#Update
እናታችን ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በኮቪድ-19 ተይዘው በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና ላይ እንዳሉ መገለጹ ይታወሳል።
በርካታ የቲክቫህ ቤተሰቦች አሁን ጤናቸው በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል፥ ጠይቁልን ባላችሁን መሰረት የጤናቸውን ሁኔታ ከማህበሩ ጠይቀናል።
ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና እናታችን አሁንም በሆስፒታሉ ጥሩ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተገለጸልን ሲሆን አሁንም ድረስ ኦክስጅን ተገጥሞላቸው እንደሚገኙ ተረድተናል።
ሆስፒታል ከገቡበት ቀናት ጋር ሲነጻጸር አሁን ላይ ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብለናል። አሁንም ሁሉም በየእምነቱ በጸሎት እንዲያስባቸው ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia

#GERD
ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ውል ማድረግ እንደምትፈልግ አስታወቀች።
ሱዳን ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ካካሄደችም በኋላም ቢሆን ድርድሩን ለማስቀጠል የሚጠይቅ መሆኑን የሀገሪቱ የውሃ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በዚህም ሱዳን ቀደም ሲል ከስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ መፈራረምን ጨምሮ ቅድመ ሁኔታውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚደረግ ጊዜያዊ ስምምነት እንደምትቀበል የውሃ ሚንስትሩ ያሴር አባስ ዛሬ ካርቱም ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በህዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል እና ድርድሮቹ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲከናወን የሱዳን ፍላጎት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ሦስቱ ሃገራት አስቀድሞ በአብዛኞቹ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ «ከመግባባት ደርሰዋል» ነገር ግን ከአንዳች አስገዳጅ ስምምነት አልተደረሰም ሲሉ ሚንስትሩ አክለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ከፊታችን ባሉት የክረምት ወራት ለማከናወን መዘጋጀቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ፣ግብጽ እና ሱዳን በአፍሪቃ ህብረት አደራዳሪነት ባለፈው የሚያዝያ ወር በኪንሻሳ ካደረጉት እና ያለስምምነት ከተለያዩበት ድርድር ወዲህ አልተገናኙም።
(ዶቼ ቨለ)

በልደታ ክ/ከተማ ቦንብ ፈንድቶ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።
በፍንዳታው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ለማወቅ ምርመራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ሰኔ 7ቀን 2013 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዮ ቦታው ዮርዳኖስ ሆስፒታል መግቢያ ፊት ለፊት ለጊዜው ምንነቱ ባልተረጋገጠ ምክንያት ከቀኑ 8፤30 አካባቢ ኤም 7.5 የሚባል ፕላስቲክ ቦንብ ፈንድቶ ቦንቡን ይዞት በነበረው ግለሰብ የግራ እጁ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶበታል፡፡
ከፖሊስ መምሪያው በተገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በአካባቢው በጎዳና ላይ ኑሮን በማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ብረታ ብረቶችን በመልቀም የሚተዳደርና ከሶስት ቀን በፊት ስብርባሪ ብረቶችን ሲለቅም ቦንቡን እንዳገኘው የሰጠውን ቃል ዋቢ አድርጎ ፖሊስ ገልጿል፡፡
ግለሰቡ ለህክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተላከ ሲሆን በፍንዳታው ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ለማወቅ ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን እና የምርመራው ውጤቱን ወደፊት እንደሚያሳውቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከተገቢው ቦታ ለማግኘት የሚያደርጋቸው ጥረቶች የሚበረታቱ ሲሆን አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ከጸጥታ አካላት ጋር ያለውን ተባባሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

TIKVAH-ETHIOPIA
#ምርጫ2013 “... ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል” - አቶ ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ። ይህን የገለፁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው። የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል…
#Update
ዛሬ ከፌዴራልና ከክልል የደህንነትና ፀጥታ ተቋማት የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት በሀገሪቱ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር አድርጎ ነበር።
በተለያዩ ርዕሰጉዳዮች የተካሄደውን ምክከር ተከትሎም የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰባቸውን የሚከተሉትን ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ወደ ተለያዩ የምርጫ ክልሎች ከዛሬ ሰኞ ምሽት ጀምሮ መላክ እንደሚጀመር ገለፀ።
ይህ የተገለፀው የቦርዱ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪር ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።
ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ፥ በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው የድምጽ መስጠት ተግባር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ወደ የምርጫ ክልሎች ምሽት ጀምሮ መላክ ይጀምራሉ ብለዋል።
በድምፅ መስጫው ዕለት (ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም) ምርጫ ጣቢዎች ማለዳ 12 ሰዓት ተከፍተው ምሽት 12 ሰዓት እንደሚዘጉ ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎ ቆጠራ እንደሚካሄዳል፤ የየምርጫ ጣቢያዎቹ ውጤትም ይገለፃል፤ በማስከተለም የአገር አቀፍ ውጤት በሕጉ መሠረት ይፋ እንደሚሆንም ገልፀዋል።
ሰኞ ስራ ይኖራል ?
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ዕለት፣ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም፣ ሥራ ይኖራል ብሎ እንደማይጠብቅ ገልጿል።
ወ/ሪት ሶሊያና ፥ በድምጽ መስጫ ዕለት ቦርዱ ሥራ እንዲኖር ፍላጎት የለውም ብለዋል።
የመንግሥት እና የግል ተቋማት ትበብር ማድረግ ሕጋዊ ግዴት መኖሩን አስታውሰው፤ ተቋማት ትብብር እንዲያደርጉ በይፋ ቦርዱ ጥያቄ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።
ወ/ሪት ሶሊያና ፥ "... ሥራ አይኖርም ብለን ነው የምናስበው። ይህ መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ እና ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ይረዳል። ይህ በረዥም ጊዜ የሚደረግ ስለሆነ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በዚህ ረገድ ይተባበሩናል ብለን እንጠብቃለን። በድምጽ መስጫ ዕለት ሥራ አይኖርም የሚለው ብቻ ነው የሚቀረው" ብለዋል።
መረጃው የቢቢሲ ነው።

#Update በሳዑዲ ዓረቢያ የህግ አስከባሪ አካላት ተይዘው የነበሩ ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ ተገፀ። የሳዑዲ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነ እና ዜጎችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰራጨቱ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ ከተለያዩ…
#Update
በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አህመድ ቀጣን እና በሳኡዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቆንስላ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሚም አል ዶሰሪ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይታቸው የነበረው ፥ በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያ ግንኙነት፣ የጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሳኡዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዙሪያ ነበር።
በውይይቱ ፥ በእስር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጉዳይ፣ የመኖሪያ ፈቃድ የተቃጠለባቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሳኡዲ አረቢያ ሲኖሩ የቆዩ ዜጎች በፈቃዳቸው ያለምንም ገንዘብ መቀጮና እስራት በፍላጎታቸው ወደ አገር በሚመለሱበት አግባብ ፣ ሰሞኑን እየተደረገ ባለው የፖሊስ አፈሳ እንዲሁም የዜጎች የሰብዓዊ መብት አያይዝ ሁኔታ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
ጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሳኡዲ አረቢያ መንግስት በከፍተኛ አመራሩ ዘንድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተመከረበት ጉዳይ ነው ተብሏል።
ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በመላው ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በትእግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሪያድ

#ምርጫ2013 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ወደ ተለያዩ የምርጫ ክልሎች ከዛሬ ሰኞ ምሽት ጀምሮ መላክ እንደሚጀመር ገለፀ። ይህ የተገለፀው የቦርዱ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪር ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው። ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ፥ በመጪው ሰኞ ለሚካሄደው የድምጽ መስጠት ተግባር አገልግሎት ላይ የሚውሉ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ወደ የምርጫ ክልሎች ምሽት ጀምሮ መላክ…
"..ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምርጫው ዕለቱ ዝግ ይሆናሉ" - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ
ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ባሰራጩት መልርክት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምርጫው ዕለት ዝግ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ፥ "በካርዳችን ዴሞክራሲን።፣ በእጃችን ችግኞችን። ድምጻችን ለመስጠት ሰኔ 14 ቀን በነቂስ እንውጣ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“አረንጓዴ ዐሻራችንን በማሳረፍ፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ የሚደረገውን ጥረት እንቀላቀል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በምርጫው ዕለት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ ይፋ አድርገዋል።
ይህንን ለማካካስም ቀጥሎ የሚመጣው ቅዳሜ የስራ ቀን እንደሚሆን አስታውቀዋል።

#ENCOM
33ተኛው የምስራቅ ናይል ሃገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት (ENCOM) ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በስብሰባው የናይል ተፋሰስን በጋራ ማልማት የሚቻልበት መንገድና እስካሁን በተፋሰሱ የተሰሩ ስራዎች የሚቃኙ ይሆናል።
የኢፌድሪ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የምክር ቤቱ(ENCOM) ሰብሳቢ ናቸው።
ይህንኑ ስብሰባ ለመታደም የሱዳንና የደቡብ ሱዳን የውሃ ሚንስትሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።
ግብጽ የዚህ ምክር ቤቱ አባል ብትሆንም በስብሰባው ሳትገኝ ቀርታለች።
መረጃው የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።

"..ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምርጫው ዕለቱ ዝግ ይሆናሉ" - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ባሰራጩት መልርክት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በምርጫው ዕለት ዝግ እንደሚሆኑ ገልፀዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ፥ "በካርዳችን ዴሞክራሲን።፣ በእጃችን ችግኞችን። ድምጻችን ለመስጠት ሰኔ 14 ቀን በነቂስ እንውጣ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።…
#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲከናወን መወሰኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት በእለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምጻቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሰረት ለመንግስታዊ እና ለማንኛውም መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።
በዚህም መሰረት ፦
- ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል ( ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) መንግስታዊ ተቋማት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ስራ ዝግ እንዲያደርጉ
- ዜጎች እለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በክልሎች (ከሃረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) እና በፌዴራል የሚገኙ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ
- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተእለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት..) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።
- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም ዜጎች ድምጽ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና እቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምጽ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ/ም

4G ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ተጀመረ።
የ4G LTE አድቫንስድ አገልግሎት ዛሬ በደቡብ ምዕራብ ሪጅን መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።
በሪጅኑ በተደረገው ማስፋፊያ ከ350 ሺህ በላይ ደንበኞቹ የLTE አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ጅማ ከተማ በነበረ ይፋዊ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ተናግረዋል።
አገልግሎቱን የሚያገኙ ከተሞች ፦
- ጅማ
- አጋሮ
- በደሌ
- ቦንጋ
- ኮይሻ
- መቱ
- ሚዛን
- ማሻ
- ቴፒ ናቸው።

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE) የሚዲያ ቁጥጥርና ዳሰሳ እንደሚሰራ አሳወቀ።
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE) ባቋቋመው የሚዲያ ታዛቢ ቡድን አማካኝነት በምርጫው ወቅት የሚዲያዎችን ዘገባ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
በአምስት ሀገር አቀፍ ቋንቋዎችና ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ቡድኑ 10 የቴሌቪዥን እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ ቁጥጥር ያደርጋል።
የሚዲያ ቁጥጥርና ዳሰሳ ሥራው በዋናነት በምርጫ ወቅት የመገናኛ በብዙኀን ሚና ምንድን ነው የሚለውን ለመመልከት እንደሆነና ይህንን የሚገልጽ ሪፖርት ለማውጣት ዓላማ ያደረገ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ከዚህ ቀደም በምርጫ ወቅት የሚዲያዎችን አስተዋፅኦ በተደራጀ መልኩ የሚታዘብ የሲቪክ ማኅበር አልነበረም፥ አሁን ላይ ግን የሀገር ውስጥና የውጪ ሚዲያዎችን ተሳትፎ የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው።
በ The Hub ሆቴል ያለው ይህ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ቡድንና የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በተለዩ ሰዓቶች የሚተላለፉ 10 የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎችን ይዘቶችን ለ6 ወር ይዞ ይቆያል ተብሏል። አብዛኞቹ መንግስታዊ መሰረት ያላቸው ጣቢያዎች ናቸው።
የግልና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የውጭ ሚዲያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ምርጫን መሰረት ያደረገ ሥራቸው የዳሰሳ ሥራ የሚሰራባቸው ይሆናል፥ ይህም በረፖርቱ የሚካተት ይሆናል ነው የተባለው።

#ENCOM 33ተኛው የምስራቅ ናይል ሃገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት (ENCOM) ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በስብሰባው የናይል ተፋሰስን በጋራ ማልማት የሚቻልበት መንገድና እስካሁን በተፋሰሱ የተሰሩ ስራዎች የሚቃኙ ይሆናል። የኢፌድሪ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የምክር ቤቱ(ENCOM) ሰብሳቢ ናቸው። ይህንኑ ስብሰባ ለመታደም የሱዳንና የደቡብ ሱዳን የውሃ…
#Update
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ 33ተኛው የምስራቅ ናይል ሃገራት የሚንስትሮች ምክር ቤት (ENCOM) ስብሰባ እየተካሄደ ነው።
ከስብሰባው ጎን ለጎን የሱዳንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከሰሞኑን ግብፅ እና ሱዳን ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን በማስመልከት “ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ባቀደችው ልክ ሳታካሂድ ክረምቱ ስለሚገባ ግድቡ የተባለውን ያህል ውሃ መያዝ አይችልም” ሲሉ የሰጡትን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፥ ግድቡ በአሁኑ ክረምት “የግድ የተባለውን የውሃ መጠን” ማለትም 13.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይይዛል ብለዋል፡፡ ይህም ከተሳካ ግድቡ ከመጀመሪያው ዙር ጋር ተደምሮ 18 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ይይዛል ማለት ነው፡፡ “ሁለቱ ተርባይኖችም ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
የሱዳን ውሃ እና መስኖ ሚንስትር የሆኑት ፕሮፌሰር ያሲር አባስ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባቷን እና ውሃውን መጠቀሟን ሱዳን እንደማትቃወም ገልፀዋል፥ ነገር ግን ከውሃው ሙሌት እና አለቃቀቅ ጋር በተያያዘ የመረጃ ልውውጥ መኖር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ምክንያት ያሉትም ከሕሴው ግድብ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሱዳን የሚገኘውን “ሮሳሬስ ግድብን ለማስተዳደር የሕዳሴው ግድብ መረጃ ያስፈልጋል ፤ ያለበለዚያ በግድቡ ውሃ ለመያዝ እና ለመልቀቅ እንቸገራለን” የሚል ነው፡፡
ግብፅ በዛሬው ስብሰባ ላይ መገኘት ሲገባት አልተገኘችም ፤ ሚኒስትርም ሆነ ባለሞያም ወደ ስብሰባው አላከችም።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።