TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቶለማበቀለ👏

አቶ ለማ በቀለ አለሙ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴኪዩሪቲ ክፍል ውስጥ ነው የሚሰሩት።

በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምግባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት ማስመስከራቸውን አየር መንገዱ ገልጿል።

አቶ ለማ በሥራ ገበታቸው ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ መንገደኛ ረስተዉ የሄዱትን የእጅ ቦርሳ ውስጡ ከነበረው 71 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ምንም ሳያጎድሉ በሙሉ ለሚመለከተው የአየር መንገድ ቢሮ ያስረከቡ ሲሆን፤ አየር መንገዱም አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ንብረቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ ተደርጓል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM