TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

"ጥላቻን መቀነስ(-) ይቅርታን ማባዛት(*) ያለንን ማካፈል (፥) በፍቅር መደመር (+) ብለን ተነስተን ከጠበቅነው በላይ #ድጋፍ አግኝተናል። ከአርቲስቶች፣ ከአትሌቶች፣ ከወጣቶች፣ ከዲያስፓራው እና በተለያየ አካባቢ የሚገኙ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጋር ውይይት አድርገን #ውጤታማ ስራ ተሰርቷል። በዛሬው እለትም በተመሳሳይ በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ እንገኛለን።"

©ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የአማራ ክልል ተማሪዎችን ምሁራን #ሸለሙ፡፡

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በነበረው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ተማሪዎቹ የበለጠ #ውጤታማ እንዲሆኑ ምሁራኑ አበረታተዋል፡፡

ከምሁራኑ መካከል ፕሮፌሰር #ዳንኤል_ቅጣው ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች ለሚቀጥለው ትውልድ መንገድ ማሳየትን፣ ቅን መሆንን፣ ለነገሮች ትኩረት መስጠትን እና በቀጣይም ፈተና እንደሚኖር ሊገነዘቡ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚቀላቀሉበት ወቅትም የጊዜ አጠቃቀምን፣ ደጋግሞ መሞከርን እና #የንባብ ባህልን ማዳበር እንዳለባችው
መክረዋል።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምባሳደር #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአሜሪካ ኢምባሲ የደስታ መግለጫ አስተላለፈ፡፡ ያለ #ሴቶች ተሳትፎ አንድ ማህበረሰብ #ውጤታማ እንደማይሆን የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን ወደ ሃላፊነት ማምጣቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብሏል የአሜሪካ ኢምባሲ በመግለጫው፡፡ መንግስት ሴቶችን ያቀፈ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰዱ ኢምባሲው #አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#USA #ETHIOPIA

" ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ቁርጠኛ ነን " - አሜሪካ

አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር #ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ስትል አሳወቀች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ነው።

የአምባሳደር ማይክ ሐመር የኢትዮጵያ ጉብኝት ውጤታ ነበር ያለችው አሜሪካ  " ለኢትዮጵያ #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነን " ስትል አስታውቃለች።

በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲበለጽጉ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ እንደምትፈልግ ገልፃለች።

@tikvahethiopia