TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ንቁ‼️ያለማስተዋላችን ጥግ፣ ያለማገናዘባችን ጥግ፣ ያለማወቃችን ጥግ፣ የዝቅጠታችን ጥግ፣ ያለመማራችን ጥግ የኛ #ብሄር ተወላጆች ከኛ ጋር አብረውን የሚኖሩት #ብቻ ይመስለናል። ከብዙዎች ጋር ተጋብተው፤ ተዋልደ እንደሚኖሩ ማስተዋል አቅቶናል። ስራ ቦታ ከብዙሀኑ ጋር እንደሚሰሩ ረስተነዋል። ከብዙዎች ጋር ጎረቤት እንደሆኑ ረስተነዋል። በመላው ሀገሪቱ ውስጥ በሁሉም አቅጣጫ እንደሚኖሩ ዘንግተነዋል። ልጆቻችን ወንድሞቻችን እሩቅ ተጉዘው ከሌሎች ብሄር ወንድሞቻቸው ጋር እንደሚማሩ ዘንግተነዋል።

ዛሬ አንተ በፌስቡክ በምታሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ፣ ያልተጣራ መረጃ፣ የጥላቻ መልዕክት፣ የእርስ በእርስ ግጭት ቅስቀሳ መልዕክቶች #እሳቱ ቢነሳ ከጫፍ ጫፍ ያለው ምስኪኑ ወገን ተቃጥሎ አመድ ይሆናል። እሳቱ ሀገር ውስጥ ብቻ ነዶ አይጠፋም ውጪ ያሉትንም ያቃጥላል። #አንተም አይቀርልህም #አመድ ትሆናለህ!

ለምናሰራጨው መረጃ እና መልዕክት ጥንቃቄ እናድርግ! የሰላም ዋጋዋን እንረዳ! ወገኖቼ እናስተውል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቆመው ሁሉም ሲጠፋፋ ብቻ ነው!

በኃላ እንዳይፀፅተን እናስተውል!
አንድነት፤ ሰላም፤ ፍቅር!

ፀጋአብ ወልዴ
#ETHIOPIA

ፎቶ፦ የሩዋንዳው የእርስ በእርስ ግጭት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቃቂ ገበያ⬆️"#እሳቱ መንደድ ከጀመረ 1 ሰዓት ከ54 ደቂቃ ሆኖታል እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም። አካባቢው ላይ ብዙ ሰው አለ እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው።" #Alex

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ርብርቡ ቀጥሏል -- አቃቂ ገበያ!

"#እሳቱ መጀመሪያ ከነበረው #ኃይል በመጠኑ ቀንሷል ግን አሁንም ከፍተኛ ነው። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ህብረተሰቡ በአራቱም አቅጣጫ እሳቱን ለማጥፋት የሚያደረጉት ርብርብ እንደቀጠለ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia