#ደቡብ_ሱዳን
የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር ሀገራቸው የናይል ወንዝን በመጠቀም ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት ዕቅድ ማዘጋጀቷን አሳወቁ።
ም/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴንግ ዳው ዴንግ ማሌክ ለናሽናል ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ ከዕርስ በርስ ጦርንት የተላቀቀችው ደቡብ ሱዳን ወደ ኢንዱስትሪ መር የገበያ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ሀይል ማመንጫ ግድብ ለመገንባት የሚስችል ገንዘብ አላት ብለዋል።
ፕሮጀክቱ መንግስት ከነዳጅ ሽያጭ በሚያገኘው ገቢ ለመገንባት ዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ተገልጿል።
ደ/ሱዳን ርካሽ፣ ታዳሽና በሀገሪቱ በየጊዜው የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ መከላከል የሚያስችል የግዙፍ ግድብ ግንባታን በይፋ ለማስጀመር ዕቅድ መያዟን ተናግረዋል፡፡
ሀገሪቱ በየወቅቱ በሚፈጠር የጎርፍ አደጋ፣ በሀይል እጥረት፣ የውሃ እጥረትና በደካማ የመሰረተ-ልማት ችግር እንደምትሰቃይ ጠቅሰዋል።
ወደ ኢንዱስትሪ መሸጋገር የሚቻለው በቅድሚያ የሀይል አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማምረት ሲቻል እንደሆነና ግድቡ የሀይል ፍላጎትን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ግድቡ ምን ያህል ርዝመት፣ ምን ያህል ውሃ መያዝና ምን ያህል ሀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚሳይ መነሻ ዝርዝር ዕቅድ እና ጥናት በሀገሪቱ የመስኖ ሚኒስቴር በኩል መከናወኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ደቡብ ሱዳን ይህን ግድብ የመገንባት ሉዓላዊ መብት እንዳላት ምክትል ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው ግድብ ሚነሱ አለመግባባቶች በትብብር መንፈስ በውይይት ሊፈታ ይገባል ብለዋል።
www.thenationalnews.com/world/africa/south-sudan-poised-to-realise-nile-dam-dream-says-minister-1.1248408
#ENA
@tikvahethiopia

#ምርጫ2013
ኢትዮጵያ በ2 ዙር የምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቃ የውጤት ይፋ መሆን እየተጠበቀ ነው።
ምርጫው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ዜጋ የተሳተፈበት መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።
ዛሬ አውሮፓ ህብረት ፣ እንግሊዝና ጀርመን፣ ጃፓንን ጨምሮ 12 ሀገራት ምርጫውን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የተሻሻሉ ሕችን ማውጣትን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አድንቀዋል፡፡
ሲቪል ማኅበራት በምርጫው ሂደት ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎ አመርቂ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ሆኖም ግን ፥ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ በተገደበበት፣ ጋዜጠኞች በሚዋከቡበት፣ የጸጥታ ችግር ባለበትና ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ምርጫ ዘመቻ ለማድረግ በተቸገሩበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫው መካሄዱን የገለጡት ሀገራቱ፣ የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ ንግግር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
አሜሪካም ከኢትዮጵያ ምርጫ ጋር በተያያዘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።
አሜሪካ ምርጫው በአለመረጋጋትና ግጭት ውስጥ የተካሄደ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ነው ብላለች።
አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸው እና ሌሎችም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ብላለች።
በድኅረ-ምርጫ ለፖለቲካዊ ንግግር፣ ግጭቶችን ለመፍታትና ለብሄራዊ ዕርቅ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ ብላለች። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ እንዲቆም ድጋሚ ጠይቃለች። #Wezema

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ሶስት ባልደረቦቹ ትግራይ ክልል ውስጥ መገደላቸውን ሪፖርት አደረገ።
MSF የባልደረቦቹን ሞት ማረጋገጫ ከሰማ በኃላ ሃዘን ላይ መሆኑ ገልጿል።
የደንገተኛ ጊዜ አስተባባሪ ማሪያ ኸርናዴዝ ፤ ረዳት አስተባባሪ ዮሀንስ ሃለፎም ረዳ፣ ሹፌር ቴድሮስ ገብረማርያም ገ/ሚካኤል ትላንት ከሰዓት ጉዞ እያደረጉ እያለ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር።
ዛሬ ጥዋት ባዶ መኪናቸው ተገኝቷል፤ ከመኪናው በትንሽ ሜትር ርቀት ደግሞ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው ተገኝቷል።
MSF ጥቃቱን ያወገዘ ሲሆን ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ ግን በሪፖርቱ ላይ ያለው ነገር የለም።
ማሪያ ፣ ዮሃንስ እና ቴድሮስ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሰዎች ድጋፍ በመስጠት ላይ ነበሩ፤ ለዚህ ስራ ክፍያቸው ይህ (ነፍሳቸውን መንጠቅ) መሆኑ ሊታሰብ የማይችል ነው ብሏል MSF።
ስለሰራተኞቹ ፦
• ማሪያ ኸርናዴዝ - ከማድሪድ (ስፔን ሀገር) የመጣች የ35 ዓመት ሴት ስትሆን ከMSF ጋር በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ በየመን ፣ ሜክሲኮ፣ በናይጄሪያ ሰርታለች።
• ዮሃንስ ሃለፎም ረዳ - ዕድሜው 31 ሲሆን ከኢትዮጵያ ነው ፤ ድርጅቱን የተቀላቀለው የካቲት ወር ላይ ነበር።
• ቴድሮስ ገብረማርያም ገብረሚካኤል - ዕድሜው 31 ሲሆን ከኢትዮጵያ ነው ፤ ከግንቦት ወር ጀምሮ የድርጅቱ ሹፌር ነበር።

.
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አርማ (logo) መቀየሩን ዛሬ አሳውቋል።
አዲሱ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አርማ ከላይ በፎቶው በቀኝ በኩል የሚታየው ነው።
ከሳምንት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽንም አዲስ አርማ ለህዝብ ማስተዋወቁ አይዘነጋም።

#Ethiopia
የ24 ሰዓት የኮቪድ ሪፖርት :
• የላብራቶሪ ምርመራ - 5,396
• ቫይረሱ የተገኘባቸው - 168
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ 774
አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 275,769 የደረሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 4,302 ህይወታቸው ሲያልፍ 258,203 ሰዎች አገግመዋል። ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,988,335 ደርሰዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ሶስት ባልደረቦቹ ትግራይ ክልል ውስጥ መገደላቸውን ሪፖርት አደረገ። MSF የባልደረቦቹን ሞት ማረጋገጫ ከሰማ በኃላ ሃዘን ላይ መሆኑ ገልጿል። የደንገተኛ ጊዜ አስተባባሪ ማሪያ ኸርናዴዝ ፤ ረዳት አስተባባሪ ዮሀንስ ሃለፎም ረዳ፣ ሹፌር ቴድሮስ ገብረማርያም ገ/ሚካኤል ትላንት ከሰዓት ጉዞ እያደረጉ እያለ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር። ዛሬ ጥዋት ባዶ መኪናቸው ተገኝቷል፤…
#Update
የMSF ባልደረቦች የተገደሉት በህወሓት ኃይሎች ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ገለፀ።
መንግስት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጣው መግለጫ ፥ አቢ አዲ በተባለ ስፍራ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኛ በሆኑ 3 ሰዎች ላይ ግድያ ተፈፅሟል፤ ግድያውን የህወሓት የሽብረ ቡድን አባላት ናቸው የፈፀሙት" ብሏል።
በዚህም ሀዘን እንደተሰማውና ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንደሚመኝ ገልጿል።
በዚሁ ሃዘን መግለጫ መንግስት በተደጋጋሚ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የፀጥታ ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ለሰራተኞች ደህንነት ሲባል ማንኛውም እንቅስቃሴ በመከላከያና በፀጥታ አካላት ታጅበው ለዜጎች እንዲያደርሱ ሲመክር መቆየቱ አስታውሷል።
ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የተወሰኑ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶቾ ከመንግስት እውቅና ውጪ ሲንቀሳቀሱ ይስታዋላል ይህም የከፈ ችግር እያስከተለ ነው ብሏል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አብይአዲ አካባቢ ህወሓት እንደሚንቀሳቀስ በመግለፅ በአካባቢው ሶስት የMSF ዳልደረቦች መገደላቸውን ገልጿል።
ሰራዊቱ ፥ "የበለጠ በራሳችን መንገድ የሚረጋገጥ ቢሆንም ፥ የህወሓት ታጣቂዎች ሰራተኞቹን ከመኪና አስወርደው እንደገደሏቸው ቅድመ መረጃ ደርሶናል" ብሏል።
ከሟቾቹ መካከል አንዷ ስፔናዊት ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ገልጿል።
በቀጣናው እርዳታ ሰራተኞች እንዲሁም ሚዲያ አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ሲያሳስብ እንደነበር አስታውሷል።
ሰራዊቱ የሟቾችን አስክሬን በክብር እንዲያርፍ ለማድረግ ፣ ለሚያጣራ አካልም ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍል ገልጾ፤ በራሱ በኩልም ጠንካራ ማስረጃ አስደግፎ እንደሚያቀርብ ቃል ገብቷል።
ወንጀለኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

"Maal Mallisaa" ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመሞቱ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው 3ኛ አልበሙ ሊወጣ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተሰምቷል። የአዲሱ አልበም ማስታወቂያዎች በመዲናችን አዲስ አበባ እየተለጠፉ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአልበሙን መውጣት በሚጠባበቁት ዘንድ ልዩ ትኩረትን ስቧል። የአልበሙ ስያሜ "Maal Mallisaa" እንደሚሰኝም ታውቋል። የአዲሱ አልበም መውጫ ቀን መቼ ነው? የሚለው ለጊዜው…
#HachaluHundessa
የዝነኛው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው ሙሉ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል ብለዋል።
ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ፥ የፊታችን ሰኞ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ በ34 ዓመቱ ከተገደለ 1 ዓመት እንደሚሆነው አስታውሰዋል።
አክለውም ፥ "ህዝቡ ለእሱ ያለውን ስሜት አውቃለሁ፤ ድምፁን መስማት ያፅናናቸዋል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።
ወ/ሮ ፋንቱ የድምፃዊ ሃጫሉ አዲሱ (3ኛው) አልበም ከመሞቱ ብዙም ሳይቆይ በፊት የተቀዱ ስራዎች እንዳሉት ተናገረዋል።
አዲሱ አልበም "Maal Mallisaa" የሚሰኝ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙ "መፍትሄው ምንድነው ?" የሚል ነው።
በነገራችን ላይ አልበሙ በቀጣይ ሳምንት ለገበያ የሚቀርብ ቢሆንም ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ በ iTunes ላይ ቀርቧል ፤ እዛ ላይ በመግዛት ማዳመጥ ይቻላል።
ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ አልበሙ በCD አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለገበያ ይቀርባል።
ውድ የቲክቫህ አባላት አልበሙን ህጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ በመግዛት እንድታዳምጡ እናበረታታለን፤ በማህበራዊ ሚዳያዎች ላይ በህገወጥ መንገድ እንዳይሰራጭ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ አድርጉ።
ድምፃዊ ሃጫሉ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ ይታወሳል።
#TikvahFamily

40 ሺህ ዜጎችን የመመለሱ ዘማቻ ተጀመረ።
በሳውዲ ዐረቢያ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ ያሉ ዜጎችን ከትላንት ሌሊት ጀምሮ መመለስ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ እስረኞችን ወደ ሀገር የመመለስ ዘመቻውን በተመለከተ ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል የሰጡት መረጃ፦
- ዛሬ ከጅዳ 4 እና ከሪያድ 2 አውሮፕላኖች በጥቅሉ 6 አውሮፕላኖች ታሳሪዎችን ወደ ሀገር መመለስ ይጀምራሉ።
- ለአሁኑ በረራ በእስር ቤቶች ዉስጥ ያሉ ሴቶች፣ህጻናትና አቅመ ደካሞች ተመርጠዋል።
- ቀጥሎም በየቀኑ 8 በረራዎችን በማድረግ 40 ሺ ታሳሪዎችን በ2 ሳምንት ዉስጥ ወደ ሀገር ለመመለስ ታቅዷል።
- ከዛሬ ጀምሮ በሁለት ሳምንት ዉስጥ ወደ ሀገር የሚመለሱት ቀደም ብለው በተለያዩ እስር ቤቶች ዉስጥ ታስረው የሚገኙትን ኢትዮጵያውያንን እንጂ ሰሞኑን እየታሰሩ ያሉትን አይጨምርም።
- ሰሞኑን በአፈሳ መልኩ እየታሰሩ የሚገኙትን አስመልክቶ በድንገት የተያዙ ስለሆነ በሳውዲ ዐረቢያ ቆይታቸው ያፈሩት ሀብትና ንብረት ያላቸው በመሆኑ ሀብትና ንብረቶቻቸውን ሳይወስዱ ባዶ እጃቸውን ወደ ሀገር መመለስ የለባቸውም ብለው ለሳውዲ ዐረቢያ መንግስት አቤቶታ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነው። ከፊሎቹ ደግሞ የገንዘብ ቅጣት ሳይከፍሉ ከሳውዲ መውጣት የማይችሉ በመሆናቸው የገንዘብ ቅጣቱ ምህረት እንዲደረግላቸው እየተጠየቀ ነው።
- ሰሞኑን በአፈሳ የተያዙ ዞጎች ጉዳይ አሁን ወደ ሀገር ለመመለስ የተዘጋጁት 40ሺህ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ዘመቻ ሲጠናቀቅ የሚቀጥል ነው።
ይህን መረጃ ከኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተገኘ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ በስደት ላይ የነበሩ 380 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገቡ።
ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና የሠላም ሚኒስትር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሁን የገቡትን ጨምሮ 2 ሺህ የሚሆኑ ከስደት ተመላሾች ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ ለማስመለስ እየተሠራ ነው።
መረጃው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

ጆርጅ ፍሎይድን በጭካኔ የገደለው ፖሊስ ተፈረደበት።
ባለፈው ዓመት በአሜሪካ፣ ሚኒሶታ ውስጥ ጆርጅ ፍሎይድን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው አሜሪካዊ የቀድሞ የፖሊስ መኮንን ዴሪክ ቻውቪን 22 ዓመት ከ6 ወር እስር ተፈረደበት።
ፍርዱን ያሳለፉት ዳኛ ቻውቪን ይህ ቅጣት የተላልፈበት "የተጣለበትን እምነት እና ኃላፊነት በማጉደል እንዲሁም በታየው ልዩ ጭካኔ" ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል።
ቻውቪን እንደ አጥቂ ወንጀለኛ እንዲመዘገብና በቀሪ ዕድሜው የጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳይሆንም ታግዷል።
የፍሎይድ ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ውሳኔውን በደስታ ተቀብለዋል።
የፍሎይድ እህት ብሪጅት ፍሎይድ ውሳኔውን ፥ "የፖሊስ ጭካኔዎች በመጨረሻ በደንብ እየታዩ መሆናቸውን ቢያሳይም ገና ብዙ የሚቀር መንገድ አለ" ብለዋል።
ጠበቃው ቤን ክሩም በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው ላይ "ይህ ታሪካዊ ቅጣት ተጠያቂነትን በማስፈን የፍሎይድ ቤተሰቦችን እና አገራችንን ወደ ፈውስ አንድ እርምጃ እንዲጠጉ ያደርጋቸዋል" ብለዋል።
የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፍርዱን "ተገቢ ይመስላል" ብለው ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ስለመናገራቸውን ቢቢሲ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ የሚገኘው።
ዪኒቨርሲቲው ዛሬ እያስመረቃቸው ያለው ተማሪዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸው መሆኑን በምረቃው ስነ-ስርዓት ተገልጿል።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ለስምንተኛ ጊዜ ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን ዛሬዎቹን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ከ13 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማሰልጠኑን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ዘግቧል።

#GERD
ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ ከሱዳን እና ከግብፅ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በወታደራዊ መንገድ የመፍታት ፍላጎት እንደሌላት አረጋግጠዋል ፤ ነገር ግን ለዚህ ሁኔታ ዝግጁነት እንዳላት ተናግረዋል።
ይህን የተናግሩት በሩስያ ሞስኮ ከተማ በ9ኛው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኃላ ከሩስያ RT ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምምልልስ እንደሆነ ከRT ድረገፅ ላይ ተመልከትናል።
ሌ/ጄኔራል ባጫ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ያለውን አለመግባባት በወታደራዊ መንገድ ይፈታ እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፥ “ለአገሬ የውሃ ጉዳይ ለጦርነት መንስኤ ሊሆን አይገባም፤ ስለሆነም መፍትሄው ወታደራዊ ሊሆን አይችልም፣ ከሁሉ የተሻለው መፍትሔ በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገው ውይይት ነው" ብለዋል።
አክለውም ፥ የግብፅ ወገን ችግሩን በድርድር ለመፍታት አይፈልጉም ፤ ለውይይት ይመጣሉ ሁሉንም ሃሳብ ውድቅ ያደርጋሉ። በእኔ እይታ የተሻለው መፍትሄ ድርድር ነው፤ ችግሩን በወታደራዊ መንገድ መፍታት አይችሉም" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌ/ጄኔራል ባጫ ግብፆቹ፥ ግድቡን ለማጥቃት አይሞክሩም ፤ ነገር ግን ቢሞክሩት እንኳን ችግሩን ሊፈቱ ወይም ድግቡን ሊያጠፉት አይችሉም፤ ግድቡ በቦንብ እና በተዋጊ ፕሌኖች ሊወድም አይችልም የድግቡን ጥንካሬ እነሱም ያውቁታል" ብለዋል።
በተጨማሪም ሌ/ጄኔራል ባጫ፥ "ችግሩን በውይይት እንፈታዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ዝግጅት ማድረጉን ይህ ደረጃ ሲያበቃም ሁሉም ነገር ጥሩ እንደሚሆን እንዲሁም ሁሉም አካል በግድቡ ግንባታ ላይ ሳይሆን በውሃ ክፍፍሉ ላይ በሚቀርቡት ሃሳቦች ላይ ለመወያየት ይመጣሉ ብለዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/GERD-06-26