TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

አልኮል ፦

- አልኮል በዓለም ላይ 3 ሚለዮን ለሚሆኑ ሞቶች አስተዋፅኦ ያደርጋል፤ እንዲሁም ደግሞ ከ200 በላይ ላሉ አካላዊ እና አዕምሮአዊ የጤና ችግሮች መንስኤ ነው፡፡

- ምንም እንኳን እንደሚወሰደው መጠንና የጊዜ ብዛት ቢለያይም የትኛውም አልኮል መጠን ጤና ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡

ከሚያስከትለው የጤና ችግር በጥቂቱ ፦
አዕምሮን ነገሮችን የሚመለከትበትን መንገድ በመቀየር የባህሪ ችግር እንዲኖርና ነገሮችን በትክክል ማሰብ እንዳይችል ያደርጋል፤ አልፎም ተርፎም ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ በማወክ ለአዕምሮ ቀውስ ይዳርጋል።
የልብ አመታት ችግር
የልብ ጡንቻዎች መድከም
ስትሮክ
የደም ግፊት
የጉበት ህመም ፤ ጉበትን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ስራውን እንዲያቆም ብሎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡
የተለያዩ ንጥረ ቅመሞችን የሚያመርተው ቆሽት መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን እንዲያመርት፤ በዚህም ምክንያት ለራሱም እንዲሁም ሌሎች አካላትን እንዲጎዱ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ለስኳር እና ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
በቀን ውስጥ 1 የአልኮል መጠጥ የምትጠጣ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድሏ ከ 5-9% ያህል ከማይጠጡት ይልቅ ይጨምራል፡፡
የአንጀት ካንሰርን ጨምሮ አልኮል የብዙ ካንሰር ዓይነቶች መንስኤ ነው፡፡
ብዙ አልኮል መጠቀም የበሽታ መከላከል አቅምን በመቀነስ ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡ 
ትምህርት ላይ ባለው ተፅዕኖ፤ የጤና እክልን በማምጣትና ያለዕድሜ ህይወት እንዲያልፍ በማድረግ ምርታማነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

በየቀኑ ወይም ደግሞ በአንድ ጊዜ ብዙ የአልኮል መጠን መውሰድ በየቀኑ ለምንሰራቸው ስራዎች እንቅፋት ይሆናል፤ በአካልም በስነልቦናም የአልኮሉ ጥገኛ ሆነን ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፤ ይህን ችግር ራሳችን ላይ ካየነው እርዳታ በመፈለግ ህክምና ማግኘት ይኖርብናል፡፡

በቅርብ ያሉ ቤተሰቦቻችን ወይም ጓደኞቻችን ላይ ይህን ችግር ካየን ለአዕምሮቸውም እንዲሁም ለአካላቸው ጤና ስንል ከማግለል ይልቅ ተገቢውን እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

#PAHO #WHO

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia