TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BREAKING

ኢትዮጵያ 4 የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን አባረረች።

ዲፕሎማቶቹ አዲስ አበባ አየርላንድ ኤምባሲ ይሰሩ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአል ዓይን በሰጡት ቃል፥ " በኢትዮጵያ ይሰሩ የነበሩ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች በሳምንት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል " ብለዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
#Breaking

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ካሳጊታ መያዙን እንዲሁም ዛሬ ደግሞ ጭፍራ እና ቡርቃ እንደሚያዙ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ በግንባር ሆነው ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) በሰጡት ቃል ነው።

በቴሌቪዥን ጣቢያው የተላለፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቪድዮ መግለጫ በግንባር ሆነው ሰራዊቱን ሲመሩ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላውን ሙሉ በሙሉ አነሳ።

ለባለፉት አራት ወራት ተግባራዊ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ አስታወቀ።

ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ክልከላው የተጣለው "የኢኮኖሚ አሻጥርን" ለመከላከል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ተግባራዊ ተድርጎ የነበረው በትይዩ እና በህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ ነበር።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#BREAKING

የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ስልጣን ለመልቀቅ እንዳሰቡ ለፖለቲከኞች ቡድን መናገራቸውን ሮይተርስ ለሃምዶክ ቅርብ ከሆኑ ሁለት ምንጮች መስማቱን ዘግቧል።

ቡድኑ በቦታቸው ላይ እንዲቆዩ ቢጣይቃቸውም እሳቸውን ግን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ነግረዋቸዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ በጥቅምት ወር በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በሚመራው ጦር መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸው ለቁም እስር መዳረጋቸው በኃላም በተደረገ ስምምነት ከሳምንታት በፊት ወደ ስልጣናቸው መመለሳቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው ? የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ሊለቁ መሆኑን ዘግቧል። የዜና ወኪሉ መረጃውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ዛሬ መስማቱን ገልጿል። ለሚዲያ ማብራሪያ መስጠት ያልተፈቀደላቸው አንድ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላ ሀምዶክ የቢሮ ሰራተኞቻቸውን አደራ እንዲያስረክቡ ማዘዛቸውን ፤ ሰራተኞቹም ይህን ከእሁድ ማታ ጀምሮ መተግበር…
#BREAKING

ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ።

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት።

ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ምንጭ መስማቱን መዘገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

ከእስር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ፦

1. አቶ ስብሐት ነጋ

2. ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ

3. አቶ ዓባይ ወልዱ

4. አቶ አባዲ ዘሙ

5. ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር

6. አቶ ኪሮስ ሐጎስ

7. አቶ ጃዋር መሐመድና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። @tikvahethiopia
#BREAKING

የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ፦

" የሚኒስትሮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ቀሪ የሚሆንበትን ጊዜ በሚመለከት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ሕውሃት እና ግብረአበሮቹ በሃገራችን ህልውና እና ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ በመሆኑ እና ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 ፀድቆ በስራ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማውጣት የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑ እና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 አንቀጽ 11(2) በተደነገገው መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ስልጣን ያለው በመሆኑ የአዋጁን ተፈጻሚነት ቀሪ እንዲያደርገው የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጥልቀት ተወያይቶ በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ "

@tikvahethiopia
#BREAKING

የአፍሪካ ህብረት ቡርኪናፋሶን አገደ።

በቡርኪና ፋሶ ከተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ጋር በተያያዘ የአፍሪካ ህብረት ሀገሪቱን ከማንኛውም የህብረቱ እንቅስቃሴ ማገዱን ዛሬ አሳውቋል።

እግዱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ወደነበረበት እስኪመለስ ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ም/ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ [የ193 አባል ሀገራት] አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ በድምፅ ወስኗል።

ስብሰባው ዛሬ ሰኞ ይካሄዳል።

ሩስያ ስትቃወም [ድምፅን በድምፅ የመሻር /veto power/ መብቷ እዚህ ላይ ተግባራዊ አይሆንም] ፤ ቻይና ፣ ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን አይነት ውሳኔ ሲወስን በ40 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በድርጅቱ ታሪክ ደግሞ 11ኛው መሆኑ ተነግሯል።

#የደገፉ_ሀገራት

🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇮🇪 አይርላድ
🇦🇱 አልባኒያ
🇬🇦 ጋቦን
🇲🇽 ሜክስኮ
🇧🇷 ብራዚል
🇬🇭 ጋና
🇰🇪 ኬንያ

#የተቃወሙ

🇷🇺 ሩስያ

#ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ

🇨🇳 ቻይና
🇮🇳 ሕንድ
🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

@tikvahethiopia