TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ " በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል ይታወቅ " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለከልም " ይሄን አልሰማንም " ያሉ ሰዎች የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ወደ ሀገር እያመጡ ይገኛሉ ተብሏል። ይህ የተሰማው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች…
#AddisAbaba

በህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ፦
* እንዳይቸገሩ ፣
* መንገድ ላይ ሰልፍ ተሰልፈውም ጊዜያቸው እንዳይጠፋ ፣
* ባሰቡበት ሰዓት በህዝብ ትራንስፖርት ያሰቡበት ቦታ እንዲደርሱ በተለየ ሁኔታ ለተወሰነ ሰዓት የግል ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ #ለመገደብ እየተሰራ ይገኛል። ይህ በቅርብ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

ዓለሙ ስሜ (ዶክተር) ፦

" በአዲስ አበባ በትራንስፖርት የሚሄደው ህዝብ አገልግሎቱን በአግባቡ የማያገኝበት ፣ ባሰበበት ሰዓት ተነስቶ ባሰበው ሰዓት የፈለገው ቦታ እንዳይደርስ የሚያደርጉ ሶስት ምክንያቶች አሉ።

1ኛ. የህዝብ ትራንስፖርት የተሽከርካሪ እጥረት ነው።

2ኛ. የመንገድ መዘጋጋት ነው።

3ኛ. የስምሪት እና የተሽከርካሪ ማናጅመት አለመዘመን ነው።

በነዚህ ሶስት ጉዳዮች እየሰራን ነው።

የተሽከርካሪ ቁጥር ለመጨመር በየዓመቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚጭኑ ማስ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እየገዛ ወደ አገልግሎት እያስገባ ነው። ዘንድሮም እየተሰራ ነው። በዓለም ባንክ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተገዝተው ለአዲስ አበባ ከተማ እንዲሰጡ እየተሰራ ነው።

የመንገድ መዘጋትን በተመለከተ መንገዶቻችን የተወሰኑ ናቸው። ሀገሪቱ ካላት ተሽከርካሪ በአብዛኛው አዲስ አበባ ውስጥ ነው ያሉት። ይሄን ችግር ለመቅረፍ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

አንደኛው ለህዝብ ጭነት ተሽከርካሪዎች የተለየ መንገድ ፣የተለየ መስመር ማበጀት ነው እሱም ተበጅቶ እየተሰራ ነው ያለው። ግን በቂ አይደለም።

ሁለተኛው በተለይ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት #የተወሰኑ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን እንዳይንቀሳቀሱ የመገደብና ህዝብን የሚጭኑ አውቶብስ ቶሎ ቶሎ እንዲመላለስ ማድረግ ነው። ከተሽከርካሪ እጥረት መንገድ ላይ የሚቆመውን ህዝብ ባለው ተሽከርካሪ ቶሎ ለመጫን መንገድ ክፍት የሚሆንበት #ሰዓቶችን መርጠን ጥናቱ አልቋል ወደ ስራ በቅርቡ ይገባል።

ስለዚህ በስራ መውጫና መግቢያ ሰዓት የግል መኪና ተጠቃሚዎች የሚገደቡበት ሁኔታ ይፈጠራል። ይሄም የግል መኪና ተጠቃሚዎች ወደህዝብ የትራንስፖርት አማራጭ እንዲገቡ የማስገደድ ሁኔታ ይመጣል። ይህ ለህዝብ አውቶብስ መንገድ ይከፈታል፣ ነዳጅ ይቆጠባል፣ የአየር ብክለትን ይቀንሳልም። ይህን አሰራር በቅርብ ተግባራዊ እናደርጋለን።

የአውቶብሶች መነሻ እና መድረሻ ሰዓታቸው እንዲታወቅ በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ስራ ከዓለም ባንክ ጋር እየተሰራ ነው። ይህም ስራ ካለቀ ከዚህ ጋር ያሉት ችግሮች ይፈታሉ። "

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia