TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WeyzeroTsionTeklu

'ኩራቶቻችን ናችሁ' በሚል ኃሳብ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታ እና የእኛ ለእኛ የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር መስራች የሆኑት ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዮት በመገኘት በተቋሙ ውስጥ የኮቪድ 19 ምርምር ማዕከል ለሚገኙ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች መገልገያ የሚውል ፔርሙዞችን በስጦታ መልክ ለግሰዋል፡፡

ለእነዚህ ሌት ተቀን ከመጋረጃው በስተጀርባ በላቦራቶሪ ውስጥ በመሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዋችን "ኩራቶቻችን ናችሁ" በማለት ያላቸውንም አክብሮትም ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WeyzeroTsionTeklu

ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ!

ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ከመጋቢት 28 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።

ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘርፍን በሚኒስትር ዴኤታነት ይመራሉ።

ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን አገልግለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው መረጃ ወ/ሮ ፅዮን 'የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ' በመሆን አገልግለዋል የሚለው #ስህተት ነው። ማስተካከያ ቢደረግበት መልካም ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia