TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዶዶላ #ሻሸመኔ #ቡታጅራ #ጅማ #ከሚሴ

ኑ ትውልድ እንገንባ!

ቤት ካላችሁ የመማሪያ መፅሃፍ ቢያንስ አንዱን ለሀገራችሁ በስጦታ አበርክቱ!

#ዶዶላ
0920068173/ቶሎሳ/

#ከሚሴ
0921632606/ኑር አህመድ/
0915543171/ሁሴን/

#ሻሸመኔ
+251915596576/አሸናፊ/

#ቡታጅራ
0910899212/Yab/

#ጅማ
+251942630419/ፍላጎት/
0911670454/አሰፋ/

•ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ የመደበኛ የመማሪያ እና አጋዥ መፅሃፍትን በመለገስ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን እናውርስ!!

📚የዘንድሮው አመት ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች በዚህ ስራ ላይ በስፋት በመሳተፍ ለመጭው ትውልድ አርዓያ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!

በዚህ ሀገራዊ ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ የበጎ አድራጎት #ማህበራትና #ግለሰቦች @tsegabwolde

በሁሉም ከተሞች ያሉ አስተባባሪዎችን በየዕለቱ እናውቃለን!

📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚

ትግራይ ክልል #ኢሮብ አካባቢ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መልዕክት አስቀምጡልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ትግራይ #ኢሮብ

በትግራይ ክልልና ኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚኖረው የኢሮብ ብሔረሰብ ተወላጆች ፣ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ለሁለት በመከፈላቸው ማኅበረሰቡ ለድርቅ ፣ ለስደትና ለተለያዩ በደሎች እየታገለጠ ይገኛል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ አሁንም ድረስ ከብሔረሰቡ 8 ቀበሌዎች ውስጥ ፦
* እንዳልገዳ፣
* ወርዓትስ፣
* ዓገረለኩማና ዳያዓሊቴና በተባሉ 4 ቀበሌዎች የኤርትራ ሠራዊት ይገኛል።

- ኢሮብን በዓዲግራት በኩል ከተቀሩት የትግራይ ክልል ከተሞች ጋር የሚያገናኘው መንገድ አገልግሎት አይሰጥም።

- በወረዳው ከባድ ረሃብ ነው ያለው። የዕርዳታ እህል ለማግኘት ምዝገባ አለ። ግን በስንት አንዴ የምግብ ድጋፍ ቢገኝም የተወሰነ እንጂ የሰውን ሕይወት ሊያተርፍ የሚችል ነገር አይገኝም።

- በጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙት 4 ቀበሌዎች ትምህርት ተቋርጧል። በተቀሩት የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸው ባሉት አራቱ ደግሞ ሕፃናት #በኤርትራ_ካሪኩለም እንዲማሩ እየተደረገ ነው።

- ከጦርነቱ በፊት የብሔረሰቡ ቁጥር 32 ሺሕ ነበር። አሁን ኅብረተሰቡ በተለይ ወጣቱ ወደ ስደት እየሄደና ብሔረሰቡም በተደራረቡበት ችግሮች ምክንያት ቁጥሩ እየተመናመነ እየጠፋ ነው።

የኢሮብ ወረዳ አስታዳዳሪ ኢያሱ ምስግና ምን አሉ ?

* ወደ 60 በመቶ የሚሆነው የብሔረሰቡ ግዛት በኤርትራ ሠራዊት ሥር ነው። ሁለቱን ቀበሌዎች ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯቸው ይገኛል። የተቀሩት ሁለቱ ውስጥ ደግሞ በከፊል ሰፍሮ ይገኛል።

* ከዓዲግራት ወደ ኢሮብ የሚወስደው መንገድ በኤርትራ ሠራዊት ወድሟል። አሁንም በሠራዊቱ ተዘግቶ ይገኛል። ይህ ዋና መንገድ በመዘጋቱ ትራንስፖርት ችግር ነው። ቀበሌዎችን ውስጥ ለውስጥ ለማገናኘት ከጦርነቱ አራት ዓመታት በፊት ቀድሞ ግንባታቸው ተጀምሮ ባልተጠናቀቁ መስመሮች ነበር የሚኬደው አሁን ይኼም አስቸጋሪ እየሆነ ነው።

* ኢሮብ ወረዳ ዘንድሮ ከባድ ድርቅ ያጋጠመው አጋጥሞታል። እስካሁን ድረስም ምንም ዓይነት ዝናብ አልተገኘም። የምግብና የውኃ እጥረት በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

* ዕርዳታ በሰብዓዊ ድርጅቶችና አልፎ አልፎ በመንግሥት ይቀርብ ነበር። በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት የምግብ ዕርዳታ ካቀረበ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖታል። በወቅቱ ድጋፉ ለአራት ሺሕ ሰዎች ነበር የቀረበው።

* መንግሥትም አልፎ አልፎ የሚልክልን የአደጋ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ነበር፡፡ እሱም ከጊዜው ቆይታ አንፃርና ከሕዝቡ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን አልነበረም።

* የመድኃኒት እጥረት ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። በረሃብ አደጋ ውስጥ ወድቀው ያሉ ብዙ ታማሚዎች የመድኃኒት ዕጦቱ ተደምሮ ሕይወታቸውን እያሳጣቸው ነው።

* የኢሮብ ብሔረሰብ የድርቅ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን እንደ ብሔረሰብ እየጠፋ ነው። ቋንቋው፣ ባህሉና ወጉ ተጠብቆ በራሱ አካባቢ መኖር ሲገባው በስደት፣ በረሃብ፣ በድርቅና በጠላት ተበታትኖ እንዳይጠፋ ዓለም አቀፍ ሕግጋት መተግበር አለባቸው፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም መከበር አለበት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሪፖርተር ጋዜጣ መውሰዱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ትግራይ #ኢሮብ

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ በኃላም ቢሆን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የኢትዮጵያ፣ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ 23 ት/ ቤቶች በኤርትራ ወታደሮች ስር ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ተነፃፃሪ የሆነ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ባለባቸው አከባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በቀጣዩ ሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመዘጋጀት ይገኛሉ።

ለፈተናው እየተዘጋጁ ያሉት ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳደር ስር ያሉ ናቸው።

በወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚታወቁ እና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት አንድ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙባቸው 23 ትምህርት ቤቶች ከ3 ዓመት በላይ #በኤርትራ_ወታደሮች_ቁጥጥር_ስር እንደሚገኙ በኢሮብ ወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤት ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶቹ  መምህራን እና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል። 
 
ቃላቸውን የሰጡ ተማሪዎች ፦
- ጦርነቱ ብዙ ነገሮች እንዳሳጣቸው
- አሁን በወረዳቸው ትምህርት ቤት የኢንተርኔት አቅርቦት ጨርሶ እንደሌለ
- ውሃ ፣ መብራት ፣ ትራንስፓርት የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንደሌለ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ በቴክኖሎጂ ታግዞ ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር ተፈኳኳሪ ለመሆን እንደሚከብድም ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ግን አሁን ላይ የተገኘው ዕድል እንዳያመልጥ ለመፈተን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

መምህራን በበኩላቸው ፥ በወረዳው ያሉት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የክልሉና የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እገዛ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ነፃ ወጥተው የዘወትር አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

በወረዳው በጦርነት ምክንያት የትምህርት ሴክተር ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የወደመ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ምንም የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በሌለበት ለመፈተን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የእገዛ እጃቸው እንዲዘረጉ የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን መረጃ የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማደረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia