TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የምርጫ ውጤት በተመለከተ ፦

• ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሰኔ 14 በሰጡት መግለጫ ፦

- ከዛሬ ጀምሮ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው ደረጃ መገለፅ ይጀመራል።

- ቆጠራ ያጠናቀቁ ጣቢያዎች በሙሉ በምርጫ ጣቢያው የተገኘውን ውጤት ከዛሬ ጀምሮ መግለፅ ይጀምራሉ።

- ከነገ ጥዋት ጀምሮ እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ ያለውን ውጤት እና ቁሳቁስ ይዞ ወደየምርጫ ክልሉ ይሄዳል።

- ምርጫ ክልሎች ቢበዛ 5 ቀን ድረስ ውጤት ለማሳወቅ ይፈጅባቸዋል። ቦርዱ ግን በጊዜያዊነት ከስር ከስር ያሳውቃል።

- ነገና ከነገወዲያ ቦርዱ የሚገባለትን ውጤት ደረጃ በደረጃ ውጤቶችን እያረጋገጥ ይገልጻል።

- በ10 ቀን ውስጥ ውድድር በተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች #ቢያንስ ጊዜያዊ ውጤት ምርጫ ቦርድ ያሳውቃል።

NB : የምርጫ ጣቢያዎች ስራቸውን አምሽተው ስለሚያጠናቅቁ እና ቆጠራው ጊዜ ስለሚፈጅ ወደምርጫ ክልል ዛሬ ለሊት ጉዞ እንዳያደርጉ በመመሪያ ደረጃ ተገልጿል።

ትክክለኛ የማንለው የምርጫ ውጤት አገላለፅ የትኛው ነው ?

• ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ፦

- ምርጫ ቦርድ ይፋ ሳያደርግ እና የምርጫው ሂደት እንዲሁም የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ እከሌ ነው ያሸናፈው፣ ይሄን ከተማ እንከሌ አሸነፈ ፣ይሄን ክልል እከሌ አሸነፈ ማለት አይቻልም።

- ቦርዱ ይፋዊ የውጤት ገለፃ ሳያደርግ ማንኛውም ግምታዊ መረጃ ፣ ቅድመ ውጤት ትንበያ ማድርግ አይቻልም።

- ሚዲያዎች ቦርዱ ይፋ የሚያደርገውን የምርጫ ውጤት ብቻ ነው መዘገብ ያለባቸው፤ ከዛ ውጪ የሚደረጉት ተቀባይነት አይኖራቸውም።

NB : ወደሌላ ችግር እንዳያመራ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ የውጤት ገለፃ እንስኪያደርግ ማንኛውም አይነት ግምታዊ መረጃ ከማሰራጨት በመቆጠብ በትዕግስት መጠበቅ ያስፈልጋል።

@tikvahethiopia
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ

በየምርጫ ጣቢያዎቹ ውጤት እየተለጠፈ ይገኛል፤ ነገር ግን በርካታ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ነው።

ውድ አባላት ይፋዊና ቦርዱ ማህተም ያላረፈባቸውን ፤ በተለም ደግሞ በዘፈቀደ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን #በጥንቃቄ እንድትከታተሉ ይሁን።

ከምርጫ በኃላ ችግር የሚፈጥረው እንዲህ አይነት ጉዳይ ስለሆነ ሰላማዊ ሂደቱ እንዲጠበቅ አስተዋጽኦ አድርጉ።

@tikvahethiopia
በፎቶሾፕ ከሚቀናበሩ የምርጫ ውጤቶች ተጠንቀቁ !

የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እያሳወቁ ይገኛሉ።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት ናቸው የተባሉ ወረቀቶች እየተለጠፉ ነው።

ነገር ግን ወረቀቶቹ ላይ ያሉትን ቁጥሮች በፎቶሾፕ የመነካካት፣ የማስተካከል ምልክቶችን ታዝበናል።

በተለይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

1ኛ. ዘመኑ የረቀቀ ነውና የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ትክክለኛው ሪፖርት እስኪላክላችሁ ታገሱ

2ኛ. ድምፅ የሰጣችሁበት የምርጫ ጣቢያ #በአካል ተገኝታችሁ የተለጠፈውን ውጤት እንድትመለከቱ እናበረታታለን።

የውጤት ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ እስካሁን የተመጣበትን #ሰላማዊ ሂደትን ሊያበላሽ ስለሚችል ከሀሰተኛ መረጃዎች/በይፋ በምርጫ ቦርድ ካልተረጋገጡ ሪፖርቶች ሁሉ እንድትርቁ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
የመገናኛ ብዙሃን ምርጫውን አስመልክቶ ለሰሩት ሥራ ምስጋና ቀረበ።

ምስጋናውን ያቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ነው።

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን መገናኛ ብዙሃን የምርጫውን ሂደት ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረ እንዲሁም ከፍ ባለ አገራዊ ስሜት መዘገባቸው የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብሏል።

የባለሰልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሀመድ ኢድሪስ ፥ "ጋዜጠኞች መረጃዎችን ለማሰባሰብ በከተማና በገጠር አካባቢዎች ተሰማርተው በተቀናጀ መልኩ ሚዛናዊና ትክክለኛ ዘገባዎችን አቅርበዋል ይህም ጋዜጠኞች መስዋዕትነት ጭምር ለመክፈል ያላቸውን ዝግጁነት ያሳያል" ብለዋል።

ዳይሬክተሩ በአንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን በምርጫው አዘጋገብ ላይ የተወሰኑ ችግሮች ቢስተዋልባቸውም በአብዛኛው በመልካም ሊጠቀስ የሚችልና የምርጫ ሂደቱን እውነታ ያሳየ እንደነበር ለኢዜአ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
በቤንሻንጉል ጉሙዝ 2 የምርጫ ክልሎች ምርጫ ተቋረጠ።

በአሶሳ ሆሃ እና መገሌ ምርጫ ክልል በ102 የምርጫ ጣቢያዎች በገጠመ የድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረትና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት ምርጫው መቋረጡን የቤንሻጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ለማ አስታውቁ።

በሁለቱ ምርጫ ክልሎች የተመዘገቡ መራጮች ቀጣይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሚሰጠው አቅጣጫ ምርጫው እንደሚካድ ኃላፊው በዛሬው ዕለት ገልፀዋል።

መረጃው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማስ ሚዲያ ነው።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፥ በምርጫ ህጉ መሰረት የምርጫ ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ መራጮች በትግስት እንዲጠባበቁና ከሌሎች ማንኛውንም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
በሲዳማ በ19 ጣቢያዎች ድምጽ እየተሰጠ ነው።

በሲዳማ ክልል "በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት" ምክንያት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ተቋርጦባቸው በነበሩ ጣቢያዎች ዛሬ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ከ5 ሰዓት ጀምሮ ነው ድምጽ እየተሰጠ የሚገኘው።

የድምጽ መስጫ ወረቀት በሂሊኮፍተር እንዲደርስ ተደርጎ ነው የዛሬው ምርጫ የቀጠለው።

የድምጽ አሰጣጡ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ስድስተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ በCarter Center በኩል ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አንድ አፍሪካ-አሜሪካዊ አዲስ አበባ በሚገኝ "ራዲሰን ብሉ" በተባለ በሆቴል ውስጥ በእራሱ ክፍል ህይወቱ አልፎ ስለመገኘቱ ኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል። በማህበራዊ ሚዲያ ግለሰቡ እንደተገደለ ተደርጎ የወጣው መረጃ "ያልተረጋገጠ" ነው ተብሏል። ምንም እንኳን እስካሁን ይፋዊ የምርመራ ሪፖርት ባይገኝም…
#Update

የፖሊስ ሪፖርት :

በውጭ አገር ታዛቢው የአሟሟት ሁኔታ ላይ ምርምራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ፖሊስ "ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል" ብሏል።

የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ነገር ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ መረጃውን እንዳገኘ ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱን እና አሜሪካዊው ከአልጋው ላይ ወደ መሬት ወድቆ ሕይወቱ አልፎ እንደተገኘ አመልክቷል።

በሟች ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ) ፣ የተለያዩ መታወቂያዎችና መንጃ ፈቃድ ተገኝቷል።

መንጃ ፈቃዱ "በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ብሔራዊ የድራይቪንግ ላይሰንስ" የሚል እንደሆነ ተገልጿል።

ፖሊስ አሜሪካዊው ሚጠቀምባቸው 'በርካታ' መድሃኒቶች ማግኘቱንና "ምናልባት ሁኔታው ሲታይ በተፈጥሮ የሞተ እንደሚመስል ፥ ነገር ግን ትክክለኛው መረጃ ከአስከሬን ምርመራ ውጤት በኋላ የሚታወቅ" መሆኑ አስረድቷል።

በአሜሪካዊው ዜጋ ሰውነት ላይ ምንም አይነት የአካል ጉዳትና ቁስለት አለመገኘቱንም ፖሊስ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመሆን በአሜሪካዊው ዜጋ አሟሟት ላይ ምርምራ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት በቀጣይ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

የካርተር ሴንተር ፕሮግራም በኢትዮጵያ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ በራዲሰን ብሉ ሆቴል ሕይወቱ ያለፈው የተቋሙ የአዲስ አበባ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ጆን ማርሽ መሆኑን አሳውቋል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopia
#Update

በትላንትናው እለት (ሰኔ 14/2013 ዓ.ም) የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሳይጠናቀቅ ከቀረባቸው ቦታዎች መካከል ጋምቤላ ክልል ያሉ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ይገኙበታል።

በእነዚሁ የምርጫ ክልሎች ላይ ተቋርጦ የነበረው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዛሬ ከቀኑ 8:00 ሰአት ጀምሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው እለት የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እንደሚጠናቀቅ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

(ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ/ም)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

መግለጫውን በVoiceChat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
Live stream finished (33 minutes)
#Update

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተለጠፉ ያሉት በምርጫ ክልል ደረጃ ማን እንዳሸነፈ የሚገልፁ መረጃዎች ሊቆሙ እንደሚገባ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።

የውጤት ድምሩ ከምርጫ ጣቢያ ተሰብስቦ ክልል ላይ ያለመጣ መሆኑንም አሳውቋል።

ማንኛውም ቦርዱ ያልገልፀውን ውጤት መግለፅ ክልክል ነው ወንጀልም ነው ሲል አስገንዝቧል።

ፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ይፋ ያላደረገውን ውጤት ከማሳወቅ በመቆጠቡ ረገድ እንዲሁም ከምርጫ ጋር ባወጧቸው መግለጫዎች ያሳዩት ሁኔታ የሚበረታታ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በአንፃሩ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች፣ አክቲቪስቶች ፣ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች በቦርዱ ያልተረጋገጠ ውጤት ሲያሰራጩ የነበረ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ተብሏል።

ሁለት እና ሶስት ቀናትን በመታገስ የምርጫ ክልል ላይ የሚወጡ ውጤቶችን ማየት እንደሚቻል የገለፀው ቦርዱ፤ ከዛ በፊት በግል የሚሰጡት አስተያየቶች ጠቃሚ አይደሉም ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፖሊስ ሪፖርት : በውጭ አገር ታዛቢው የአሟሟት ሁኔታ ላይ ምርምራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ፖሊስ "ትናንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል አሜሪካዊ ዜጋ በመኝታ ክፍሉ ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል" ብሏል። የሆቴሉ የጽዳት ሠራተኛ ትናንት ጠዋት አንድ ሠዓት ገደማ አሜሪካዊው ያረፈበትን የመኝታ ክፍል ለማጽዳት ስትገባ ያየችውን ነገር ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ፖሊስ ገልጿል።…
#Update

"ራዲሰን ብሉ ሆቴል" ውስጥ ሞተው የተገኙት ግለሰብ ታዛቢ አለመሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሟቹ ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ) እና ሌሎችም ቁሳቁሶችን አግኝቻለሁ ሲል ለኢዜአ መናገሩ ይታወሳል።

ከደቂቃዎች በፊት ወቅታዊ መግለጫ የሰጡት የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ግለሰቡ የካርተር ሴንተር አለም አቀፍ ታዛቢ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ግለሰቡ እንደማንኛውም ድጋፍ ሰጪ አለም አቀፍ ተቋም በታዛቢነት ሳይሆን በእንግድነት ከቦርዱ ባጅ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

ግለሰቡ የተሰጣቸው "የልዩ የእንግድነት ባጅ" ነው ያሉት ሶሊያና በዚህ የልዩ ባጅ የምርጫ ሂደቱን የመከታተል ነገር ግን የመታዘብ ስራ ከማይሰሩ አጋር ድርጅቶች የሚሰጥ ባጅ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ፥ ከካርተር ሴንተር ምርጫውን ለመታዘብ የመጣ ታዛቢ የለም ብለዋል።

"አሟሟታቸውን ቦርዱ ሰምቷል በዚህም አዝኗል ፤ አማሟታቸው በመንግስት ፖሊስ እና በሌሎች ተቋማት እየታየ እንደሆነ ሰምተናል ነገር ግን ከምርጫው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Exclusive

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከምርጫ 2013 ጥቂት ቀን አስቀድመው በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ በግል ምክንያት ምርጫውን መቀጠል እንደማይችሉ መግለፃቸው ይታወሳል።

ትላንት በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ግን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በተወዳደሩበት ጅማ አካባቢ የመራጮችን ድምፅ ስለማግኘታቸው በምርጫ ጣቢያ ላይ በተለጠፈ ውጤት መግለጫ ወረቀት ላይ ለማየት ተችሏል።

ይህን ጉዳይ የ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዴት እንደማያየው ? የጠየቅናቸው የቦርዱ የኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ይህን አጭር ምላሽ ሰጥተውናል ፦

"እኛ ጋር አጠቃላይ የተመዘገቡ 148 የግል ተወዳዳሪዎች አሉ፤ ከማንኛውም ተወዳዳሪነት ለመውጣት የግልም ሆነ የፓርቲ ተወዳዳሪ እጩነቴን ትቻለሁ የሚል "እጩነት መተው" የሚባል ፎርም አለ እሱ ተሞልቶ መቅረብ አለበት።

እኔ እስከማውቀው ድረስ በኡስታዝ አህመዲን ጀበል የቀረበ የእጩነት መተው ማመልከቻ የለም እኛ ጋር ፤ ባሎቱ ላይ አሉ ፤ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ አሉ ተቆጥሮ ይቀጥላሉ።"

NB : ወ/ሪት ሶሊያና ቦርዱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተመስርቶ ህጋዊ ውሳኔ እንደማይወስድ ገልፀዋል። እጩነት የህጋዊ ሂደት ነው ፤ በእጩነት መመዝገብ እና መሰረዝ ህጋዊ ነው ፣ እጩነትን መተውም ህጋዊ ነው እያንዳንዱ የራሱ ሂደት አለው ከዛ አንፃር እጩነትን መተው በሚል ቦርዱ ጋር የገባ ነገር እንደሌለ ገልፀዋል። በዚህ መሰረት ለምርጫ ክልሎች / ጣቢያዎች ምንም አቅጣጫ አልተሰጠም ፤ ድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ እንዳሉ እንደማንኛውም እጩ ነው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል የተስተናገዱት ብለዋል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሲዳማ በ19 ጣቢያዎች ድምጽ እየተሰጠ ነው። በሲዳማ ክልል "በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት" ምክንያት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ተቋርጦባቸው በነበሩ ጣቢያዎች ዛሬ ምርጫ እየተካሄደ ነው። የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በተቋረጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ከ5 ሰዓት ጀምሮ ነው ድምጽ እየተሰጠ የሚገኘው። የድምጽ መስጫ ወረቀት በሂሊኮፍተር እንዲደርስ ተደርጎ ነው የዛሬው ምርጫ የቀጠለው። የድምጽ አሰጣጡ እስከ ምሽት…
"...ለሊቱን ቆጠራው ተከናውኖ ውጤቱ ነገ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ይደረጋል" - አቶ ፍሬው በቀለ

ከ5 ሰዓት ጀምሮ በሲዳማ ክልል የቀጠለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሰላም ተጠናቋል።

ምርጫው ለዛሬ ያደረው በ "ድምፅ መስጫ ወረቀት እጥረት" ምክንያት መሆኑ ይታወቃል።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ እና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው በቀለ ለኢዜአ እንደገለጹት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በ19ኙ የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ 1 ሺህ 998 ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቶ ተጠናቋል።

በጣቢያዎቹ ሌሊቱን ቆጠራውን በማከናወን ውጤቱን ነገ ጠዋት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ፍሬው ለኢዜአ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ፣ ትግራይ ክልል የተነሳው ግጭት እንሆ 8 ወር አስቆጥሯል።

ግጭቱ የሺዎችን ህይወት እንደቀጠፈ፣ ሺዎችንም እንዳሰደደ ቤት ፣ በርካቶች አካል እንዳጎደለ፣ በርካታ ሴቶችን ለፆታዊ ጥቃት እንደዳረገ፣ በርካታ ህፃናትን በአካልም በስነልቦናም እንደጎዳ፣ እንደተመድ ሪፖርት መቶ ሺዎችን ለረሃብ እንዳጋለጠ ይታመናል።

የፌዴራል መንግስቱ የትግራይ ሁሉንም ከተሞች በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኃላ በተለያዩ ጊዜያት ከዚህም ከእዚያም የግጭት ሪፖርቶች ይወጡ እነደነበር የአደባባይ ሃቅ ነው።

ከሰሞኑን ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ፣ የኢትዮጵያን ጉዳይም የሚከታተሉ የዓለም ሚዲያዎችም ፊታቸውን ወደምርጫው ሲያዞሩ ጠንከርና ከበድ ያለ ግጭት በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች እንደነበሩ ተሰምቷል።

ከባድ ግጭት እንደነበረም የሀገር መከላከያ ሰራዊትም ያረጋገጠው ጉዳይ ነው።

ከፌዴራሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገባው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወሓት ኃይል በርካታ የክልሉን ከተሞችን መያዙን እየገለጸ ነው። የመከላከያ ሠራዊት ቡድኑ አገኘሁ ያለውን ድል "ሐሰተኛ ዜና" ሲል አጣጥሎታል።

የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮ/ል ጌትነት ከሰሞኑ ከባድ ውጊያ እንደነበረ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል፥ የህወሓት ኃይሎች ከተሞችን ፣ የጦር መሳሪያዎችን ወይም ወታደሮችን ማርከናል ያሉትን ግን ሐሰት ነው ብለዋል።

"የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫ በማካሄድና በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ሥራ በበዛበት ጊዜ ሽብርኛው ህወሓት፣ ታዳጊዎችን በማሰለፍ በሽብር ተግባራት ላይ ተሰማርቶ ነበር" ሲሉ ገልፀዋል ኮሎኔሉ።

የተካሄደው ዘመቻ የቡድኑን መሪዎች ለመያዝ እንደነበር አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Crisis-06-23

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ አለ ?

በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ አዲስ በሚመሰረተው መንግስት ላይ ተፅእኖ ይኖረው ይሆን ሲሉ ይጠይቃሉ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት ለቲክቫህ በሰጠው ምላሽ ምርጫ 2013 በሁለት ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም።

የቦርዱ የኮሚኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በሰጡት ማብራሪያ ምርጫው በ2 ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ ምንም የሚፈጥረው ተፅእኖ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ "ምርጫው በሁለት ዙር ተደርጎ የሚጠናቀቀው መስከረም ከመግባቱ በፊት ነው ፤ የአዲሱ መንግስት ምስረታ ደግሞ መስከረም መጨረሻው ሳምንት ላይ ስለሆነ ከዛ በፊት ምርጫና ውጤቱ ስለሚያልቅ የመንግስት ምስረታ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም" ብለዋል።

ሰኞ ብዙ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫው ስለተካሄደ መንግስት የሚመሰርተውን አካል ማወቅ እንደሚቻል ገልፀዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ "ሰኔ 14/2013 ዓ/ም ምርጫ ሳይደረግ በቀሩት ክልሎች ማን ይወክለናን የሚለውን ለመወሰን በተለይ የክልል መቀመጫቸውን ምክንያቱም በዚያኛው ጊዜ የፌዴራል መቀመጫን ነው የምናስበው ፤ የክልል መቀመጫ የሚያሸንፉ ሊኖሩ ስለሚችሉ የክልል መቀመጫቸውን አይተው እዛ ላይ ማነው ክልሉን የሚያስተዳድረው የሚለውን ለመለየት ጠቃሚ ነው፥ በተጨማሪ መራጮች ወኪሎቻቸውን ልከው ለመደራደር ለመከራከር ይጠቅማቸዋል ፤ ነገር ግን ምርጫው በሁለት ዙር መደረጉ በመንግስት ምስረታ ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም" ሲሉ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia