TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሩዋንዳ ዛሬ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) 30ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው። በ1994 እ.አ.አ ሩዋንዳ ውስጥ በቱትሲ ጎሣ ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከደረሱት አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋዎች አንዱ ነው። በ100 ቀናት ገደማ ውስጥ ብቻ ከ800,000 እስከ 1,000,000 የሚሆኑ ሰዎች እንዳለቁ ይገመታል። ከተገደሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ቱትሲዎች ናቸው፤ ሆኖም…
በሩዋንዳው #ጄኖሳይድ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አደረገ ?

ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ባለቁበት የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ወቅት የዓለም መሪዎች ምንም እንኳን ስለ ዘር ጭፍጨፋው (ጄኖሳይድ) ቢያውቁም ጣልቃ አልገቡም ነበር።

ለረጅም ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ' ጄኖሳይድ ' የሚለውን ቃል ከመጠቀም ተቆጥቦ ነበር ፤ ይህም #በአሜሪካ ጫና እንደሆነ ይነገራል።

አሜሪካም ወታደሮቿን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ያልፈለገች ሀገር ናት።

የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ሃላፊ ባን ኪሙን በ20ኛው ዓመት የዘር ጭፍጨፋው መታሰቢያ ወቅት " ድርጅቱ የዘር ማጥፋት ወንጀሉ  መከላከል ባለመቻሉ አሁንም ድረስ ያፍራል " ሲሉ ተናግረው ነበር።

ጭፍጨፋው ከመጀመሩ በፊት (እኤአ በ1994 መጀመሪያ ላይ) ተመድ ወደ ሩዋንዳ የላከው ኃይል UNAMIR አዛዥ ጄኔራል ሮሜዮ ዳላይር ስለ ግድያው / ጭፍጨፋው በቂ የደህንነት መረጃ ደርሶት ነበር። በሁቱዎቹ የተከማቸ ሚስጥራዊ የጦር መሳሪያ (እንደ ገጀራዎች) እንዳለ አውቆ ነበር። 

ከጥር እስከ መጋቢት ወር ድረስ 5 መልዕክቶችን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ልከዋል።

በዚህም በሩዋንዳ ያላቸው ተልእኳቸው እንዲሰፋ ሁቱዎች ያከማቿቸው መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እና የተመድ የሰራዊት ቁጥር እንዲጨምር ቢጠይቁም እዛ ያሉት ሰዎች ግን ማስጠንቀቂያዎቹን ችለ ብለው ትተዋቸዋል።

ግድያው ሲጀመር ተመድ እና የቤልጂየም መንግሥት የUNAMIR ሰላም አስከባሪዎችን አስወጡ።

የፈረንሳይ እና የቤልጂየም ሰላም አስከባሪዎች ቱትሲዎችን ለመርዳት ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረት በተሽከርካሪ የነበሩ የሌላ ሀገር ዜጎችን አስወጥተዋል።

ሳይወጡ የቀሩና ትንሽ የተረፉ የተመድ ኃይሎች በኪጋሊ ውስጥ እንደ " ሆቴል ዴ ሚሌ ኮሊንስ " እና " አማሆሮ ስታዲየም " ባሉ ቦታዎች የተሸሸጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጥበቃ አድርገዋል።

በአንድ አጋጣሚ ግን በኪጋሊ ኢኮሌ ቴክኒክ ኦፊሴሌ (የቴክኒክ ት/ቤት) የተጠለሉ 2,000 ሰዎችን የሚጠብቁ ወታደሮች ቦታቸውን የውጭ ዜጎችን ለማስወጣት ሲሉ ቦታቸውን ለወቀው ሲወጡ በትምህርት ቤቱ እልቂት / ጭፍጨፋ ተፈፅሟል።

ቱትሲዎችን ለማጥፋት እቅድ እንዳለው እያወቀች የፕሬዝዳንት ሃብያሪማናን መንግሥት ስታስታጥቅ የከረመችው ፈረንሳይ በግድያዎቹ የመጀመሪያ ቀናት ጭምር ከሁቱ መንግስት ጋር መተባበሯን ቀጥላ ነበር። RPFንም ለፍራንስ አፍሪካ ግንኙነት ጠንቅ ነው ብላ ታስብ ነበር።

በመጨረሻ ተመድ ግንቦት 17/1994 በሩዋንዳ ላይ የጦር መሳሪያ እገዳ ጣለ፣ UNAMIRን ለማጠናከር ውሳኔ አሳለፈ። እስከ ሰኔ ድረስ ግን አዲስ ወታደሮች ሩዋንዳ መግባት አልጀመሩም ነበር።

ይህ ሁሉ እስኪሆን አብዛኛው ግድያ ተፈጽሞ ነበር።

የምዕራቡ ዓለም የሚዲያዎችም ጭፍጨፋውን “ የእርስ በርስ ” ወይም “ የጎሳ ” ጦርነት በማለት ነው ሲገልጹ የቆዩት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
Al Jazeera

@tikvahethiopia