TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ግጭቱ ቆሟል-ማዕከላዊ ጎንደር‼️

ሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ጎንደር #ጭልጋ_ወረዳ እና አካባቢዉን ሲበጠብጥ የነበረዉ ግጭት እና ሁከት #መቆሙን የአካባቢዉ ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት እስታወቁ።

የአማራ መስተዳድር ባለሥልጣናት እንዳሉት የቅማንት ብሔረሰብ አባላት በሚኖሩባቸዉ አካባቢዎች በተቀሰቀሰዉ ግጭት በትንሽ ግምት ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። ሰባት መኖሪያ ቤቶች እና ወፍጮ ቤቶችም ተቃጥለዋል። የአካባቢዉ ነዋሪዎች ግን የሟቾቹን ቁጥር እና የጠፋዉን ንብረት መጠን ባለሥልጣናቱ ከገለፁት ከፍ ያደርጉታል።

የፌደራሉና የመከላከያ ጦር ባካባቢዉ ከሠፈረ ወዲሕ ግን በአብዛኞቹ አካባቢዎች ግጭቱ መቆሙን የአማራ መስተዳድር የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ ብርጌድየር ጄኔራል #አሳምነዉ_ፅጌ አስታዉቀዋል። ማዕከላዊ ጎንደር የሚኖሩት የቅማንት ብሔረሰብ አባላት የራሳቸዉ መስተዳድር እንዲኖራቸዉ ጥያቄ ካነሱ ካለፈዉ ዓመት ወዲሕ አባካባቢዉ ጠብ እና ግጭት ተለይቶት አያዉቅም።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጭልጋ

"ችግሩ የተፈጠረው ቅማንት ኮሚቴውን መያዝ መቻል አለብን፤ ወንጀለኛ ነው ብሎ ነው እያሰማራ ያለው ይሄን ፋኖ፤ ወደ 8 -9 ሰው ሞቶብናል፤ 7-8 ሰው ቁስለኛ አለ።...ፋኖ የሚባለው እራሱን የቻለ ልብስ ነው ያለው። ፋኖ ነው የሚለው..." የቅማንት ማህበረሰብ አባል
.
.
"ፋኖ የሚባል ጦር የለም! እውነታው ይሄ ነው" የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ
.
.
"በክልሉ ውስጥ በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ አጀንዳ ይዞ የሚሰራ ኃይል አለ። ይሄ ኃይል አሁን ፅንፈኛ የቅማንት ኮሚቴ አባላት ክልሉን ማተራመስ እንዲችሉ ማስታጠቅ ነው አንደኛው፤ ባለፉት አመታት እኔም ወደዚህ ቢሮ ከመምጣቴ በፊት ጄነራል አሳምነው በነበረ ጊዜም ከዚያም በፊት ሌሎች ቢሮ ኃላፊዎች በነበሩ ጊዜ ግጭት ነበር። ስለዚህ እዚህ ቢሮ ያለ ሰው በሙሉ ለቅማንት ፅንፈኛ ኮሚቴ ጠላት ነው። ጄነራል አሳምነው ነበር ጠላት ነው፤ ከዚያ በፊት አቶ ደሴ አሰሜ ነበር ጠላት ነው፤ ከዚያ በፊት አቶ እዘዝ ዋሴ ነበር ጠላት ነው፤ አሁን ደግሞ እኔ መጣሁ ጠላት ነኝ፤ ስለዚህ አጀንዳ መቅርፅ ነው። እዚህ ቢሮ ላይ የምንመደብ ሰዎች ህግና ስርዓት ለማስከበር በምናደርገው እንቅስቃሴ ስም ማጥፋት ነው፤ ስም ማብጠልጠል ነው።" የአማራ ክልል ሰላምና ግንባታ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጭልጋ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከጭልጋ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ችግር እየተሻሻለ መምጣቱን አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ ከጭልጋ እና አካባቢው አስር ቀበሌ ከሃይማኖት አባቶች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ከወረዳና ቀበሌ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉ ሪፖርት ተደርጓል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት አመራር ሌ/ጀ ይመር መኮነን ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞንን የሽብርተኞች አደባባይ በማድረግ የሀገርን ሰላም ለማሳጣት የሚንቀሳቀሱ የፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ እተወሰደ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም ፥ በኮማንድ ፖስቱ እንዲሁም በህብረተሰቡ የጠነከረ ቅንጅት በየጊዜው መሻሻሎች እየተመዘገቡ እንደመጡም ገልፀዋል።

የ33ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ደስታ ተመስገን በበኩላቸው የተመዘገበውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ሰላም በቀጣይነት ለማረጋገጥ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ይበልጥ ተባብረው መስራት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ለበጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ መዘጋጀታቸውን እና በህዝብ ውስጥ ሰላማዊ ሰው በመምሰል ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ለግጭት የሚዳርጉ ወንጀለኞችን በመጠቆም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia