TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ችሎት !

ፍርድ ቤት የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ፍርድ ለመስጠት በድጋሚ ቀጠረ፡፡

አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ በቦሌ ክ/ከ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ያለአግባብ ወስደዋል ተብለው በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ዓቃቢህግ አራት ምስክሮች አቅርቦ አሰምቶ ነበር፡፡

የአቶ የሙሉጌታ ጠበቆች አንድ የአይን ዕማኝ እና አንድ ባለሙያ አቅርበው መከላከያ ምስክር አሰምተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የቀጠረ ቢሆንም በጽ/ቤት የምስክር ቃል ተገልብጦ የደረሰኝ አሁን በመሆኑ መርምሬ አላጠናቀኩም ሲል በድጋሚ ፍርድ ለመስጠት ለሀምሌ 19 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል፡፡

አቶ ሙሉጌታ በዚሁ ክስ በ80 ሺህ ብር ዋስ ከዕስር የተፈቱ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 11 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ ያለአግባብ ወረራ አድርገዋል ተብለው በቀረበባቸው አንደኛው ክስ ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ነጻ እንዳላቸው ይታወሳል፡፡

መረጃው የጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ነው።

@tikvahethiopia
የሰብአዊ እርዳታ ወደ መቐለ እየገባ ነው።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሁለት ሳምንት ወደ ትግራይ ሲጓጓዝ የነበረ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቐለ ከተማ እየገባ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገፃ አሳውቋል።

 “አሁንም በትግራይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 2.1 ሚሊዮን ሰዎች ለመድረስ 1 ሺህ ሜትሪክ ቶን የህይወት አድን ምግብ ማዳረስ ያስፈልጋል” ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አመራሮች እና የየመስተዳድር አካላት የተካተቱበት ልዑክ ተፈናቃዮች በሚገኙበት አራት የጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ከነበሩ ወገኖች ጋር የጋራ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል። ውይይቱ በግዜያዊ መጠለያ ጣቢያው የሚያጋጥሙ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ አተኩሮ የተካሄደ ነበር።

የመተከል ዞን የተቀናጀው ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት አባል የሆኑት ብ/ል ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ተፈናቃዮችን ቋሚ ተፈናቃይ አድርጎ በማቆየት በግላቸው የሚጠቀሙ ሀይሎች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን የእነዚህን ሀይሎች ሴራ መረዳትና በጋራ መታገል አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለህዝቡ የሚቀርበውን የምግብ እህሎችን ሸጠው ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በህዝቡ ተሳትፎ በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉንም አስታውሰዋል። ይሄ ተግባር በቀጣይነት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ልዩ ልዩ የመመገቢያ ቁሳቆሶች እና ሰብአዊ እርዳታዎች መድረስ ከሚገባው ግዜ መዘግየቶች ማጋጠማቸውን የጠቆሙ ሲሆን አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
#USA

"የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለውም" - አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ፤ ትላንት እሁድ በሰጡት ቃል አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ብቸኛው መፍትሄ ዲፕሎማሲ ነው ብላ ታምናለች ብለዋል።

ከTeN የሳተላይት ቻናል ቃለምልልስ የነበራቸው ዋርበርግ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ ለአፍሪካ አህጉር እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ዓላም አቀፉ ማህበረሰብ የህዳሴው ግድይ ጉዳይ ለናልይ ተፋሰስ ቀጠና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ተገንዝቧል ብለዋል።

ዋርበርግ፥ የግድቡ ጉዳይ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በማንሳት "በአፍሪካ አህጉር ምንም አዲስ ጦርነት ልንገምት አንችልም" ብለዋል።

የተፋሰሱ አገራት እና የ #አፍሪካ_ህብረት ድርድርን እንደገና መጀመር እንዳለባቸው ጠቁመው አሜሪካ ማንኛውንም የፖለቲካ ወይም የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል።

ዋርበርግ፥ "ውይይቱን ለመቀጠል አሜሪካ ሁሉም ወገኖች ከማንኛውም መግለጫ እንዲታቀቡ ጥሪ ታደርጋለች ፤ የሚደረገው ማንኛውም ውይይት ድርድሮችን ወደፊት ለማስቀጠል ያለመ መሆን ይገባዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ድርድሩ ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያልፍ አትፈልግም ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹 #Russia🇷🇺

ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ያተኮረ የ3 ቀናት ውይይት ሲካሄድ ነበር።

ውይይቱ ዛሬ የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውይይት በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን ተመልክቷል።

አሁን ላይ የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየውን ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የመከላከያ ሰራዊቱን አቅም በእወቀት፣ በክህሎት እና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑም ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።

መረጃው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ቀን የኮቪድ-19 ሞት አልተመዘገበም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 የሞተ ሰው የለም።

በሌላ በኩል ከተደረገው 4,358 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 66 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በትላንትናው ዕለት 33 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ በኩዋዙናታል እና በሃውቴን ፕሮቪንሶች በዋናነት በደርባን እና በጆሃንስበርግ እንዲሁም በዙሪያቸው በሚገኙ ከተሞች እና ሎኬሽኖች በሚገኙ የቢዝነስ ተቋማቶች ላይ ያነጣጠረ የዝርፊያና የማቃጠል/ማውደም እየደረሰ ነው።

ይህን ክስተት የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ትላንት ምሽት አሳውቀዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በደ/ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ማምሻውን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

በኩዋዙናታል እና በሃውቴን ፕሮቪንሶች በዋናነት በደርባን እና በጆሃንስበርግ እንዲሁም በዙሪያቸው በሚገኙ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ሰለባ እንዳይሆኑ ፦
- ከሀገሪቱ መንግስት ፣
- በደ/አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
- ከማህበረሰቡ ሚዲያዎች
- ከአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች የሚሰጡትን የጥንቃቄ መልዕክቶች በትኩረት እንሲከታተሉ እና ራሳቸውን ከጥቃት እንዲሁም አቅም በፈቀደ መጠን ንብረታቸውን ከዝርፊያ እና ውድመት እንዲከላከሉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ALERT

ኑሯችሁን በደቡብ አፍሪካ ያደረጋችሁ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሰሞኑን የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የተጀመረው ረብሻ አሁን መልኩን ቀይሮ የስደተኛ ንብረቶች እና የሀገሪቱ ትልልቅ ካምፓኒዎች (Checkers and Shopright ) የመሳሰሉትን ማውደም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ስለዚህም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የምትኖሩ #ኢትዮጵያውያን እራሳችሁን ከጥቃት እንድትጠብቁ እና የሀገሪቱን ሚዲያዎች በትኩረት እንድትከታተሉ አደራ እንላለን።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትላንት ማታ የደ/ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲርል ራማፎሳ " ግጭት እያስከተሉ ያሉ ተቃውሞዎች እንዲቆሙ የጠየቁ ሲሆን፤ "ለዚህ አመጽ እና የንብረት ውድመት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም" ማለታቸው የሚታወስ ነው።

Faya (Tikvah-Family)
South Africa
Limpopo

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrArkebeOqubay የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ለዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ድጋፉን ሰጠ። በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ህብረት ለUNIDO ዋና ዳይሬክተርነት እንዲወዳደሩ እጩ አድርጎ ላቀረባቸው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ድጋፍ መስጠቱን Africa-newsroom.com አስነብቧል። የአፍሪካ የፋይናንስ ፣ ዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ጉባኤ አባል ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ዶክተር አርከበ ዕቁባይን…
#Update

የጀርመን የፌዴራል የምጣኔ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት/UNIDO/ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመረጡ።

ሙለር በዋና ዳይሬክተርነት የተመረጡት በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ቦርድ አማካኝነት ነው፡፡

የቦርዱ ምርጫ የድርጀቱ ከፍተኛ አካል በሆነውና እንደፈረንጆቹ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 3/2021 በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

አዲሱ ተመራጭ ጀርመናዊው የወቅቱ የኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ገርድ ሙለር “ ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትን መምራት ይችላል በሚል፤ ለተጣለበኝ እምነት እጅጉን አመሰግናለሁኝ ”ብሏል፡፡

ለUNIDO ዋና ዳይሬክተርነት ከተወዳደሩት መካከል እና ፉክክሩን አሸንፈው እንደሚመረጡ የብዙዎችን ቅድመ ግምት አግኝተው የነበሩት የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪና በኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች ላይ የካበተ ልምድ እንዳላቸው የሚታመንባቸው ዶ/ር አርከበ ዑቅባይ ስይሳካላቸው ቀርቷል።

ዶ/ር አርከበ ከጀርመኑ ገርድ ሙለር እና ከቦልቪያው በርናንዶ ካልዛዲላ ጋር ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ነበር የቆዩት።

መረጃው የአል ዓይን ነው።

Photo Credit : Luis J. Campuzano

@tikvahethiopia
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል።

የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሰጣል።

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።

በወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ፈተናው ትግራይ ክልልን እንደማያካትት ተገልጿል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

በሀገሪቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች #የኢኮኖሚክስ_ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ መሆኑን ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሯ በዛሬ መግለጫቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰጠ ስላለው ስለኮቪድ-19 ክትባት መረጃ ሰጥተዋል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት እንደወሰዱ ከ42 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ የሁለተኛው ዙር ክትባት እንደወሰዱ አሳውቀዋል።

ክትባቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰተ እጥረት መዘግየቱን ያነሱ ዲሆ በቅርቡ 400 ሺህ የሚጠጋ የአስትራዜኒካ ክትባት ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከአርብ ጀምሮ ደግሞ በክልሎች የመጀመሪያውን ክትባት ከወሰዱ 3 ወር የሞላቸው ዜጎች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋን።

ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማግኘት የማፈላለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህኛው ዙር ክትባት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ዝርዝር ፦

• የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች ( የአውቶብስ እና የሚኒባስ ሹፌሮች)፣
• የመንግስትና የግል ባንኮች ሰራተኞች፣
• የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ቢሮዎች ሰራተኞች፣
• የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የማረሚያ ቤቶችና የፍርድ ቤቶች ሰራተኞች
• የውልና ማስረጃ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች፣
• መምህራን የህጻናት ማቆያ የመደበኛና የኮሌጅ መምህራን፣
• የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰራተኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

NB : የመጀመሪያ ዙር ክትባት የሚወስዱ ዜጎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ከ3 እስከ 4 ሳምንት ስለሚሰጥ ዜጎች ክትባቱን እንዲወስዱም ዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
3 አጭር መረጃ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ፦

#1

የኢፌድሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር ሂደት በጋራ ተቀባይነት ያለው ውጤት ለማምጣት እንዲሁም ስኬታማ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ስለሚያስችል በኢትዮጵያ በኩል ለድርድሩ ቁርጠኝነትና ከፍተኛ ተነሳሽነት መኖሩ ገልጿል።

የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ ተመድ የጸጥታ ምክር ቤት መወሰዱ ተገቢ እንዳልነበር አንስቷል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በቀረበው የደረጃ አካሄድ ላይ ለመስራት ዝግጁ በመሆኗ ግብፅም ሆነ ሱዳን ሂደቱን ወደፍሬ ለማምጣት በቅን ልቦና እንዲደራደሩ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያበረታታ ተገልጿል፡፡

#2

የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለዋና ፀሀፊው ግንባታው ስላለበት ሁኔታ፣ ሰለሁለተኛ ዙር ሙሌት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ስለሚካሄደው ድርድር ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

#3

የፀጥታው የም/ቤት አባላት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች በመገንዘብ ጉዳዩ ወደአፍሪካ ህብረት እንዲመለስ መደገፋቸውን እንደሚያደንቁ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተለመደው ሁሉን አቀፍ እና ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት መንገድ ለመደራደርና ሂደቱንም ለመቋጨት ዝግጁ ነች ብለዋል፡፡

"ሀገሬ ኢትዮጵያን ወክለን በመቅረብ እውነቱ በመገለጡ የተሳካ ውጤት አግኝተናል" ያሉት ሚንስትሩ "ኢትዮጵያ መፍትሄው በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በድርድር ይፈታል እንጂ የደህንነት ስጋት አድርጎ በመሳል በዓለም አቀፍ አካላት ሊታይ አይገባም ብላ ታምናለች" ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል። የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት ወር ይሰጣል። ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ ገልጿል። በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች…
የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት ወር የሚሰጥበት ምክንያት ምንድነው ?

የትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ገፁ ላይ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይፋ ማድረጉን አስነብቧል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ፈተናው ጥቅምት ወር ላይ እንዲሰጥ የተወሰነበትን ምክንያት እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦

- በክረምት ወቅት ፈተና መስጠት አስቸጋሪ በመሆኑ
- ከፍተኛ የተፈታኝ ቁጥር በመኖሩ (ከ620,000 በላይ)
- ከተፈታኞች ብዛት አንጻር በቂ #የህትመት ጊዜ በማስፈለጉ
- በክረምት ወቅት ፈተና መስጠቱ ከስረጭት አንጻር ከ2,200 በላይ ወደ ሚሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ፈተና ለማጓጓዝ እና ለማድረስ አመቺ ባለመሆኑ
- የትግራይ ተማሪዎች ጉዳይ፣
- የዩኒቨርሲቲ የቅበላ ጊዜ፣
- ክልሎች ፈተናውን ለመስጠት ያላቸው ዝግጁነት፣
- በመስከረም ወር ተደራራቢ በዓላት መኖራቸው
- የፌዴራልና የክልል የመንግስታት የምስረታ ወቅት በመሆኑ ፈተናው ጥቅምት አጋማሽ እንዲሰጥ ተወስኗል ብለዋል።

የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመቅረቱ በ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ620 ሺ በላይ ተማሪዎች (99%) መመዝገባቸው ተገልጿል።

ይህም በ2012 ዓ/ም ለ አገር አቀፍ ፈተና ከተመዘገቡ 350 ሺህ ተማሪዎች በእጥፍ ያህል ብልጫ እንዳለው ነው የተነገረው።

መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከNEAEA የተሰባሰበ ነው።

@tikvahuniversity
#UNHCR

የUNHCR ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ደህንነትን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በትግራይ ግጭት ከተጀመረ አንስቶ ስደተኞቹ በሁለት ተዋጊ አካላት መሃል ለመውደቅ መገደዳቸውን ፣ ሁለት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች መውደማቸውን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለማትረፍ ዳግም ለመሰደድ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ኤርትራውያን ስደተኞች በአንድ ወይም ሌላ ወገን ደጋፊነት ተፈርጀው #የበቀል_ጥቃት እየደረሰባቸው እንዲሁም ተጠልፈው እየተወሰዱ እና እየተያዙ ስለመሆኑ የተጣሩ እና በማስረጃ የተደገፉ ሪፖርቶች ለኮሚሽኑ መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በማይ አይኒ እና በአዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚገኙ ስደተኞች ላይ በተለያዩ ታጣቂዎች በተለይ ማታ ማታ የሚፈፀሙ አጠቃላይ የወንጀል ድርጊቶች በእጅጉ ረብሸውኛል ብለዋል።

ባለፉት ሳምንታት ሽረ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ለእስር ተዳርገዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፣ በመቐለ የሚገኙ አካላት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ እንዲሁም በሕገ-ወጥ መንገድ የታሰሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በጣም ከባድ የሆኑ የኃይል ጥቃቶች እየደረሱ ስለመሆኑ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ በመሆኑ፣ የፌደራል መንግሥትም ሆነ በትግራይ ክልል ያሉ አካላት በእነዚህ ተዓማኒ ክሶች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia