TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Live stream started
#LIVE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከላይ ባለው Voice Chat 'Join' በማለት በቀጥታ ማድመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
#Live

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡ የምርጫ ክልሎችን ውጤት እያሳወቀ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከላይ በ Voice Chat አድምጡ።

@tikvahethiopia
#Update

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከ942 የምርጫ ክልሎች መካከል እስካሁን የ618ቱ ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን አስታውቀዋል።

160 ምርጫ ክልሎች ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች የቅሬታና አቤቱታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

ከአቤቱታዎቹ ከፊሉ በተደራጀ መልኩ ስላልቀረቡ ተስተካክሎ እንዲቀርብ ለፓርቲዎች ጥሪ ተደርጓል ብለዋል።

@tikvahethiopia
Live stream finished (1 hour)
#Tigray

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በትላንትናው ዕለት የተናጠል በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ካወጀ በኃላ በተለያዩ ሀገራት የተሰጡ አስተያየቶች።

- UNICEF ያሰማው ክስ።

- በኔትዎርክ መቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወላጆች እና ትግራይ ክልል ውስጥ ቤተስብ ያላቸው ዜጎች ጭንቀት።

-የአሜሪካ ትግራይን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝ መግለጿ።

- የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ስለ ትግራይ ጉዳይ የሰጡት አስተያየት።

- የህወሓት ኃይሎች ሽረን መያዛቸው፣ የኤርትራ ሰራዊት ከሽረ መውጣቱ።

- የህወሓት ኃይሎች በሰጧቸው አስተያየቶች ላይ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ያወጣው ጠንከር ያለመግለጫ።

- የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ስለቀረበለት ጥሪ።

.
.
.
ሌሎችም ጉዳዮች!

(ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የተዘጋጁ)

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-06-29-2
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,550
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 63
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 685

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 276,037 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,320 ህይወታቸው ሲያልፍ 260,302 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 2,010,091 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#ZamZamBank

ዘምዘም ባንክ ከተቋቋመ 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ወስጥ ወደ 3 ቅርንጫፎች አደገ።

ባንኩ ሁለተኛና ሶስተኛ ቅርንጫፎቹን በዛሬው ዕለት ስራ አስጀምሯል።

የዘምዘም ባንክ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቅርንጫፎች በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ የተከፈቱ ሲሆን ቅርጫፎቹ ሃጅ ቱሬ እና ሰፍዋ ይሰኛሉ ( Safwa Branch @ Dubai Tera Area , Haji Ture Branch @ Merab Hotel area )

በመርካቶ የተከፈቱት የዘምዘም ቅርንጫፎች ለንግዱ ማህበረሰብ የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሊካ በድሪን ዘምዘም ባንክ የሸሪዓ ህግን ተከትሎ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመላ አገሪቱ ውስጥ አገልገሎት ለመስጠት እየሰራ ነው ብለዋል።

Photo Credit : Zamzam Bank

@tikvahethiopia
#Update

የህወሓት ኃይል የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተናጠል ተከሱስ አቁም አዋጅ ማወጁን እንደማይቀበል ገልጿል፥ ውሳኔውን "ቀልድ" ነው ሲል አጣጥሎታል።

የህወሓት የታጠቀው ኃይል ይህን ያሳወቀው በአቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከአሶሼትድ ፕሬስ /AP/ (ናይሮቢ ከሚገኘው) ጋር ባደረጉት ቆይታ የፌዴራል መንግስቱን የተናጠል ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተውን የተኩስ አቁም አዋጅ አጣጥለውታል።

አቶ ጌታቸው ለAP ተዋጊዎቻችን "እያንዳንዱን ካሬ ኢንች ነፃ ያወጣሉ" ሲሉም ተናግረዋል። ትላንት ለሮይተርስ በሰጡት ቃል "የጠላትን የመዋጋት አቅም ለማዳከም ወደ ኤትራም ሆነ አማራ ክልል መግባት ካስፈለገ እንገባለን" ሲሉ መዛታቸው አይዘነጋም።

ይህ አስተያየታቸው ግጭቱ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተናጠል ተቁስ አቁም ካወጀ በኃላ የትግራይ ከተሞች ስላሉበት ሁኔታ እስካሁን ያለው ነገር የለም፤ ነገር ግን ከዚህ ቀደም በፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ስር የነበሩ ከተሞች በህወሓት ኃይሎች ስር ገብተዋል ፥ የፌዴራል ሰራዊቱም ከተሞችን እየለቀቀ ወደኃላ መመለሱ ተነግሯል።

ትግራይ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ቴሌኮሚኒኬሽን በመቋረጡ መሬት ላይ ያለውን ሁነት ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል።

@tikvahethiopia
#Update

የአሜሪካ መንግስት ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት ማወጁ ግጭት እና የሚፈፀሙ ጭካኔዎችን ለማስቆም፣ ያልተገደበ ሰብአዊ ርዳታን በማድረስ በኩል በመሬት ላይ ለውጥ ካመጣ አዎንታዊ እርምጃ ሊሆን ይችላል ብሏል።

ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተልን ነው ያለው የአሜሪካ መንግስት፤ ግጭቱን ለማስቆም፣ ትግራይ ክልልን ለማረጋጋት እንዲሁም የኢትዮጵያን መንግስት አንድነት፣ ሉዓላዊነቱን እና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት የሚጠብቅ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ አውድ እንዲፈጥር ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ፣ ላልተወሰነና በድርድር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያድረጉ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት፥ ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግን በጥብቅ እንዲያከብሩ ፣ ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲያደርጉ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎችን የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትን ገለልተኛ መንገድ እንዲያመቻቹ ጠይቋል።

የአሜሪካ መንግስት በመግለጫው ፥ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አስከፊ የሆነውን የሰብዓዊ ሁኔታ መፍታት ነው ብሏል።

ከዚህ ቀደም የረሀብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል የተባሉ 900,000 ሰዎች ጨምሮ ለሌሎችም ሕይወት አድን የምግብ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከትግራይ ባለሥልጣናት፣ ከተባበሩት መንግስታት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ለመስራት ዝግጁ ናት ብሏል የሀገሪቱ መንግስት በመግለጫው።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በትግራይ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመልሱ እና ሰብአዊ ድርጅት ሠራተኞች ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ ያልተገደበ የመንቀሳቀስ ነፃነትን እንዲፈቅዱ እንጠይቃለን ብሏል።

@tikvahethiopia
#Update

ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ የማስወጣቱን ዘመቻ አጠናክራለች።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ በትናትናው ዕለት 1 ሺ 657 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
#ጭልጋ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከጭልጋ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ችግር እየተሻሻለ መምጣቱን አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ ከጭልጋ እና አካባቢው አስር ቀበሌ ከሃይማኖት አባቶች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ከወረዳና ቀበሌ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉ ሪፖርት ተደርጓል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት አመራር ሌ/ጀ ይመር መኮነን ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞንን የሽብርተኞች አደባባይ በማድረግ የሀገርን ሰላም ለማሳጣት የሚንቀሳቀሱ የፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ እተወሰደ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም ፥ በኮማንድ ፖስቱ እንዲሁም በህብረተሰቡ የጠነከረ ቅንጅት በየጊዜው መሻሻሎች እየተመዘገቡ እንደመጡም ገልፀዋል።

የ33ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ደስታ ተመስገን በበኩላቸው የተመዘገበውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ሰላም በቀጣይነት ለማረጋገጥ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ይበልጥ ተባብረው መስራት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ለበጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ መዘጋጀታቸውን እና በህዝብ ውስጥ ሰላማዊ ሰው በመምሰል ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ለግጭት የሚዳርጉ ወንጀለኞችን በመጠቆም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

@tikvahethiopia
#Update

“የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ሰኔ 21/2021 ዓ.ም. የወሰደው ‘በሰብዓዊ ምክንያት ተኩስ የማቆም አዋጅ’ ትግራይ ውስጥ ላለውን ግጭት መፍትኄ ለማግኘት ትክክለኛ እርምጃ በመሆኑ እንደግፈዋለን” ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲገኝ መንገድ ለመጥረግ እንዲቻልም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ የሆነ ቋሚ ተኩስ ማቆም ላይ እንዲደረስ እንዲሠሩ የኅብረቱ ሊቀ መንበር ጠይቀዋል።

ለዚህም ሁሉም ዓይነት የግጭት ሁኔታዎች እንዲቆሙ ፤ በዓለም አቀፍ ህግ መሠረት ሲቪሎችን ከአደጋ ለመጠበቅ እና ክልሉ ውስጥ ለተጎዱት ሁሉ እጅግ አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ የሰብዓዊ እርዳታ ተዋናዮች ደኅንነቱ የተረጋገጠ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁሉም ወገኖች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አድርገዋል።

ለትግራይ ክልል ግጭት የፖለቲካ መፍትኄ እንዲፈለግም ሊቀ መንበሩ በተጨማሪ መጠየቃቸውንና በሃገሪቱ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥረቶች የአፍሪካ ኅብረት ድጋፉን ለመስጠት ያለውን ያልተቋረጠ ዝግጁነት ማሳወቃቸውን ከፅ/ ቤታቸው የወጣው መግለጫ ይጠቁማል። (VOA)

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የፌዴራሉ መንግስት ካወጀው የተናጠል ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም ጋር ተያይዞ የሚወጡት መግለጫዎች ቀጥለዋል።

በተለያዩ ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እና ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉት ፦
- ዴቪድ ሺና፣
- ቪኪ ሐድልስተን፣
- ፓትሪሺያ ሃስላች፣
- ኦውሪሊያ ብራለዚል
- ቲቦር ናዥ የተኩስ አቁም ውሳኔውን ተከትሎ መግለጫ አውጥተዋል።

በትግራይ ክልል የነበረውን ሁኔታ በቅርበት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው የፌደራሉ መንግሥት የሰላም አማራጭ ማቅረቡ "ትልቅ እፎይታን ፈጥሮልናል" ብለዋል።

አምባሳደሮቹ ይህ መልካም አጋጣሚ መታለፍ የለበትም ያሉ ሲሆን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ በመንግሥት የቀረበውን ጥሪ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች በበጎ አድራጊ ተቋማት ተደራሽ እንዲሆኑ፣ በትግራይ ያሉ የውጭ ኃይሎች ከግጭቱ ክልል ለቀው እንዲወጡ እና የግጭቱ ተሳታፊዎች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም በትግራይ ቀጣይ ሁኔታ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ውይይትና ድርድር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቀረባቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ በመከላከያ በኩል ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ናቸው መግለጫውን የሰጡት።

ምን አሉ ?

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ለቆ በመውጣቱን ገልፀዋል። "እንደምንወጣ ከሳምንታት በፊት የነገርናቸው የውጭ ተቋማት ነበሩ ብለዋል።

- በሁሉም አቅጣጫ ማለትም በሱዳን ፣ ኤርትራ አፋር እና አማራ ወሰን ዝግ መሆኑን ገልፀዋል።

- የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል ዙሪያ ለሚኖር ችግር ተጠያቂ እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡

- ዓለም አቀፍ ተቋማት ፥ “ከዚህ በኋላ ዕርዳታ ደረሰ አልደረሰ ብለው የፌዴራል መንግስትን ሊጠይቁ” እንደማይገባ ገልፀዋል፤ የትግራይ ክልልን በተመለከተ ሙሉ ኃላፊነቱን አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው "ህወሃት" እንደሚወሰድ አሳውቀዋል።

- በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረጋት ገልጸዋል፤ በልማት ሂደቱ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ተናግረዋል፡፡

- ሕወሃት የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ እንደጣለ ተናግረዋል፤ ሱዳን የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር ጥሳ እንድትገባ አጋልጦ እንደነበርም ገልፀዋል።

- 8 ወራት ብቻ የጦር ወጪን ሳይጨምር የፌደራሉ መንግሥት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማደረጉን ገልጸዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Update-06-30

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ በመቋጠረጡ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታም በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ የቲክቫህ አባል፥ ስላልጃቸው ደህንነት ማወቅ ባለመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እሳቸውን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ተቋማቱን አምነው ጥሪ ሲቀርብ ልጃቸውን እንደላኩ የገለፁት አባላችን ተቋማቱን የሚይመራው አካል እስካሁን ግንፅ ማብራሪያ አለመስጠቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው አስረድትዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ ሌላ እናት በላኩት መልዕክት ልጃቸውን ባለፉት ቀናት ሊያገኙት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በፌዴራል እና መከላከያ ጥበቃ ስር ነበር እኛም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው በሚል ነው ልጆቻችን አምንነ የላክነው አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም ብለዋል።

የፌዴራል ጠባቂዎች ቀድመው እንደሚወጡ ከታወቀ ለምን ልጆቻችን እንዲመለሱ አልተደረግም ሲሉም ጠይቀዋል ? ቤተሰብ በእጅጉ ተጨንቋል አስቸኳይ ማብራሪያ እንፈልጋለን ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላጆች እያቀረቡት ላለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፤እስካሁን ግን ምላሽ አላገኘም።

በሌላ በኩል የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው፥ በግቢው የቀሩ ተማሪዎች እንዳሉ የራያ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።

በትግራይ በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት መሬት ላይ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

@tikvahethiopia