TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ችሎት

3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መሰረተ።

ዐቃቤ ህግ የ #አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጁን ተገን በማድረግ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል የፈፀሙ 3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መስርቷል።

ክስ የተመሰረተባቸው ፦
1ኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ተሰማ መለሰ በዲስፕሊን ጥፋት ከስራ የተሰናበተ
2ኛ ተከሳሽ ዋ/ሳጅን ፈንቴ ፈይሳ የፖሊስ መኪና ሾፌር
3ኛ ተከሳሽ ረ/ሳጅን ተስፋዬ በላይ የፖሊስ መኪና ተወርዋሪ ናቸው።

ተከሳሾች ምንድነው የፈፀሙት ?

ተከሳሾቹ በጥቅም በመመሳጠር ህዳር 03 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ12፡30 - 1፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 0228 በሆነችና 2ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክራት የፖሊስ መኪና የግል ተበዳይ አቶ ዘሪሁን ሀይሉ ወደሚኖርበት መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ።

1ኛ ተከሳሽ የፖሊስ አባል በመምሰል 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ የፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወን እና የግል ተበዳይን የመያዝ የስራ ድርሻ ሳይኖራቸው እና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው 2ኛ ተከሳሽ የግል ተበዳይን “በወቅታዊ ጉዳይ ትፈለጋለህ” በማለት 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ወደ ግል ተበዳይ መኪና በመግባት 1ኛ ተከሳሽ ተበዳይን ያለምንም ጥያቄ 6 ወር ትታሰራለህ እኛ እንድንተባበርህ ከፈለክ 200 ሺ ብር ስጠን ብለው ይጠይቁታል።

በመጨረሻም 120 ሺ ብር እንዲሰጣቸው ተስማምተው 60 ሺ ብሩን 1ኛ ተከሳሽ ወደሚጠቀምበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ገቢ እንዲያርግ በማድረግ እና 10 ሺህ ብር በጥሬው በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ተቀብለው ከተከፋፈሉ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ሊቀበሉ ሲሉ በማህበረሰቡ እና በህግ አስከባሪ አካላት ተይዘዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። 

ዐቃቤ ህግ ከዚህ በፊት ታህሳስ 4/2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ወንጀል በፈፀሙ አራት የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ክስ መስርቶ ተከሳሾች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ መልስ በመስጠት የችሎቱን ብይን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Ministry-of-Justice-12-29