#EthioTelecom
ኢትዮ-ቴሌኮም በ2013 በጀት ዓመት 56.5 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የዕቅዱን 101.7% እንዲሁም የደንበኞች ብዛት 56.2 ሚሊዮን በማድረስ የዕቅዱን 108% ማሳካቱን ዛሬ አሳውቋል።
ኢትዮ-ቴሌኮም በ2013 በጀት አመት ያስመዘገበውን ውጤታማ አፈጻጸም በማስመልከት ለ3 ቀናት የሚቆይ ነፃ አገልግሎት ለደንበኞቹ ፈቅዷል።
በዚህም 1 GB የኢንተርኔት እና 303 ፍሌክሲ ነፃ ስጦታ ለደንበኞቹ አቅርቧል።
ስጦታው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት (እስከ ሀምሌ 9/2013) ድረስ የሚቆይ ነው።
ስጦታው ከሌሊት 6 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ብቻ ስራ ላይ የሚዉል መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
Photo Credit : Ethio-Telecom
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ALERT ኑሯችሁን በደቡብ አፍሪካ ያደረጋችሁ የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሰሞኑን የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው የተጀመረው ረብሻ አሁን መልኩን ቀይሮ የስደተኛ ንብረቶች እና የሀገሪቱ ትልልቅ ካምፓኒዎች (Checkers and Shopright ) የመሳሰሉትን ማውደም ላይ ትኩረት አድርጓል። ስለዚህም ደቡብ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video : በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች የተነሳውን ረብሻ ለመቆጣጠር ሠራዊቷን አሰማርታለች።
ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በተነሳው ረብሻ ቢያንስ 45 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ወደ 800 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የተገደሉት ሰዎች 19ኙ ከጉዋቴንግ እንዲሁም 26ቱ ከኩዋዙሉ-ናታል ናቸው።
ዝርፊያውም ተባብሶ ቀጥሏል፤ ረጅም አመት በደ/አፍሪካ የኖሩ ኢትዮጵያውያን ለፍተው ጥረው ያፈሩት የላባቸው ውጤት በነውጠኞቹ ተዘርፏል።
Video Credit : AFP

#Tigray #Amhara
የትግራይ እና አማራ ክልል ዕለታዊ የተጠቃለለ ሪፖርት ፦
የአማራ እና ትግራይ ክልል ውዝግብ ውስጥ የከተታቸው የአዋሳኝ አካባቢዎች ጉዳይ በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ከተወጀ እና የፌዴራል የፀጥታ ሃይሎች የትግራይ ከተሞችን ለቀው ከወጡ በኃላ ከወትሮ በተለየ ተካሯል ፤ ውጥረቱ እጅግ አይሏል።
በሁለቱ ክልሎች ጉዳይ የሚፅፉ የማህበራዊ ሚዲያዎችም በጦርነት ድባብ ተሞልተዋል፤ አንዳንዶቹ ወጣቶች ታጥቀው እንዲዋጉ ጥሪ ሲያቀርቡ ይታያል።
ከጦርነት ቅስቀሳ በተጨማሪ የጥላቻ ንግግሩ እና ሀሰተኛ መረጃው ስርጭት ተባብሷል።
ዘመናትን አብረው በጋራ በኖሩት የትግራይና አማራ ህዝቦች መካከል አስከፊ ደም አፋሳሽ ግጭት ሳይካሄድ እና የማይፋቅ ጠባሳ ከማስቀመጡ በፊት ሁሉም የታጠቀ ኃይል ትጥቁን አውርዶ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ የሚያቀርቡም ብዙ ናቸው።
ከአማራ ክልል በኩል የ "ሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር" ለህዝቡ የክተት አዋጅ ሲያውጅ ፣ አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ለህዝባዊ ትግል ጥሪ አቅርቧል ፤ የክልሉ መንግስት ደግሞ የአማራ ህዝብ "ለዕልውና ትግል" እንዲዘጋጅ በይፋ አሳውቋል።
የትግራይ ክልል ኃይሎች በአማራ ክልል ተያዙብን ያሏቸውን ኮረምና አላማጣ ከተሞች ማስለቀቃቸውን እና የቀሩትንም ለማስለቀቅ ውጊያ እንደሚቀጥሉ እየገለፁ ነው።
በፌዴራሉ መንግስት በኩል እስካሁን ድረስ የተሰጠ አስተያየት ፣ መግለጫ ፣ ማብራሪያ የለም።
በአማራ እና በትግራይ ጉዳይ በዛሬው ዕለት (ሃምሌ 6/2013 ዓ.ም) የወጡ ሪፖርቶችን በአጭሩ ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-Amhara-07-13

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,880 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ አድርጋ 75 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ ሰዓት #አራት ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ይህ የሟቾች አሃዝ ከሁለት ቀን በኃላ የመተመዘገበ ነው።
ትላንት 80 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እስካሁ ያለው ቁጥራዊ መረጃ ምን ይመስላል ?
የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 2929862 ሲሆን ከነዚህ መካከል 277,212 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ሲገኙ ከነዚህ መካከል 4,347ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 262,102 ሰዎች አገግመዋል።
ኢትዮጵያ እስካሁ 2,064,777 ዜጎቿን የኮቪድ-19 ክትባት ከትባለች።

#Ethiopia 🇪🇹 #Tokyo2020
ለቶኪዮ 2020 የሉዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በታላቁ ቤተመንግስት ሽኝት ተደረገለት።
በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ፦
- የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፤
- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር ዶ/ር ሂሩት ካሳው
- የኢትዮጵያ ኦሎፒክ ኮሚቴ ፕሬደዛንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፤
- የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌደረሽን ፕሬዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ
- በኢትዮጵያ የጃፓን አንባሳደር ጥሪ የተደረገላቸው ባለስልጣት፤ እንግዶች ተገኝተው ነበር።
በታላቁ ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት በተዘጋጀው የእራት ሽኝት ፕሮግራም ላይ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለሉዑካን ቡድኑ ተወካዮች ለአትሌት ለሊሳ ዴሲሳና አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አስረክበዋል።
መረጃው ከኢትዮ ራነርስ የተገኘ ሲሆን የፎቶ ባለቤቶች አማን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦሎንፒክ ኮሚቴ ናቸው።
ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ !
ተጨማሪ ስፖርታዊ ጉዳዮች በ @tikvahethsport

#Update
የሲሚንቶ ግብይትን የሚወስነው እና በንግድና ኢንዱስትሪ ተግባራዊ ሲሆን የቆየው መመሪያ መሻሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዛራ አስታወቀ።
በዚህም ሲሚንቶ ከዛሬ ጀምሮ በነፃ ገበያ ስርዓት እንዲገበያይ ተወስኗል።
ለዚህ ዋና ምክንያት ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራዎች ስለሚቀንስና ከሱ ጋር ተያይዞ የሲሚንቶ ምርት ፍላጎት ስለሚቅንስ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪ የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንዳይኖር መንግስት ከውጪ ለማስገባት ዝግጅት ማጠናቀቁና ፋብሪካዎች ምርታቸው እንዲጨምር በመደረጉ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አብራርቷል።
መረጃው የኢቢሲ ነው።
@tikvahethiopoa

"...ችግሮች የሚባባሱ ከሆነ የመንግስትን ውሳኔ ተከትሎ የሚተላለፉ እርምጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ" - ሀገር መከላከያ
መከላከያ ሰራዊት ትዕዛዝ በሚደርሰው ጊዜ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አሳወቀ።
ሰራዊቱ ይህን ያሳወቀው በህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በኩል ነው።
ኮሎኔል ጌትነት ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ "አንዳንድ አሉባልተኞች ያላወቁት ነገር የተኩስ አቁም እርምጃ በክላሽና በመድፍ ብቻ አይደለም ከቃላት መወራወርም መቆጠብን ጭምር ያካተተ ነው" ብለዋል።
አክለውም መቼና ምን ማድረግ እንዳለብንም ጠንቅቀን እናውቃለን ፤ መከላከያ ሰራዊት ትዕዛዝ በሚደርሰው ጊዜ አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስድ የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
የሰራዊቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ፥ "ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር በሚያራግቡት ወሬ አንደናገርም" ያሉ ሲሆን ካወጣነው አዋጅ ጋር የሚጻረር ስራ ላለመስራት ስንል ብዙ ከመናገር ተቆጥበናል ሲሉ አስረድተዋል።
ሰራዊቱ የት ላይ ምን ማድረግ እንዳለበት እና ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ያውቃል ያሉት ኮ/ሌ ጌትነት አዳነ ፥ የተዛቡ መረጃዎች በተለቀቁ ቁጥር ምላሽ መስጠቱ አስፈላጊ አይደለም የሚል አቋም ተይዟል ብለዋል።
በመጨረሻም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ፥ "የተዛቡ መረጃዎች ቢሰራጩም በእነሱ ፕሮፓጋንዳ ልክ ወሬ ባለማብዛት ጨዋነታችንን ማሳየት ይጠበቅብናል ፤ ችግሮች የሚባባሱ ከሆነ ግን የመንግስትን ውሳኔ ተከትሎ የሚተላለፉ እርምጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ" ሲሉ አሳውቀዋል።

Video : በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች የተነሳውን ረብሻ ለመቆጣጠር ሠራዊቷን አሰማርታለች። ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በተነሳው ረብሻ ቢያንስ 45 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ወደ 800 የሚጠጉት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተገደሉት ሰዎች 19ኙ ከጉዋቴንግ እንዲሁም 26ቱ ከኩዋዙሉ-ናታል ናቸው። ዝርፊያውም ተባብሶ ቀጥሏል፤ ረጅም አመት በደ/አፍሪካ የኖሩ ኢትዮጵያውያን ለፍተው ጥረው ያፈሩት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : የደቡብ አፍሪካ ነውጠኞች በየአካባቢው የንግድ ተቋማት ላይ ከሚፈፅሙት ዝርፊያ በተጨማሪ ኮንቴነር ሰብረው እስከመዝረፍ ደርሰዋል።
በአገሪቱ አሁንም ረብሻ ባለባቸው ቦታዎች ነዋሪዎች በላባቸው ያፈሩትን ንብረት መዝረፍ እና ማውደም ቀጥሏል፤ የሚያቆመውም ጠፍቷል።
የደ/አፍሪካ 2,500 ሰራዊት ቢሰማራም ዝርፊያው ሊቆም አልቻለም።
የማይዘረፍ ነገር የለም ከልብስ እስከ መጠጥ፣ ከህፃናት ንፅህና መጠበቂያ እስከ ቤት ውስጥ ቁሳቁስ፣ ከወርቅ እስከ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች ብቻ ሁሉም የተገኘው ነው የሚዘረፈው።
አሁናዊ ሪፖርት እንደሚያሳየን ከሆነ ረብሻ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ የሞቱ ሰዎች ከ70 ተሻግረዋል፤ ከ1200 በላይ ሰዎች ታስረዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንግድ ስፍራዎች ተዘርፈዋል (የሀገራችን የኢትዮጵያ ዜጎች ጨምሮ)።
Video Credit : Intelligence Bureau SA

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ :
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተናጠል ተኩስ አቁሙ #የመጨረሻው ሰላማዊ ዕድል ነው አሉ።
ጠ/ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ ለህዝብ ባሰራጩት አጭር መግለጫ ነው።
በመግለጫቸው ላይ ፥ "ለትግራይ ሕዝብ ያለንን ሐሳብ ፤ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለንን ቦታ ለመጨረሻ ጊዜ አሳይተናል" ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ "ግጭት ላለማባባስ፣ ለሕዝቡ የእርሻ ወቅት ፋታ ለመስጠት እንዲሁም የርዳታ አቅርቦቱ ያለ ሰበብ እንዲከናወን ስንል በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አድርገናል" ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም ፤ "ሰላም የተወሰነ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ብናውቅም ይህ ግን የመጨረሻ ሰላማዊ ዕድል ነው" ሲሉ አሳውቀዋል።
እሳቸው "ጁንታ" እያሉ የሚጠሩት የህወሓት ቡድን "የሰላም መንገድ ሊዋጥለት አልቻለም ፤ አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም፤ ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል" ብለዋል።
የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል ሲሉም ገልጸዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ "ለሕዝባችን ስንል የከፈልነው ዋጋ ባልገባቸው ደካሞች ምክንያት ውጤት አላመጣም" ያሉ ሲሆን "ጁንታ" ሲሉ የሚጠሩት ህወሓት የኢትዮጵያ ህልውና ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ደግሞ እያስመሰከረ ነው ብለዋል።
ይሄን መላ ሕዝቡን በማስተባበር እንቀለብሰዋለን ሲሉም ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ፥ "በአንድ በኩል ሰብአዊ ርዳታ እንዲቀላጠፍ እየሠራን በሌላ በኩል የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተናበው የከፈቱብንን ጥቃት መክተን እንቀለብሰዋለን" ሲሉ በመግለጫቸው ላይ አስፍረዋል።
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

ቪድዮ : የደቡብ አፍሪካ ነውጠኞች በየአካባቢው የንግድ ተቋማት ላይ ከሚፈፅሙት ዝርፊያ በተጨማሪ ኮንቴነር ሰብረው እስከመዝረፍ ደርሰዋል። በአገሪቱ አሁንም ረብሻ ባለባቸው ቦታዎች ነዋሪዎች በላባቸው ያፈሩትን ንብረት መዝረፍ እና ማውደም ቀጥሏል፤ የሚያቆመውም ጠፍቷል። የደ/አፍሪካ 2,500 ሰራዊት ቢሰማራም ዝርፊያው ሊቆም አልቻለም። የማይዘረፍ ነገር የለም ከልብስ እስከ መጠጥ፣ ከህፃናት ንፅህና መጠበቂያ…
የAU በደቡብ አፍሪካ የተፈጠረውን ሁከት አወገዘ።
የአፍሪካ ህብረት (AU) የቀድሞውን ፕሬዝዳንት የጃኮብ ዙማን መታሰርን በመቃወም በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን ሁከት በጥብቅ አውግዟል።
ህብረቱ ፥ በደቡብ አፍሪካ የዜጎች ሞት፤ የህዝብ እንዲሁም የግለሰቦች ንብረት የዘረፉ ትዕይንቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በማውገዝ ሁከቱ እንዲቆም ጠይቋል፡፡
በደ/አፍሪካ የህግ የበላይነት እንዲከበር ፤ሰላም እና መረጋጋት በፍጥነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የተፈጠረውን ሁከት እና ብጥብጥ መፍታት አለመቻል በሀገር እንዲሁም በአህጉር ደረጃ “ከባድ ተጽኖዎች” እንደሚኖሩት ገልጿል።

ኢትዮጵያ በ5 ቀናት ከ11 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከሳዐዲ አረቢያ መልሳለች።
ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቿ የማስመለስ ዘመቻ እያደረገች መሆኑን ይታወቃል።
በ5 ቀናት ውስጥ 11,542 ዜጎቿን ከሳዐዲ አረቢያ አስወጥታ ወደሀገር መልሳለች።
ከተመለሱት ዜጎቻችን መካከል 729 ህፃናት ሲሆኑ 1,885ቱ ሴቶች ናቸው።
ዜጎቻችን የተመለሱበትን የጊዜ ቅድመ ተከተል እና ቁጥር ስንመልከት ፦
• ሃምሌ 2 ቀን 2013 ዓ/ም - 2,536 ዜጎች ተመልሰዋል (333 ሴቶች / 161 ህፃናት ይገኙበታል)
• ሃምሌ 3 ቀን 2013 ዓ/ም - 2,573 ዜጎች ተመልሰዋል (118 ሴቶች / 72 ህፃናት ይገኙበታል)
• ሃምሌ 4 ቀን 2013 ዓ/ም - 2,385 ዜጎች ተመልሰዋል (572 ሴቶች / 112 ህፃናት ይገኙበታል)
• ሃምሌ 5 ቀን 2013 ዓ/ም - 2,006 ዜጎች ተመልሰዋል (633 ሴቶች / 248 ህፃናት ይገኙበታል)
• ሃምሌ 6 ቀን 2013 ዓ/ም - 2,042 ዜጎች ተመልሰዋል (229 ሴቶች / 136 ህፃናት ይገኙበታል)