TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል። ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል። ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ…
#Update

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ፤ " ፈተና አንፈተንም " ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ  እንደማይችሉ አረጋግጠዋል፡፡

በግል መፈተን እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ያልተፈተኑና በተለያዩ #አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ፣ የወለዱ ተማሪዎች #ከአንድ_ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

የፈተና ዉጤት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተፈተኑ ተማሪዎች በወጣላቸዉ ፕሮግራም መሰረት ከተፈተኑ በኋላ የሁለቱንም ዉጤት ተጠቃሎ እንደሚገለፅ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" በደቡብ አፍሪካ በነበረው ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በስራ ጉብኝት በጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ይገኛሉ።

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ለአርባምንጭና ለአካባቢው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ወቅት ስለ ደቡብ አፍሪካ ድርድር ስምምነት የተወሰኑ ሀሳቦችን አንስተው ተናግረዋል።

ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለድርድር አይቀርብም በሚለው በሁለቱም ወገን (በመንግስት እና ህወሓት ማለታቸው ነው) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንድ ሀገር ወስጥ #ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም በሚለውም ጉዳይ ከስምምነት ተደርሷል።

- በትግራይ ክልል ህገወጥ በሆነ መንገድ የተደረገው ምርጫ በህጋዊ ምርጫ መተካት አለበት የሚለውም በሁለቱም ወገኖች (በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት) ተቀባይነት አግኝቷል።

- በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ያለው የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው እና አከራካሪ ቦታዎች የሰው ልጆችን ህይወት ሳይጠይቁ በሰላም፣ በድርድር እና በሀገሪቱ ህግ መሰረት ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ በሁለቱም ወገኖች መተማመን ላይ ተደርሷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በደቡብ አፍሪካ በነበረው የሰላም ድርድር ኢትዮጵያ መቶ በመቶ ያቀረበችው ሀሳብ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION

" ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል "

በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

" ሕዝቡ የሚኖረው በከብቶቹ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ድርቁ እስከ መቼ እንደሚቀጥል አይታወቅም፡፡

ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል።

የሞተውን የእንስሳት ሀብት ቁጥር ገና እየተጠና ነው፤ በሰዎች ላይ የደረሰውንም ጉዳት እየተገመገመ ነው።

ስለጉዳቱ የተጣራ አኃዝ ባይኖረንም በምግብ እጥረት ችግር ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች መረጃ አለን። "

NB. አምና በሶማሌ ክልል ካሉ 11 ዞኖች በአሥሩ ከባድ የድርቅ አደጋ ደርሶ #ከአንድ_ሚሊዮን ያላነሱ እንስሳትን ገድሏል። የዳዋ ዞን ገና ከዚህ አደጋ ያላገገመ ሲሆን ዘንድሮም ከባድ አደጋ ገጥሞታል።

Credit : #Reporter

@tikvahethiopia
በዓለም አቀፍ ርብርብ የተዘጋው ድረገፅ " ጄነሲስ ማርኬት " !

የሰዎችን የይለፍ ቃሎች ጨምሮ የግል መረጃዎችን ለአጭበርባሪዎች በመሸጥ የሚታወቀው ድረ-ገጽ በአለም አቀፍ ፖሊስ ትብብር መዘጋቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

ድረገጹ በኢንተርኔት ላይ የማጭበርበር ስራ የሚፈጽሙ ግለሰቦች መረጃዎችን የሚሸምቱበት የዓለማችን ትልቁ የመረጃ መረብ ወንጀል ጣቢያ ሆኖ ቆይቷታ።

" ጄኔሲስ ማርኬት " የተሰኘው ድረገጽ የግለሰቦችን ዲጂታል የጣት አሻራዎችን ጨምሮ፣ አድራሻዎችን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለወንጀለኞች ሲሸጥ ነበር።

ከዚህ ድረገጽ የተገኙ የግል መረጃዎችና የይለፍ ቃሎች የግለሰቦችን #የባንክ_አካውንት ድና የኢንተርኔት ግዢዎችን በቀላሉ ወንጀለኞች እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ድረገጹ እነዚህንም መረጃዎች አብዛኛውን ጊዜም #ከአንድ_ዶላር ባነሰ ዋጋ ሲሸጥ ቆይቷል።

ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የፖሊስና ደህንነት አካላት በመቀናጀት ነው ይህንን የሳይበር የወንጀል ጣቢያ ያዘጉት።

ጉዳዩን በተመለከተ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የወንጀል ኤጀንሲ (ኤንሲኤ) ምን አለ ?

" በተከታታይ በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ድረገጹን ሲጠቀሙ የነበሩ 24 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዚህም መካከል ድረ-ገጹን በመጠቀም የማጭበርበር ስራ እየፈጸሙ ያነበሩ ግለሰቦችም ይገኙበታል። "

ማክሰኞ ረፋድ ላይ በተጀመረው ክትትልና ፍተሻ ከ17 አገራት የተውጣጡ ፖሊሶችና የደህንነት አባላት በቅንጅት ተሳትፈዋል።

ዘመቻው በአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ / #FBI / እና በኔዘርላንድ ብሄራዊ ፖሊስ የተመራ ሲሆን የዩኬው NCA፣ የአውስትራሊያ ፌደራል ፖሊስ እና በርካታ የአውሮፓ ሃገራት ተጣምረውበታል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ያህል ፍተሻዎች የተከናወኑ ሲሆን በዚህም 120 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ረቡዕ ዕለት ወደ ጀነሲስ ድረገጽ የገባ ማንኛውም ሰው ‘ኦፐሬሽን ኩኪ ሞንስተር’ የሚል ማስጠንቀቂያና ድረገጹም መቆሙን የሚያሳይ መልዕክት አግኝተዋል።

የጄኔሲስ ድረገጽ 80 ሚሊዮን የሚሆኑ የዲጂታል አሻራዎችና የግል መረጃዎችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የማጭበርበር ገበያ የተፈጸመበት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የተሻሻለው የ " ንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያ " ሊወጣ ነው !

ከስልሣ ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ የወጣውን አዲሱን የንግድ ሕግ ማስፈጸሚያ መመርያዎች ውስጥ እና የመጀመርያው የሆነው በዚህ ዓመት ፀድቆ ሥራ ላይ እንደሚውል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

የንግድ ሕጉ ማስፈጸሚያ ይሆናል የተባለው ይህ የመጀመርያው መመርያ የ " አክሲዮን ማኅበራት " ን የሚመለከት ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ፤ " የአክሲዮን ማኅበራት ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ " በሚል የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ ተዘጋጅቶ በመጠናቀቁ በዚህ በጀት ዓመት ይፀድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

መመርያው ምን ይዟል ?

- በንግድ ሕጉ ላይ " የመተዳደሪያ ደንብ ያስፈልጋል ? አያስፈልግም ? " የሚለውን ጉዳይ ለማብራራትና በቀላሉ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎችና በሁሉም ፈጻሚ ተቋማት ወጥ በሆነ መንገድ እየተተረጎመ እንዲፈጸም ለማስቻል በሚረዳ መልኩ በመመርያው እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡

- መመርያው አክሲዮን ማኅበራት ሲደራጁ ገንዘብ ከሕዝብ የሚሰበሰብበት መንገድ ላይ ምን መሆን እንዳለበት በግልፅ ያመላክታል። ኅብረተሰቡ እንዳይበዘበዝ እንዴት መተዳደር እንዳለበት በዝርዝር የተቀመጡ አንቀጾችን አካቷል፡፡

አደራጆች የምሥረታ ሒደት ለማካሄድ የሚያስከፍሉት አስተዳደራዊ ወጪ የሚዋጣው ገንዘብ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለት በረቂቅ መመርያው ተመላክቷል፡፡

በምሥረታ ሒደት ከፈራሚዎች አስተዳደራዊ ወጪን ለመሸፈን ገንዘብ የተሰበሰበ እንደሆነ፣ ማኅበሩ ሲመሠረት የምሥረታ ወጪን ለማኅበሩ ማስተላለፍ የሚቻለው የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ክፍያ የምሥረታ ወጪውን ለመሸፈን ያልበቃ መሆኑን የምሥረታ ኦዲተር ካረጋገጠ ብቻ ነው።

በምሥረታ ኦዲተር ሪፖርት መሠረት ለአስተዳደራዊ ወጪ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቀሪ ገንዘብ ያለ እንደሆነ ማኅበሩ ሲመሠረት ፣ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ ይኖርበታል። ይህም ቀድሞ ለአገልግሎት ተብሎ የተሰበሰበን ገንዘብ ከብክነት ያድናል።

- አደራጆች በአክሲዮን ምሥረታ ወቅት ከፈራሚዎች ሚሰበሰበውን መዋጮ በባንክ በዝግ ሒሳብ ሲያስቀምጡ በገበያው ላይ ካለው የወለድ ምጣኔ አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ ወለድ እንዲያፈራ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።

- የማኅበሩ ምሥረታ በስኬት የተጠናቀቀ እንደሆነ ዋና ገንዘቡና ያስገኘው ወለድ ለማኅበሩ ገቢ መደረግ አለበት።

- የግል አክሲዮን ማኅበር ሚመሠረተው በመሥራቾች እንደሚሆን ይደነግጋል። መሥራቾች በባለአክሲዮንነት ከሚያገኙት መብት ውጪ በመሥራችነታቸው ምክንያት የሚከፈላቸው የአገልግሎት ክፍያ አይኖርም።

- በአክሲዮኖች ላይ #ከአንድ_መቶ_ብር (100) ያነሰ ዋጋ የተጻፈባቸው አክሲዮኖች ያላቸው ማኅበራት፣ ይህ መመርያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ቢያንስ ወደ አንድ መቶ ብር በማሳደግ መመሥረቻ ጽሑፋቸውን አሻሽለው ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

- የአክሲዮን ኩባንያዎች የሚያደራጁ ሰዎች ያለባቸው ኃላፊነት ምንድነው የሚለውም በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን በአዲሱ የንግድ ሕግ የአክሲዮን ኩባንያዎች የኤሌክትሮኒክስ ስብሰባ ማድረግ የሚችሉ በመሆኑ፣ ይህንን ለማስፈጸም ዝርዝር ጉዳዩ በዚህ መመርያ ተገልጿል።

" የቦርድ ስብሰባ " የሚደረግበት የኤሌትሮኒክ ዘዴ የተሰብሳቢዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል ፤ የውይይቱን የድምጽ ቅጂ በትክክል መያዝ የሚችል መተግበሪያ ያለውና ፤ ሚስጢራዊነትንም መጠበቅ የሚችል መሆን አለበት።

በመመስረቻ ጽሑፍ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በስተቀር እያንዳንዱ የቦርድ አባል በዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ ላይ በአካል የመገኘት መብት ያለው ሲሆን፣ የቦርድ ስብሰባን በኤሌትሮኒክ ዘዴ ለመሳተፍ ዳይሬክተሩ ጥያቄ ካላቀረበ በቀር፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊያስገድድ ወይም በአካል የመሳተፍ መብቱን ሊገድብ እንደማይችች ተቀምጧል፡፡

- ከመመርያው መውጣት በኋላ ብዙ አክሲዮን ያላቸው ኩባንያዎች በቀላሉ ስብሰባቸውን እንዲያካሂዱ ዕድል ይሰጣቸዋል።

- የአክሲዮን ዝውውሮችን በተመለከተ በዚህ መመርያ ግልጽ ድንጋጌ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በተለይ የግለሰብ አክሲዮንን ለማስተላለፍ #የትዳር_አጋር_ስምምነት ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡

"በግል የአክሲዮን ማኅበር" ውስጥ በግለሰብ የተያዘ አክሲዮንን ፦
- በሽያጭ ፣
- በስጦታ ፣
- በመያዣ
- በሌላ በማንኛውም መንግድ ለማስተላለፍ በሕግ ወይም ደግሞ በመመሥረቻ ጽሑፍ ከተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ አስተላላፊው በአስገዳጅነት ያገባ ከሆነ የትዳር አጋሩ ውል ለማዋዋል እና ሰነድን ለመመዝገብ ' ሥልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ ' ስምምነቱን መግለጽ አለበት።

ያላገባ ከሆነ / ከሆነች አግባብ ካለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ተገቢውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል በሚል መመርያው ይደነግጋል፡፡

- ሁሉም የአክሲዮን ማኅበራት ይህ መመርያ ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ድረገጽ ማበልጸግና በድረገጹ ላይ በሕጉ መሠረት ተገቢነት ያላቸውን መረጃዎች ማስቀመጥ አለባቸው። ይህንን ድንጋጌ የማይፈጽም የአክሲዮን ማኅበር የንግድ ፈቃዱ ሊታገድ እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

- አክሲዮን ለመሸጥ ስለሚወጡ #ማስታወቂያዎች በመመርያው ላይ ተቀምጧል።

ይህም ፤ " በማንኛውም በሕዝብ ማኅበር በምሥረታ ሒደት አክሲዮን ለመሸጥ በሚተላለፍ ማስታወቂያ ስለ ታሳበው የንግድ ሥራ አዋጭነት በጠቅላላው ከመግለጽ በስተቀር ስለሚያስገኘው የትርፍ መጠን በምን ያህል ጊዜ ለኢንቨስትምንት የተከፈለው ገንዘብ እንደሚመለስ ወይም ሌሎች በተጨባጭ ሊረጋገጡ የማይችሉ መረጃዎችን መስጠት አይቻልም " በሚል ተጠቅሷል፡፡

በማንኛውም #ዋና_ገንዘብ በማሳደግ ሒደት በግል ማኅበር ወይም በሕዝብ ማኅበር፣ ለሕዝብ አክሲዮን ለመሸጥ የሚደረግ ማስታወቂያ ማኅበሩ አስቀድሞ ያገኘውን ትርፍ የሚገልጽ ከሆነ፣ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመታት የትርፍ ውጤት መግለጽ ግዴታ አለበት፡፡

ነገር ግን ማኅበሩ #ለወደፊት የሚኖረውን አትራፊነት በቁጥር ወይ በመጠን መግለጽ አይቻልም።

ሚኒስቴሩ (ንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር) ወይም አግባብ ያለው ሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት አሳሳች ናቸው ብሎ ከወሰነ፣ አክሲዮን ለመሸጥ ለሕዝብ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች እንዲቋረጡ ለማዘዝ ይችላል።

.
.
.

መመርያው በአጠቃላይ ከአክሲዮን ምሥረታ ጀምሮ እስከሚፈርስበት ጊዜ ድረስ #ዝርዝር የአሠራር ጉዳዮችን በመተንተን የቀረበ ነው።

በአዲሱ የንግድ ሕግ መመርያ የማውጣት ሥልጣን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡

መመርያን ያዘጋጀው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሲሆን በተለይ #የሕዝብን_ገንዘብ ተቀብለው የሚያስተዳድሩ የአክሲዮን ማኅበራት ላይ መጠነኛና ቁጥጥር ለመዘርጋት የሚያስችል ነው፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ የረቂቅ መመርያው ዝግጅት ተሳታፊ የሕግ ባለሙያ አቶ ፈቃዱ ጴጥሮስን ዋቢ በማድረግ ያወጣው)

@tikvahethiopia