበር። ይህ አግባብነት የለውም። እባካችሁ ለጅቦች ራሳችንን አሳልፈን አንስጥ። ያጠፉ ሰዎችን መፈረጅ ምንም ማለት አይደልም፣ ያጠፉ ሰዎችን መውቀስ ምንም አይደልም፣ ስለ አንድ ቡድን ጥፋት እና ክፉ ስራ መናገር ችግር የለውም ስህተቱ በነዛ ሰበብ ሁሉንም ማጠቃለሉ ላይ ነው። ይህንን ፈጣሪም አይወደውም። ሰዎች ወደው ባላመጡት ብሄር እና ዘር ሊሰቃዩ በፍፁም አይገባም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ከዶክተር አብይ ጋር ወደፊት!
#TEAMLEMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስንደመር ከልብ ይሁን፣ ስንደመር በእውነተኛ ፍቅር ይሁን፣ ስንደመር ለመረዳዳት ይሁን፣ ስንደመር ለመከባበር ይሁን፣ ስንደመር በእውነተኛ የይቅር ባይነት መንፈስ ይሁን፣ ስንደመር ለእውነተኛ አንድነት ይሁን።

መደመራችን ሰዎች ላይ ለመፍረድ፣ ሰዎችን ለመጥላት፣ ሰዎችን ለመውቀስ፣ ያለፈውን እያነሱ ለመወቃቀስ፣ መልካም ስራዎችን ለመርሳት፣ የተሰሩትን አፍርሶ እንደአዲስ ለመጀመር፣ የራስን አስተሳሰብ በሰዎች ላይ ለመጫን፣ የሰዎችን ማንነት ላለመቀበል፣ የሰዎችን መብት ላለማክበር አይሁን።

የምናውራውን ካልኖርነው አንድ እርምጃ ወደፊት አንራመድም። ፍቅር ያሸንፋል ስንል እውነተኛ የፍቅር ሰዎች ልንሆን ይገባል።

💪እኛ ወጣቶች የዛሬዋ ኢትዮጵያ በእጃችን ላይ ናት ተፋቅረን፣ ተዋደን፣ ተከባብረን፣ አንድ ሆነን እናት ሀገራችንን ሀያል ልናደርጋት ይገባል።

⭕️ብሄር አይለየንም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነታችን ከብሄር ይገዝፋል!

⭕️ዘር አይለያየንም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነታችን ከዘር ይገዝፋል!

ለሰው ልጅ ሁሉ፤ ለኢትዮጵያዊ ሁሉ ፍቅርና ሰላም ይብዛለት!

ከዶክተር አብይ ጋር ወደፊት!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
#TeamLemma
@tsegabwolde @tikvahethiopia