TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update መግለጫው ተራዘመ⬇️

ሰኔ 16 ቀን ጠ/ሚ #አብይ_አሕመድ ድጋፍ ለመግለጽ በመስቀል አደባባይ በተጠራ ሰልፍ ላይ የደረሰው ስለተፈጸመው የቦምብ ጥቃት እና የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር #ስመኘው_በቀለ ግድያ አስመልክቶ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በነገው ዕለት መግለጫ ለመስጠት የያዘውን ቀጠሮ #ለጳጉሜ 1 ቀን 2010 ዓ.ም አራዝሞታል፡፡

©DireTube
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አስመራ⬇️

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ በአስመራ ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አሕመድ ወደ ኤርትራ ተጉዘው የአሰብ ወደብን እየጎበኙ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት #ሞሐመድ_አብዱላሒ+ሞሐመድ ዛሬ አስመራ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሶስቱ አገሮች በመሪዎች ደረጃ የሚወያዩበት ጉዳይ #ምንነት ግን አልተገለጸም።

ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ኤርትራ የገቡት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ የምፅዋ ወደብ እና አስመራን እንደሚጎበኙ የኤርትራው የማስታወቂያ ምኒስትር አቶ የማነ ገብረአብ በትዊተር ገልጸዋል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ምኒስትር አብይ በሚያደርጉት ውይይት ባለፈው ሐምሌ ወር የተፈራረሙትን ሥምምነት ተግባራዊነት እንደሚገመግሙ አቶ የማነ ገልጸዋል።

የቻይና አፍሪቃ የትብብር ጉባኤን ተሳትፈው ወደ ኤርትራ ያቀኑት ጠቅላይ ምኒስትር አብይ ከአሰብ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን 71 ኪሎ ሜትር መንገድ መጎብኘታቸውን ለገዢው ግንባር ቅርበት ያለው ራዲዮ ፋና ዘግቧል።

©የጀርመን ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር አይሻ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አሕመድ ባዋቀሩት አዲስ የካቢኔ አባላት ውስጥ #የመከላከያ_ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ የሚባል ዜጋ የለም "ኢትዮጵያ ለሁሉም #እኩል የሆነች አገር ናት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሌለበት ገልፀው፤ "ፖለቲከኛም፣ ጤነኛም ሆነ በሽተኛ መሆን የሚቻለው #አገር ስትኖር ነው" ብለዋል።

በየትኛውም ደረጃ ያለ ማንኛውም የመንግሥት አመራር ላይ ያለ ሰው ገለልተኛ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ አይሻ፤ "ይህን ደግሞ በሚያንፀባርቁት ሐሳብም በድርጊትም ማሳየት ይገባቸዋል።"ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት(ፂዮን ግርማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"ነገ #ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል። እንደ ምንጮቼ ጥቆማ በነገው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አሕመድ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቅርበው #ያሾማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው።

ለጊዜው ስማቸውን መግለፅ የማልችለውና በአሁኑ ወቅት በዳኝነት ሥራ ውስጥ የሌሉ ሴት የሕግ ባለሞያ በእጩነት ቀረበው እንደሚሾሙ ያገኘሁት መረጃ ያስረዳል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩና ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ፀጋዬ አስማማው መልቀቂያ ማስገባታቸውን መረጃዎች ይጠቁማል።"

ምንጭ፦ ፂዮን ግርማ(VOA አማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

ፓርላማው ነገ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

• የቀድሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወ/ት #ብርቱካን_ሚደቅሳ ሰብሳቢ ይሆናሉ ተብሏል

• የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጉዳይ #ውሳኔ ላይ #አልተደረሰም

በነገው ዕለት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት በጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አሕመድ ዕጩ ሆነው የሚቀርቡትን የቀድሞዋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና የሕግ ባለሞያ ወ/ት ብርቱካን ሚደቀሳ ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያው አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነርነት በዕጩነት ቀርበው በመንግሥትና በእርሳቸው በኩል የተጀመረ ንግግር ቢኖርም እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አለመደረሱን ምንጮች ጠቁመዋል።

በመንግሥትና በአቶ #ዳንኤል_በቀለ መካከል ንግግር መጀመሩንና ነገር ግን ውሳኔው አለመጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

🔹አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪና በዲቨሎፕመንት ስተዲስ በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል። እንግሊዝ ከሚገኘው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለም አቀፍና የሰብዓዊ መብቶች ሕግ በማስተርስ ተመርቀዋል። በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ሕግ ከዚያው ከኦክስፎርድ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለመጨረስ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ይቀራቸዋል።

አቶ ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል፣ በሕብረት ኢንሹራንስ የሕግ ዳይሬክተረ ነበሩ። መንግሥታዊ ባልሆነው ግብረ ሰናይ ድርጅት (Actionaid- Ethiopia ) አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። በምርጫ 97 ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው ነበር። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር ነበሩ።

ምንጮች እንደገለፁት አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እዲመሩት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለና በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስ ነው። በዚህ መሰረት በነገው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርበው ሹመት የብሔራዊ ምራጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ብቻ ነው።

🔹ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል። ከረዳት ዳኛነት እስከ ፌደራል ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል። በጥብቅና ሞያና በሕግ አማካሪነት ሠርተዋል። በ1992 ዓ.ም ተወልደው ያደጉበትን (ፈረንሳይ ለጋሲዮን) አካባቢ በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ተወዳዳሪ ነበሩ። የቅንጅት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሆነው ሠርተዋል። በእዚህ ወቅትም ለእስር ተዳርገዋል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ አንድነት ፓርቲን በሊቀመንበርነት መርተዋል። በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ ታስረዋል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዛ National Endowment for Democracy (NED) ኔድ በተሰኘ የታወቀ የዴሞክራሲ የምርምር ተቋም ውስጥ ተመራማሪ ፌሎ በመሆን ለአንድ ዓመት በዴሞክራሲ ላይ ምርምር አድርገዋል። በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ውስጥም (Scholars at Risk) በተሰኘ ፕሮግራም ለአንድ ዓመት ሰልጥነዋል።

በዚሁ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ አስደዳደር (Public Administration) በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቀዋል። ምክር ቤቱ ነገ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያን በወ/ት ብርቱካን ተክቶ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ያልተሟሉ የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መናብርት ሹመትን ለማፅደቅ የውሳኔ ሐሳብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ፂዮን ግርማ(ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia