TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተጣለው ጊዜያዊ እገዳ ተነስቷል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲስ ስታንዳርድ የበየነ መረብ ሚዲያ ላይ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ማንሳቱን ተሰምቷል። ባለሥልጣኑ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው እገዳውን ለማንሳት መወሰኑን ያስታወቀው። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ለአሜሪካ…
#Update

ላለፉት ቀናት ስራውን አቆርጦ የነበረው 'አዲስ ስታንዳርድ' የበየነመረብ ሚዲያ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ወደ ስራው መመለሱን ገልጿል።

ዓመታትም በኦንላይን ሚዲያነት የሰራው 'አዲስ ስታንዳርድ' ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት በጣም ጥቂት #በእንግሊዘኛ ቋንቋ የመረጃ ማቅረብ አገልግሎት የሚሰጥ ድረገፅ ነው።

ከሰሞኑን የኢመብባ "አዲስ ስታንዳርድ" በሕወሓት የሚመራውን ኃይል “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በመድረስ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ ሆኗል” በሚል ሚዲያውን በጊዜያዊነት ማገዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በኃላ ሁለቱ አካላት ውይይት አድርገው መግባባት ላይ ደርደው እገዳው ተነስቷል።

አዲስ ስታንዳርድ፣ አስቀድሞም እገዳ የተጣለበት ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑን ከእገዳው መነሳት በኃላ ባወጣው መግለጫ ገልፆ ነበር።

ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ድረገፁ ወደቀደመ መደበኛ አገልግሎቱ ተመልሷል።

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

👉 ሙሉ ስም
👉 የመታወቅያ ቁጥር
👉 ትምህርት ክፍል
👉 የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

@tikvahethiopia
በሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ተማሪዎችን ሲያስተምሩና ደመወዝ ሲበሉ የቆዩ ግለሰቦች ተፈረደባቸው።

ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማሰራት በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ 3 ግለሰቦች ያለ ብቃታቸው እና ያለ ሙያቸው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው ክስ ተመስርቶባቸው ውሳኔ ተላለፈባቸው።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ፣
2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ፣
3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ የተባሉት ግለሰቦች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ውስጥ " አንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ያለ ሙያቸው እና ያለ ብቃታቸው ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ተይዘው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ ፦ ከአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ #በባዮሎጂ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 10/04 /2011 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያየ የደመወዝ መጠን #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 215 ሺህ 739 ብር ተከፍሎታል።

2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ #በእንግሊዘኛ  መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከ04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 800 ብር ተከፍሎታል።

3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ በሂሳብ ትምህርት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 008 ብር ደመወዝ ተከፍሎታል።

ሶስቱም ተከሳሾች ያለሙያቸውና ብቃታቸው ሲያስተምሩ በቆዩባቸው ጊዜያት በተማሪዎች ላይ በገንዘብ የማይተመን እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እና በመንግሥት ላይ ባልተገባ መልኩ በተቀበሉት ደመወዝ 455, 755 የሚገመት ብር ጉዳት አድርሰዋል።

ዓቃቤ ህግ በፈፀሙት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት እና በመገልገል በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል።

የበሉትን ደመወዝም እንዲመልሱ በክሱ ላይ ቀርቧል።

የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸው በማለት ሶስቱም ተከሾች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እንዲሁም ያለአግባብ የበሉትን አጠቃላይ 455,755 ብር ለመንግሥት እንዲመልሱ ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopia