TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ይኽን አስተውለው ያውቃሉ?

- በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መስማት የተሳናቸው ወገኖቻችን ይገኛሉ።

- ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የምልክት ቋንቋ ባለቤት ናት፤ ይህ ማለት ይህንን ቋንቋ ሚሊዮኖች ይናገሩታል ማለት ነው።

- ቋንቋ መግባቢያ ሲሆን የምልክት ቋንቋም እንደማንኛውም ቋንቋ ከሰዎች ጋር የምንነጋገርበት፤ የምንግባባበት ነው።

እጆች ይናገራሉ .... አይኖች ያዳምጣሉ ስንል፦

- በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያለው ይኽ ቋንቋ በፖሊሲም ሆነ በአፈጻጸም ትኩረት እንዲሰጠው፤

- መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከሌሎች ዜጎች እኩል የመስራትና የመማር እድል እንዲፈጠርላቸው፥ እንዲሁም በወረቀት የተከበረላቸው ህጎች በተግባር እንዲተገበሩ፤

- መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች በተለይም ለሴቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጥ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ነው።

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia      @RWethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ዜጎች ይኖራሉ?

በወቅታዊ ጥናት ላይ ተሞርክዞ የቀረበ መረጃ ባይኖርም እንደማሳያ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ፣ የዓለም የጤና ድርጅትና የዩኒሴፍ ጥናቶችን መመልከት ይቻላል፡፡

የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በ2005 ዓ.ም በሰራው ዳሰሳ ኢትዮጲያ ከህዝብ ቁጥሯ 3 በመቶ የሚሆነው አካል ጉዳተኛ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከዚህ ውስጥም 20 በመቶ ሚሆኑት (720 ሺ) መስማት የተሳናቸው መሆናቸውን ይጠቅሳል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በ2003 ዓ.ም ባወጡት ሪፖርት ከኢትዮጲያ ከህዝብ ቁጥሯ 15 ሚሊዮን ዜጎቿ (17.6 በመቶ) አካል ጉዳተኛ መሆናቸውን ገልጾ፤ ከዚህ ውስጥም 20 በመቶ ሚሆኑት (3.5 ሚሊዮን በላይ) መስማት የተሳናቸው ይላል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በ2013 ዓ.ም ባወጣው ቁጥራዊ ማስረጃ (Fact Sheet on Deafness and Hearing loss) ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ5 ሚሊዮን በላይ መስማት የመስማት ችግር ያለባቸው ዜጎች መኖራቸውን ይጠቅሳል።

ዩኒሴፍ ከሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር በ2008 ዓ.ም በሰራው ዳሰሳ የአካል ጉዳተኛ ዜጎች ከአጠቃላይ የህዝብ ቁጥሩ 9.3 በመቶ (7.8 ሚሊዮን) መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ ከላይ በሁለቱም ጥናቶች የተወሰደውን ስሌት ተጠቅመን 20 በመቶዎቹ መስማት የተሳናቸው ናቸው ብንል ከ1.5 ሚሊዮን በላይ መስማት የተሳናቸው ዜጎች ይኖራሉ።

#ማስታወሻ፡ በተለያየ ጊዜያት የተሰሩትና ማግኘት የቻልናቸው የጥናት ውጤቶች ግኝት በጣም የተራራቁ ቢሆንም ለማሳያ ያክል የቀረቡ ናቸው። ቁጥራዊ መረጃዎቹ ወቅታዊ መረጃን ገላጭ አይደሉም፡፡ ተጨማሪ መረጃዎች ካሎት @RWethiopia ላይ ያካፍሉን

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በኢትዮጵያ ምን ያህል መስማት የተሳናቸው ሰዎች እንዳሉ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ከመስማት ጋር የተገናኘ ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንደሚኖሩ ይገመታል።

የምልክት ቋንቋዎች የራሳቸው ሰዋሰው፣ መዝገበ ቃላት እና ዘዬ ያላቸው የተሟሉ፣ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ ከውልደት ጀምሮ መስማት ለተሳናቸው ሕጻናት ደግሞ ብቸኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ነው፡፡

ከኢትዮጵያ የብሔር ብዝኃነት አንጻር ተጨማሪ ቋንቋዎችን በሥራ ቋንቋነት ለማካተት የሚያስችል የቋንቋ ፖሊሲ በቀረጻ ሂደት ላይ መሆኑ ቢታወቅም፤ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የግድ አስፈላጊ የሆነውን የምልክት ቋንቋን የሥራ ቋንቋ ለማድረግ በቂ ትኩረት አላገኘም።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በዚህም የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባት።

የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የሚኖራቸውን የተሳትፎ መጠንና የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ ብሎም ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉና ውጤታማ በሆነ ደረጃ እንዲረጋገጡ ለማስቻል አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡

ሙሉ ጹሑፉን ለማንበብ https://ehrc.org/expertview

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia
የትኞቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ ናቸው?

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች።

በስምምነቱ መሰረትም ፈራሚ ሀገራት መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የምልክት ቋንቋ ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ እንዳለባቸው ይጠቅሳል። (አንቀጽ 24፣ 3/ለ)

በተጨማሪም ፈራሚ ሀገራት [መስማት የተሳናቸው ሰዎች] በሁሉም የሕግ አሠራር ሂደቶች ከሌሎች ጋር በእኩልነት አስተማማኝ የፍትሕ ተደራሽነት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸውም ይላል፡፡ (አንቀጽ 13)

እርሶ በየትኛው የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋም መስማት የተሳናቸው ዜጎችን በተለይ ሴቶችን ያማከለ አገልግሎት ሲሰጥ ታዝበዋል? 👉 @RW_Ethiopia ያካፍሉን

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትኞቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ ናቸው? ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነትን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 አጽድቃ ተቀብላለች። በስምምነቱ መሰረትም ፈራሚ ሀገራት መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የምልክት ቋንቋ…
በኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ ሕገ-መንግስታዊ እውቅና ሊሰጠው ይገባል !

በዓለም ላይ #ሰባ_አምስት ሀገራት የምልክት ቋንቋን እንደ ብሔራዊ ቋንቋ አድርገው ከመቀበል ጨምሮ በሰነድ የተደገፈ ሕጋዊ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ዙምባቡዌ ብሔራዊ ቋንቋቸው አድርገው ተቀብለውታል፡፡

በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ያለው ይኽ ቋንቋ በፖሊሲም ሆነ በአፈጻጸም ትኩረት ያልተሰጠው ቋንቋ ነው፡፡

በኢትዮጵያም የምልክት ቋንቋ ሕገ-መንግስታዊ እውቅና ሊሰጠው ይገባል።

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ
አንድ ወር የሚቆይ የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ!

በሚሊዮን ለሚቆጠሩ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች፥ የምልክት ቋንቋ መግባቢያቸው ነው። የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ ደግሞ ለበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች ምላሽና ለዕኩል እድል ተጠቃሚነት በር ከፋች ነው።

በዓለም ላይ 75 ሀገራት የምልክት ቋንቋን እንደ ብሔራዊ ቋንቋቸው መቀበልን ጨምሮ በሰነድ የተደገፈ ሕጋዊ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ዙምባቡዌ ብሔራዊ ቋንቋቸው አድርገው ተቀብለውታል፡፡

በኢትዮጵያም የምልክት ቋንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንጠይቅ!

በሀገራችን ይህ ተፈጻሚ እንዲሆን #እየተጠየቀ ነው። እርሶም ድምጽ በመስጠት፤ የተዘጋጀውን የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ በመቀላቀልና ለሌሎች በማጋራት #በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች ድምጽ ይሁኑ።

ለመፈረም፦ https://chng.it/zJwncqjqC5

በጉዳዩ ላይ ሞያዊ ሂስና አስተያየት ለመስጠት [email protected]

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ