TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 በነበረው መግለጫ የነጌሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) በክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮት እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ መግለጫ እየሰጡ የሚገኙት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሚደቅሳ በምርጫ ክልሉ ከቦርዱ እውቅና ውጪ ከመቶ በላይ በሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ መደረጉን ገልጸዋል።

ምርጫ ስርዓቱ የህግ ውጤት የሚኖረው እንደማይሆን /ውድቅ መደረጉን አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ብርቱካን የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ችላ ብለው ድምፅ እንዲሰጥ ያደረጉ አካላት በህግ ይጠየቃሉ ብለዋል፤ ጉዳዩንም ለፌዴራል ፖሊስ አሳውቀናል ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
Live stream finished (54 minutes)
#Update

"በደሴ 10 በሚሆኑ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ተሞልተው ተገኙ" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

በ10ሩ የምርጫ ጣቢያዎች የተፈጠረውን ጉዳይም ዛሬ በነበራቸው መግለጫ አስረድተዋል።

በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የውጤት አገላለፅ እንዲሁም የውጤት አመዘጋገብ በትክክለኛው መንገድ ስለመፈፁ የሚረጋገጥበት የራሱ ደረጃ አለው ይህም በስልጣና ላይ ተሰጥቷል ብለዋል።

ከእንዚህ ደረጃዎች/ሂደቶች መካከል ፦
- የመጀመሪያው በዚያ ጣቢያ ስንት ሰው ነው የሚመዘገበው ?
- በዕለቱ መጥቶ መዝገብ ላይ ፈርሞ ድምፅ የሰጡ ብዛት ስንት ናቸው ? ፊርማቸው ተቆጥሮ መመዝገብ አለበት።
- የመጡት ሰዎች ተመዝግበዋል ከተባሉት ሰዎች ቁጥራቸው መበላለጥ ስለሌለበት ይህም ይረጋገጣል።
- የደረሰው የድምፅ መስጫ ወረቀት ብዛት ስንት ነው ?
- ሳጥን ውስጥ የተገኘው ምን ያህል ነው ?
- የተበላሸ የድምፅ መስጫ ወረቀት ስንት ነው ? የሚሉት ይገኙበታል።

ደሴ የተገኙት 10 ምርጫ ጣቢያዎች ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጡ አካሄዶችን ሳይፈፅሙ ፣ ሂሳቡንም በትክክል ሳይሰሩ በመላካቸው በምርጫ ክልል ደረጃ እንደገና መታየት ስላለበት / ድምፅ ቆጠራው መደገም ስላለበት የምርጫ ክልሉ ለጊዜው ኳራንታይን አድርጎ አስቀምጦታል።

ይህ ሁኔታ ነው የማይሆን ትርጉም ተሰጥቶት #ሀሰተኛ_መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት የሆነው ሲሉ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :

• የላብራቶሪ ምርመራ - 4,525
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 99
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ 642

አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 275,601 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,296 ህይወታቸው ሲያልፍ 257,429 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,987,927 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#ምርጫ2013

በምርጫ ወቅት የምንጠቀማቸው ቃላቶች ፦

በአሁን ወቅት በተደጋጋሚ ለሚነሱት የምርጫ ቃላቶች ማብራሪያ እንዲሰጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስን ጋብዘናል።

ማብራሪያ የተሰጠባቸው ቃላቶች፦

- ኳራንታይን
- ውጤት ማጣራትና ማረጋገጥ

በተጨማሪም ወ/ሪት ሶልያናን ስለ ቅሬታ አቀራረብ እና ውጤት ስረዛ ጥያቄ አቅርበንላቸዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና የሰጡትን ምላሽ ከላይ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

#TikvahFamily #ምርጫ2013

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ኳራንቲን የተደረጉ /በምርመራ ላይ ያሉ ጣቢያዎች ስንት ናቸው ?

በአዲስ አበባ የመጫረሻ #ኳራንቲን ፣ ምንም የማይደረግበት ወይም ደግሞ ወደውጤት ቋት ውስጥ የማይገባ በሚል የተያዙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አሳውቀዋል።

አንደኛው በምርጫ ክልል 24 ያለ ሲሆን ሌላኛው በንፋስ ስልክ ያለ ነው።

ከዛ ውጭ እንደገና በመቁጠር እና ሰነዶችን እንደገና በማየት የሚስተካከሉ ሊኖሩ ይችላሉ።

NB : በምርጫው ሂደት "ኳራንቲን ማድረግ" ማለት ከዋናዎቹ ውጤቶች ጋር ሳይቀላቀል ማግለል ወይም ደግሞ መለየት እና በልዩ ሁኔታ ማጣራት ማለት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ያሶን ጨምሮ 5 እስረኞች ከእስር ተፈተዋል። በእስር ላይ ከነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) አመራር እና አባላት መካከል ያሶ ከበበውን ጨምሮ 5 እስረኞች ትላንት ተፈተዋል። በእነ አቶ ያሶ መዝገብ ስር በተከሰሱት ስድስት ተከሳሾች ላይ የቀረበባቸው ማስረጃ እውነት መሆኑም ማረጋገጥ ባለመቻሉ ፍርድ ቤት ስድስቱም ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን የተከሳሽ ጠበቆች ለኦ ኤም ኤን ተናግረዋል። …
"በነፃ አልተለቀቅንም"

ከትላት በስቲያ ከእስር የተፈቱ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፖለቲካ መኮንን አቶ ያሶ ከበበው ስለአፈታታቸው እንዲሁም ስለእስራቸው ትላንት ምሽት አየር ላይ በዋለው የቪኦኤ አፋን ኦሮሞ የሬድዮ ስርጭት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።

ከ30 የጊዜ ቀጠሮ በኃላ ፍርድ ቤት የተመላለሱት እነ አቶ ያሶ በነፃ እንዳልተለቀቁ እና ታስረው እንደወጡ ወቀሳ አሰምተዋል።

አቶ ያሶ፥ "ፍ/ቤቱ ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ነፃ ነህ አለኝ እንጂ አንተ ነፃ ሰው ነህ አላለኝም።

አንድ ሰው ሁለት አመት ታስሮ ነፃ ነህ ተብሎ ሲፈታ መደሰት ይለበትም፤ ምክንያቱም ሁለት አመት ታስሮ ነው የወጣው መባል አለበት።

ፍርድ ቤት በነፃ ነው ያሰናበትኩት ማለት የለበትም ፤ እኔ ሁለት ዓመት ታስሬ ነው የወጣሁት ነገር ግን ከተጠረጠርኩበት ወንጀል ነፃ ነህ የሚል ሃሳብ ነው ከተከሳሾቼ የተረዳሁት" ብለዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስለእነ አቶ ያሶ ተይዘው ስለቆዩበት ጊዜ በሰጠው አስተያየት በክርክር ሂደት በእስር ቤት ቆይተው ፍርድ ቤት በመመላለስ የባከነ ጊዞ ሳይሆን የፍትህ ማስገኛ ጊዜ ነው ሲል ገልጿል።

አቶ ያሶ መንግስት የህግ የበላይነት አስከብራለሁ እያለ ያለ ሰዎችን ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይታሰራሉ ያሉ ሲሆን አጋጥሟቸው የነበረውን ችግር ተናግረዋል፦

"ለምሳሌ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይል ቁጥጥር ስር ሲውል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሆን አለበት። ነገር ግን እኔ ከመንገድ ላይ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነው የተያዝኩት፤ ይህ ህገወጥ ነው። በተጨማሪ ከታሰርን በኃላ አራዳ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት ሰጥቶን የዋስትና ማስከበሪያ ከተከፈለ በኃላ አሁንም ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደጎን በመተው ለአንድ አመት ከስምንት ወር አሰረን"

ያንብቡ : telegra.ph/YASO-KABABAW-06-25

@tikvahethiopia
#AtoAbdiRagassa

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር አቶ አብዲ ረጋሳ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ወደማይታወቅ ቦታ እንደተወሰዱ ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ አሳወቁ።

አቶ አብዲ ከአንድ ዓመት በላይ ታስረው የቆዩ ሲሆን ፥ከተወነጀሉበት ክስ ነፃ ተብለው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወስኖላቸው ነበር።

ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ከዳለቴ እስር ቤት ትላንት የተለቀቁት አቶ አብዲ፥ አንድ ኪሎሜትር ሳይርቁ አብረዋቸው ከነበሩት ጓደኛቸው እና የኦነግ አመራር ጀቤሳ ገቢሳ ጋር በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ተወስደዋል።

በኃላም ፀጥታ ኃይሎች አቶ ጀቤሳ ገቢሳን የለቀቁ ሲሆን ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸውን አቶ አብዲ ረጋሳን ግን ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል።

አቶ አብዲ የት እንደታሰሩ አይታወቅም።

ጠበቃቸው ስለጉዳዩ በሰጡት አስተያየት ይህን መሰሉ ከህግ ያፈነገጠ ድርጊት ለሀገርም፣ ለመንግስትም ሆነ ለህዝብ የማይበጅ አደገኛ ድርጊት ነው ብለውታል ለኦኤምኤን በሰጡት ቃል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ነገ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ባለፈው ሳምንት ለ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሰኞ በሚዘጉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምትክ ቅዳሜ የሥራ ቀን እንደሚሆን አሳውቀው እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም #ነገ ሰኔ 19/2013 ሁሉም መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
ኢንጂነር እምብዛ ታደሰ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አሳወቀ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በኢንጂነር እምብዛ ታደሰና ባለፋት ተከታታይ ወራት በክልሉ በንፁሐን አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን በጥብቅ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

በእንጅነር እምብዛ ታደሰ አሰቃቂ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘንም ገልጿል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ በግምት ከቀኑ ሰባት ሰዓት በኃላ ወጣት እንጅነር እምብዛ ታደሰ ከቢሮ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ የአየር ማረፊያ ለመጓዝ በተዘጋጀበት፣ ለግዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አፋኞች በሐይል ተወስዶ ደብዛው ጠፍቶ ነበር።

በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሐይሎች በተከናወነ አሰሳ ኢንጂነር እምብዛ በጨካኝ የከተማ ሽብር ተልእኮ አስፈፃሚ ወንጀለኞች በዓይደር ልዩ ስሙ " ማረሚያ ቤት" በተባለ ስፍራ ተገድሎ ለጅቦች ከተጣለበት ስፍራ ትላንት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ቁርጥራጭ የሰውነት አካላቱን በመለየት በተጨማሪ ምርመራም፤ በጭካኔ መገደሉን ማረጋገጥ መቻሉን ለኢዜአ አሳውቋል።

* የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
"...የመኪና አሽከርካሪዎች በቀንም ሆነ በሌሊት ሲያሽከርክሩ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል" -

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ስራ ከጀመረ ጀምሮ አንስቶ ከ550 በላይ ጊዜ የመኪና አሽከርካሪዎች በንብረት ላይ ጉዳት እንዳደረሱበት አስታወቀ።

ዛሬ ዑራኤል አካባቢ ቪትዝ ተሽከርካሪ የባቡሩን አጥር ሰብሮ መግባቱን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ ገልፀዋል።

ይህን ተከትሎም ለሶስት ሰዓት ያህል የባቡር ትራንስፖርት አግልግሎት ተቋርጦ ነበር።

ያደረሰው ጉዳትም ከሁለት ቀን በኃላ ግምቱ እንደሚታውቅ ጠቅሰው የባቡር ትራንስፖርት አግልግሎቱ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

በተደጋጋሚ ከጦር ሀይሎች እስከ አያት በሚደርሰው የባቡር መስመር ላይ የመኪና አሽከርካሪዎች የባቡሩን አጥር ሰብረው በመግባት የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ነገር ግን እስካሁን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ነው ያሉት፡፡

የመኪና አሽከርካሪዎች በቀንም ሆነ በሌሊት ሲያሽከርክሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ስራ አስኪያጁ አሳስበዋል።

መረጃው የፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ነው።

Photo Credit : ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር። የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።…
#ሳዑዲአረቢያ

በእስር ላይ ያሉ ዜጎችን ለመርዳት ከትላንት በስቲያ በይፋ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

በማህበራዊ ሚዳያ ላይ የቀረበውን #የእንተጋገዝ_ጥሪ ተከትሎ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ክፍተኛ ርብርብር እያደረጉ ይገኛሉ።

ወገኑን ወዳድ የሆነው የኢትዮጵያዊ ችግር ላይ ለሚገኙት ዜጎች ደከመኝ ፤ ሰለቸኝ ሳይል የአቅሙን ሁሉ እያበረከተ ነው።

እየተደረገ ካለው የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪም ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ዜጎች በጉልበት ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በጅዳና አካባቢው ያለው ኢትዮጵያዊ በእስር ቤት ውስጥ ያሉና የተቸገሩ ወገኖቹን ለማገዛ ከድሮ በበለጠ የአንድነት ስሜት እየተረባረበ ይገኛል።

እየተደረገ ያለው ድጋፍ ፦
- ለህፃናት የሚሆን ወተት
- የህፃናት ዳይፐር /ሃፋዛ/
- ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎች የሚሆኑ ደረቅ ምግቦች - ለሴቶች እና ለሕፃናት የሚሆኑ የመፀዳጃ ቁሳቁሶች በተለይ ዋይፕና ሞዴስ
- የሚጠጣ ውሃ
- ፍራሽ የመሳሰሉት ነው።

NB : የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ\ቤት ጅዳ፥ የጄዳና የአካባቢው ማህበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) ጽ / ቤት ጥሬ የገንዘብ ዕርዳታ ለዚሁ አላማ አይቀበልም።

@tikvahethiopia
የ3 ዓመት ከ2 ወር ህፃን ያገቱት ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

በእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሰኔ 15/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ገደማ የ3 ዓመት ከ2 ወር ሕጻን በማገት ተሰውረዋል፡፡

በዕለቱ ከቀኑ 11፡30 ገደማ ላይ የሕጻኑ ወላጆች በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ 8ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

ሪፖርት በሚያደርጉበት ጊዜ ከአጋቾች በኩል ለሕጻኑ ወላጆች ስልክ ተደውሎ 300 ሺህ ብር መክፈል ከቻሉ ሕጻኑ እንደሚመለስላቸው ይነግሯቸዋል፡፡

ፖሊስ ሕጻን በማገት ድርጊት የተሳተፉት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥ ሥር ለማዋል ስምሪት ያደርጋል ፤ በማኅበረሰቡ ጥቆማ አዴትና ሰባታሚት ተብለው ወደሚጠሩ አካባቢዎች ልዩ ስምሪት በማድረግ ትናንት ከቀኑ 9፡00 ላይ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋል ችሏል።

ከዋናው ተጠርጣሪ ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሌሎች ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ፖሊስ እንደገለፀው ፥ ተጠርጣሪው ከማቀድና ሁኔታዎችን አቀነባብሮ ድርጊቶችን ስለመፈጸሙ እንዲሁም ሕጻኑን አግቶ እንደተሰወረ አምኗል፡፡ ስለፈጸማቸው ድርጊቶች ሁሉ ለፖሊስ ቃል ሰጥቷል።

ተጠርጣሪው ዛሬ ጠዋት 4፡00 ላይ ፖሊሶችን ሕጻኑ ወደተደበቀበት ይልማና ዴንሳ መርቶ ወስዷል፤ በዚህም መሰረት 5፡15 ላይ ሕጻኑን ማግኘት ተችሏል።

የለበሰው ልብስ ከመቀየሩ ውጪ ሕጻኑ ምንም ጉዳት አልደረሰበትም።

የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመ በአራተኛው ቀን ሕጻኑ ለወላጆቹ እንዲመለስ ተደርጓል።

ምንጭ፦ #አሚኮ

@tikvahethiopia