የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን "ሪፖርተር ጋዜጣ" ይቅርታ ይጠይቀኝ/የእርማት ማስተካከያም ያድርግ አለ።
ኮርፖሬሽኑ፥ 'ሪፖርተር ጋዜጣ' ይቅርታ ይጠይቀኝ/የእርማት ማስተካከያ ያድርግ ያለው ጋዜጣው በቀን ሰኔ 2/2013 ዓ.ም ባወጣው ህትመት "የከተማ አስተዳደሩ የ20/80 እና የ40/60 የጋራ ቤት እጣ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ" በሚል ያወጣው ዘገባ ከእውነት የራቀ በመሆኑ ነው።
ኮርፖሬሽኑ፥ "የ20/80 እና የ40/60 የጋራ ቤት እጣ ሊያወጣ ነው" ተብሎ የተዘገበው ዘገባ የሚመለከታቸው አካላት ያልሰጡት መረጃ ነው/ከእውነት የራቀ ነው ብሏል።
ጋዜጣው ከተማ አስተዳደሩን ሆነ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዲሁም የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለተሰራጫው ያልተረጋገጠ ዘገባ ይቅርታ በመጠየቅ ማስተባበያ እንዲያወጣ ኮርፖሬሽኑ አሳስቧል።
የሪፖርተር ዜና የመረጃ ምንጭ ማን እንደሆነ እና ማን እንደሰጠው የት እንደተሰጠ ያልገለፀ በመሆኑና የኮርፖሬሽኑ አመራሮችም ምንም አይነት መረጃ እንዳልሰጡ በመግለፃቸው ከታመኑ ምንጮቻችን አግኝተናል ብሎ መዘገቡ አግባብ ስላልሆነ የማስተካከያ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ብሏል ኮርፖሬሽኑ።
በተጨማሪ ፥ እስከ ዛሬ ድረስ የቤቶች ልማት ኮረፖሬሽን በቁጥር በ10 ሺዎች የሚጠቀሱ ቤቶች ሲያስተላልፍ እንጂ የሚታወቀው ከ2 ሺህ ቤቶች በላይ ተብሎ የተጠቀሰው ከትክክለኛ ምንጭ ያልተነገረ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብሎታል።
ሪፖርተር ጋዜጣ ለተዘገበው ዘገባ ማስተባበያ በ10 ቀን ማስተባበያው በጋዜጣው እንዲታተም እንዲያድረግና በተሰራጨው ዘገባ የተደናበረውን ሕዝብ የማረጋጋት ስራ እንዲሰራ ተጠይቋል።
ጋዜጣው ይህን ሳያደርግ ቀርቶ ማስተባበያውን ካላወጣ ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ እንደሚገደድ ኮርፖሬሽኑ ለጋዜጣው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14/2013 ድምጽ መስጠት የማይቻልባቸውና ምርጫው ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ የተወሰነባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም መግለጹ የሚታወስ ነው።
ከዚህ ውስጥ ለምን ያህል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቀመጫዎች እና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ምርጫው እንደማይካሄድ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዝርዝር አቅርቧል።
በዚህም፦
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - ለ4 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ13 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በኦሮሚያ ክልል - ለ7 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በአማራ ክልል - ለ10 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ9 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በደ/ብ/ብ/ህ ክልል - ለ16 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ22 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በሐረሪ ክልል - ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ3 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• በአፋር ክልል - ለ2 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ7 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ፤
• ሶማሌ ክልል - ለ23 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዲሁም ለ72 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ በሰኔ 14 ምርጫ የማይካሄድባቸው ናቸው።
በአጠቃላይ ሰኔ 14 በ64 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ላይ ምርጫ #የማይካሄድ ሲሆን በእነዚህ አከባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ ይሆናል።
* ዝርዝር ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል።
#TikvahFamily

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,399 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 134 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 274,480 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 7 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,257 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,954,623 ደርሰዋል።

#DrLiaTadesse
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት እና በቀጣይ በሚሰጠው 2ኛ ዙር ክትባት መርሃ ግብር ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በህንድ ሃገር የተከሰተውን የኮቪድ-19 የወረርሺኝ መስፋፋት ተከትሎ በተለያዩ ሃገራት የክትባት እጥረት ማጋጠሙን በመግለጫቸው ላይ አስታውሰዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሀገራችንም #የክትባት_እጥረት ያጋጣመ ሲሆን ይህን እጥረት ለመፍታት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን ተጨማሪ ክትባቶችን ከለጋሽ አገሮችና እና ክትባትን ከሚያመርቱ ተቋማት ለማግኝት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
እየተሰራ ባለው ስራ በቅርቡ በተለያየ መጠን ተጨማሪ ክትባት መምጣት እንደሚጀምር ከኮቫክስ የዓለም አቀፍ ጥምረት የተገለጸ መሆኑ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሰረት ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙር ለወሰዱ እና ክትባቱን ከወሰዱ ሶስት ወራት የሞላቸው የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች መስጠት እንደሚጀምር አሳውቀዋል።
2ኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት እንደ መጀመርያው ዙር የክትባት አሰጣጥ መርሃ ግብር ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ይሰጣል ብለዋል።
መረጃው የጤና ሚኒስቴር ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አህመድ ቀጣን እና በሳኡዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቆንስላ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሚም አል ዶሰሪ ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው የነበረው ፥ በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያ ግንኙነት፣ የጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሳኡዲ አረቢያ…
በሳዑዲ ዓረቢያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ መንግሥት የፀጥታ ኃይላት ከፍተኛ ወከባ፣ እስር እና ዝርፊያ እየደረሰባቸው ነው።
የሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታ ኃይላት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ቤቶች እየዘረፉ ለእስር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን የችግሩ ሰለባ ኢትዮጵያውያን ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
ቃላቸውን ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል ለ8 ዓመት በጅዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ካልድ ሲራጅ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳላቸው እየተናገሩ ከባለቤታቸው እና ሁለት ልጆቻቸው ጋር ለ3 ቀን ታስረው መፈታታቸውን ገልጸዋል።
አቶ ካሊድ፥"ቀጥታ መጡ፤ ልክ ከዝሁር በኋላ ከምሳ ሰአት በኋላ መጡ፤ ሰበሩ። ኢቃማ [ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ] አለን እያልናቸው እንኳን ሊሰሙን አልቻሉም፤...ተንጋግተው መጥተው ነው ቤቱን ሰብረው የገቡት" ብለዋል።
ከትናንትና ወዲያ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ የጸጥታ ኃይላቱ "ሀበሻ" የሚሏቸውን ኢትዮጵያውያን ማሰርና ቤቶቻቸውን መስበር መቀጠላቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል።
አቶ አሕመድ ሁሴን የተባሉ ነዋሪ ደግሞ ወከባ፣እስርና ዝርፊያው መቀጠሉን ተናግረዋል።
«ተደበደበ፤ኅብረተሰቡ ንብረቱን ተወረሰ። ምነው ሂዱ ከተባልን ንብረታችንን እንኳን ይዘን ብንሄድ ? እንኳን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የመኖሪያ ፈቃድ ያለንም ብንሆን ወደ ሀገራችሁ ግቡ ብንባል በሰላም ብንገባ ምንአለበት እና ኅብረተሰቡ ተዘረፈ እያልን አሁንም ኤምባሲ እየደወልን እየተናገርን ነው" ብለዋል።
አክለውም፥ "ሰሞኑን በሐበሻ ላይ የሚሠራው ሥራ ያለአግባብ ነው፤ ይመጣሉ ፤ ቤት ይሰብራሉ፤ሰብረው ሰዉን ይወስዳሉ ፤ ከዚያ ተከትሎ ወጣቱ ተከትሎ እየገባ ኅብረተሰቡ ተዘርፏል" ሲሉ ገልፀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Saudi-Arabia-06-15
#ዶቼቨለ

የአረብ ሊግ ስብሰባ እና የኢትዮጵያ ምላሽ :
የዐረብ ሊግ የተመድ ጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስንብሰባ እንዲያደርግ ትላንት ባደረገው ስበባ ጠይቋል።
የሊጉ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ሰብሰባ የሁሉንም አካላት ፍላጎት የሚያሳካ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት አንስተዋል።
የዐረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር አዝጋሚ ነው ሲል ገልጾታል።
ሚኒስትሮቹ በኳታር መዲና ዶኃ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት ስር እየተካሄደ ያለው ድርድር አዝጋሚ በመሆኑ የጸጥታው ም/ቤት በግድቡ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የሊጉ ዋና ፀሀፊ አህመድ አብዱል ጌት እንዳሉት የግብፅና የሱዳን የውሃ ደህንነት ጉዳይ የዐረብ ሀገራት ደህንነት አካል መሆኑን መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።
የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የዐረብ ሊግ ለሱዳን እና ለግብፅ ድጋፍ እንዳለውም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አሳውቃለች።
የአረብ ሊግ የግብጽ እና የሱዳንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ላይ ሳይመሰረት በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ገንቢ ሚና መጫወት ሲገባው ሚዛናዊነት የጎደለው እና ወደ አንድ ወገን ያደለ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጻለች።
ውሳኔው በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብርና በዘላቂነት ለመጠቅም የሚያስችል መንገድ አለመሆኑንም አሳውቃለች።
የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም እና የኢትዮጵያን ነባር አቋም በሚገባ ሊያውቁ ይገባቸዋልም ብላለች።
#ኢብኮ #አልዓይን

#Attention
የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት:-
- አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠማችሁ በስተቀር አሁን በሳዑዲ ያለው የአፈሳና ፍተሻ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ሁሉም ዜጎች ወደ ቆንስላ ጽ\ቤቱ አካባቢ እንዳትሄዱ።
- የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሚወስዱት እርምጃም በተለይ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ኖሯቸው በህግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኃይል አጠቃቀም ምክንያት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያጋጠማቸው የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው / ዘረፋ ያጋጠማቸው ዜጎች ተጨባጭ ማስረጃ በመያዝ ለቆንስላ ጽ\ቤቱ መጠቆም ይችላሉ። መረጃውን መሰረት በማድረግ የቆንስላ ጽ\ቤቱ ከሳዑዲ ወገን ጋር እነጋገራለሁ ብሏል።
-የመኖርያ ፈቃዳቸው ተቃጥሎ በራሳቸው ወጪ ወደአገር ለመግባት አሻራ ለመስጠት ሲጠባበቁ የነበሩ ዜጎች ከትላንት በስቲያ ጀምሮ የሳዑዲ ወገን የአሻራ አገልግሎት መስጠቱን ያቋረጠ በመሆኑ ከአገሪቱ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር አገልግሎቱ ዳግም እስኪጀመር ድረስ እንዲታገሱ።
- ዜጎች በቆንስላ ጽ\ቤት አካባቢ ጨምሮ በየትኛውም አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የሳዑዲ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ባወጣው ደንብ መሰረት የራሳቸውን እና የሌላውን ጤና ለመጠበቅ / ደንቡን ካለማክበር ከሚደርስ ቅጣት ለመዳን ሙሉ አፍና አፍንጫችሁን በማስክ ሸፍናችሁ እንድትንቀሳቀሱ አደራ ተብሏል።
አሁንም #ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንድትቀጥሉ በጅዳ የሚገኘው ቆንስላ ጽ\ቤት የጥንቃቄ መልዕክቱን አስተላልፏል።
(የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፣ ጅዳ)

የጥሞና ወቅት ምንድነው ?
የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን 4 ቀናት ያካትታል፡፡
በጥሞና ወቅት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ኃላፊነቶች አሉ፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች መተግበር ያለባቸው ፦
• የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከ4 ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡
• የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው 4 ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን #በጥብቅ የተከለከለ ነው)
• የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡
• ብሄራዊ የምረጫ ቦርድ የሚያወጣቸውን መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡
መገናኛ ብዙሀን ተቋማት መተግበር ያለባቸው ፦
• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪ የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡
• የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ሀላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትን እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡
(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
VIDEO : የእስራኤል የአየር ጥቃት በጋዛ 👆
የአስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ የሀማስ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘሩን አሳወቀ።
ጦሩ ጥቃት የፈፀመው ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ተቀጣጣይ ነገሮችን ይዘው ለተለቀቁ ፊኛዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል።
የአስራኤል ጦር "ከጋዛ ሰርጥ በቀጠለው የሽብር ተግባር ምክንያት የጦርነት መጀመርን ጨምሮ ለሁሉም አይነት ክስተቶች ዝግጁ መሆኑን" ገልጿል።
የአስራኤል የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት እንዳሳወቀው ትላንት ጥዋት ፥ በርካታ ፊኛዎች ከጋዛ ወደ አስራኤል ተለቀው በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቢያንስ 20 ቦታ የእሳት ቃጠሎ አስነስተዋል።
እስራኤል በፈፀመችው ጥቃት ዛሬ ከንጋት በፊት ጋዛ ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።
ባለፈው ግንቦት ወር ለ11 ቀናት በሁለቱ ወገኖች በኩል የተካሄደው ውጊያ በተኩስ አቁም ከተጠናቀቀ በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያው ግጭት ነው።
የአሁኑ ጥቃት የተፈጸመው ማክሰኞ በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ውስጥ አክራሪ አይሁዶች ሰልፍ ካካሄዱ በኋላ ጋዛን ከሚያስተዳድረው ታጣቂ ቡድን ሀማስ በኩል ማስፈራሪያ መሰንዘሩን ተከትሎ ነው።
የሀማስ ቃል አቀባይ በትዊተር ገጹ የእስራኤልን ጥቃት በተመለከተ ባሰፈረው መልዕክት ፍልስጤማውያን "መብታቸውን እና ኢየሩሳሌም ውስጥ ያሉትን ቅዱስ ቦታዎችን ለመከላከል የጀግንነት ተጋድሏቸውን ይቀጥላሉ" ብሏል።
ዛሬ እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው የአየር ድብደባ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሆነ ወዲያውኑ የታወቀ ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

• በደቡብ ክልል በቢጣ ጊሻ እንዲሁም በማሻ የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ምርጫ አይካሄድም፤ ምርጫው ወደ ጳጉሜ 1 ተዘዋውሯል።
• ከምርጫ ጋር በተገናኘ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6 የፓለቲካ ፖርቲዎች ጋር በፍርድ ቤት ክርክር እያደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሁን ላይ በፍርድ ቤት ከፖርቲዎች ጋር እየተከራከረባቸው የሚገኙ 6 የክስ ሂደቶች መኖራቸውን አስታውቋል።
ቦርዱ በፍርድ ቤት በተያዙ ጉዳዮችና ክርክሮች ምክንያት የሐረሪ ክልል ምርጫ(ሙሉ በሙሉ)፤ በደቡብ ክልል በቢጣ ጊሻና በማሻ የምርጫ ክልሎች የምርጫ ጊዜያቸውን ከሰኔ 14 ወደ ጳጉሜ 1 ያዛወራቸው ናቸው።
ከእነዚህ መካከል የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ክስ አንዱ ነው። ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በደቡብ ክልል ስር ለመወዳደር ፍቃድ ያገኘ ክልላዊ ፓርቲ ሲሆን ዋና ጽ/ቤቱ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ላይ ይገኛል። ፓርቲው ከሌላ ዞን የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች ይሰረዝልኝ ሲል ቦርዱን ከሷል።
ፓርቲው ቅሬታ ያቀረበባቸው ከከፋ ዞን ሳይለም ወረዳ እና ከቀድሞ ቤንች ማጂ ዞን ከአሁኑ ቤች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ወደ ሸካ ዞን ማሻና ቴፒ የተጨመሩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲቀየሩ ነው የጠየቀው።
ቦርዱ ለፓርቲው በሰጠው ምላሽ በዚህ ረገድ ተመሳሳይ ጥያቄዎች መኖሩን ጠቅሶ የህዝብና ቤት ቆጠራ ሳይደረግ የምርጫ ክልል ማስተካከል እንደማይችል ገልጾ የ2013 ጠቅላላ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበረው ለውጥ ሳይደረግ እና የምርጫ ጣቢያዎችን ከአንዱ ወደ አንዱ ምርጫ ክልል ሳያሸጋሽግ በነበሩበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን አሳውቋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የከፍተኛ ፍርድ ቤት የቦርዱን ሀሳብ በማጽናት የምርጫ ጣቢያዎች በነበሩበት ሊቀጥሉ ይገባል ሲል በ8/7/2013 ውሳኔ አስተሏልፏል።
ያንብቡ telegra.ph/TIKVAH-06-16

የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ።
በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው በሙያቸው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እያገለገሉ የነበሩ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች በታጣቂዎች ተገደሉ።
#አሥራት_ሺካ እና #ሮቤል_ልደቱ የተባሉት ወጣት ኢንጂነሮች ትላንት ሰኔ 8/2013 ለሥራ ጉዳይ "አማሮ ልዩ ወረዳ" ሲጓዙ "ጀሎ" በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል።
ሁለቱም ወጣት ኢንጂነሮች ባላቸው እውቀት ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት።
የወጣቶቹን ግድያ የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቀናል ብሏል።
በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን ባወጣው የሀዘን መግለጫ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
ባልስልጣኑ 'ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት' ብሎ ከመግለፅ በዘለለ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስለግድያው ፣ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ተያያዥ መረጃ እንዲሰጠን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ኢትዮጵያ 381 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረብያ መለሰች።
ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት 381 ዜጎቿን ከሳኡዲ አረብያ ፤ ጂዳ ከተማ በማስወጣት ወደ አገራቸው መልሳለች።
ዜጎቻችን ከጄዳ ሹሜሲ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ነው ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው።
ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን በተጠናከረ ዘመቻ ወደ ሀገራቸው የመመለሱን ተግባር አሁንም ቀጥላለች።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ነው።

#Update
እናታችን ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በኮቪድ - 19 ተይዘው በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና ማግኘት ከጀመሩ ሁለት (2) ሳምንት ሊሆናቸው ነው።
እዳዬ አሁንም በሆስፒታሉ ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በበጎ አድራጎት ስራቸው በሀገራችን ባሻገር በዓለምም በጣም የሚታወቁ የደግነት ምልክት ፤ የእናትነት ተምሳሌት ናቸው፡፡
#AGOHELMA