TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሸዋሮቢት‼️

በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በእናትና ልጅ ላይ #አሰቃቂ_ግድያ ፈጽሟል በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብን አሳልፋችሁ ስጡን በሚል የከተማዋ ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያውን አጨናንቀዋል፡፡ #ፖሊስ በበኩሉ ድርጊቱን #አጣርቼ ለፍርድ እስካቀርብ ድረስ ታገሱን በሚል #የማረጋጋት ሥራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ነዋሪዎቹ በሟቾቹ ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ፍርዱን #እኛው መስጠት አለብን በማለት ፖሊስ ጣቢያውን ከበው እንዲሁም ዋናውን የአስፋልት መንገድ በመዝጋትና ጎማ በማቃጠል ድምጻቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች እንደሚሉት ከሆነ ትላንት ምሽት 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰናይት ት/ቤት ጀርባ ከምሽቱ በግምት 1፡30 አካባቢ በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሉ 1 እናትና ከአንዲት ሴት ልጇ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው በመገኘታቸው ነው ነዋሪው ቁጣውን በተለያዩ አግባቦች በመግለፅ ላይ ያለው፡፡

የከተማው የጸጥታ አካላት የተጎጂ ቤተሰቦችን እና የከተማውን ማህበረሰብ በማረጋጋት ላይ ነው።

Via Shewa Robit City Administration Kentiba office
@tsegabwolde @tikvahethiopia