TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዜዳንቶች በቅርቡ ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት እንዳደረጉ ቪኦኤ ዘግቧል። የክልሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዜዳንቶች ባደረጉት ውይይት ወቅታዊው የክልሉ የፀጥታ ችግር በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ…
#Amhara

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን፤ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችን አቋም በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው መረጃ " #የተሳሳተ ነው " አሉ።

ከሰሞኑን በአማራ ክልል ስላሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምንድነው የተባለው ?

ከቀናት በፊት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የፎረሙን ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ዶ/ር አስማረ ደጀንን ዋቢ በማድረግ ባወጣውና ቲክቫህ ኢትዮጵያም ባጋራው ዘገባ ፤ በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁኔታው #በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል የሚያስችል እንዳልሆነ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤
*  ተማሪዎች ገብተው ግጭቶች በሚመጡበት ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነት እንደማይወስዱ፤

* ዩኒቨርሲቲዎች ለ2016 የሚሆን የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት የነበረባቸው ቢሆንም አቅራቢዎቹ ከቦታ ቦታ ፤ ምርት ካለበት ቦታ ሄደው ተዘዋውረው መግዛት ስላልቻሉ የምግብ ግብአቶች በጠቅላላው ተማሪን ሊያስጠራ የሚችል እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴር " ለ2016 ትምህርት በአሁን ሰዓት ተማሪዎችን ጥሩ እያለ ነው " ብሎ ለፀጥታው ኃላፊነት የሚወስድ አካል ከሌለ ይህን ማድረግ #እንደሚያስቸግር ነው የገለፀው።

ከዚህ ባለፈ የፎረሙ አባልና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ፤ በአካባቢው የቀጠለው አለመረጋጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እንደማያስችል ከተስማሙት የፎረሙ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

ያለው ሁኔታ ካልተሻሻለ በስተቀር አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ግቢ ውስጥ ተማሪ ማስገባት በእጅጉ ፈታኝ እንደሚሆንና ለልጆችም ደህንነት በጣም አስጊ መሆኑን ፕሬዜዳንቱ ለጣቢያው ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨ ከቀናት በኃላ የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዛሬ በሰጡት ቃል " ሰሞኑን የተሰራጨው መረጃ በአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ያልተባለና ስህተት ነው " ብለዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል አመች ሁኔታዎችን እየተጠባበቁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን መጥራት መጀመራቸውንም ገልጸው፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ ማስተላለፉን ለአብነት አንስተዋል፡፡

"አብዛኞቹ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን እየጠሩ ነው" ያሉ ሲሆን " ብዙ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለመጥራት ግን የግብዓት ችግር ለተቋማቱ እንቅፋት ሆኗል " ብለዋል።

ዶ/ር አስማረ፤ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ግብዓት አቅራቢዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለማቅረብ የተቸገሩ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ መሆኑን አሳውቀዋል። በየአካባቢው ያሉ አቅራቢዎች ግብዓት እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን ተቀበሉ በሚልበት ጊዜ የማይቀበሉበት ምክንያት እንደሌለም ገልጸዋል።

" ክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር እየተሻሻለ ከመጣ ተቋማቱ ተማሪዎቻቸውን ወዲያው ይጠራሉ፤ ተማሪዎችን አይጠሩም የተባለው ስህተት ነው፤ አልተባለምም " ሲሉ ተናግረዋል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ግብዓት ለማግኘት ከመቸገራቸው ውጭ የመማሪያ ክፍሎችን አጽድተዋል፣እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም አድሰው ለትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ ለክልሉ ሚዲያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia