TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን⬇️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #ወደነበረበት የሚመልስ ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ። ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ይቋቋማል

በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው #ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ቀውስ ወደ #ፌዴራል መንግሥት የተዘዋወረውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ወደ ከተማው አስተዳደር መመለስ የሚያስችል ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ባካሄደው ጥናት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የራሱ የሆነ አዲስ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዲመሠርት ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ባከናወነው ጥናት ላይ የመጀመርያ ዙር ውይይት ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ወቅት በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ›› የተሰኘ አዲስ የካቢኔ አባል የሚሆን ተቋም እንዲመሠረት ሐሳብ ቀርቧል፡፡

ይህ አዲስ ተቋም ላለፉት 14 ዓመታትአስተዳደር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሥር ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በድጋሚ ወደ ከተማው በመመለስ፣ የከተማውን ደንብ ማስከበር አገልግሎትና በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚቋቋሙትን የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን አቅፎ ይይዛል፡፡

#የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታና ቢሮ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለከተማ #አስተዳደሩ ከንቲባ ይሆናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ፍቃዱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተዘጋጀው ጥናት ለካቢኔ ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

በቀረበው ረቂቅ ጥናት ላይ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 እና በቻርተሩ 95 አንቀጽ 10 መሠረት፣ አዲስ አበባ ከተማ ራሱን የማስተዳደር #መብት አለው፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል፣ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደንግጓል፡፡

ረቂቅ ጥናቱን ያቀረቡት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ቤተ ማርያም መኮንን እንዳሉት፣ አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን የራሱ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የለውም፡፡

‹‹ራሱን የቻለ የፀጥታ መዋቅር ባለመኖሩ የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ባደረገ መንገድ ባለመደራጀቱ፣ የፀጥታ ተቋማቱ በተለያየ መዋቅር እንዲመሩ ሆኗል፤›› በማለት የገለጹት አቶ ቤተ ማርያም፣ ‹‹አዲስ የፀጥታ አስተዳደር መዋቅር ተግባራዊ ሲሆን ይህ ችግር ይፈታል፤›› ብለዋል፡፡

በአዲሱ መዋቅር መሠረት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ያሉ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤቶች በቢሮው ሥር ይተዳደራሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የፍትሕ፣ የፀጥታ፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መነሳታቸውን ያስታወሱት ደግሞ፣ የከተማው ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ግዛው ናቸው፡፡

ከነዋሪዎች የሚነሱትን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት፣ የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ አዲሱ መዋቅር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

ይህ ጥናት እንዲካሄድ መመርያ የሰጠው የከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመሆኑ፣ በሒደት ላይ ያሉ ሥራዎች ሲጠናቀቁ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ)/ODP የኦሮሞ ህዝብ #ጥያቄን ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፤ #የአዲስ_አበባ እና #የአፋን_ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ መሆኑን ODP አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የአዲስ_ፓርቲ ምስረታ ገና አላለቀም 108+ #Loading...

Via Endalkachew E. Maraso
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የአዲስ_አበባ_ሞተረኞች...

የሞተር ብስክሌት #እገዳው በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን–የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/Mot-07-09-2
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . .

ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል።

ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ?

ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ላለፉት ሁለት / 2 ዓመታት አከራካሪ በሆኑ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች በተለይም ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች የማሻሻያ ጥናት ማድረጉን አሳውዋል።

በጥናቱም ፦

በ2000 ዓ.ም ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተዘረዘሩት 83 ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል 41 የሚሆኑት በስልታዊ የዘፈቀደ ዘዴ (systematic random sampling) ተመርጠዋል ሲል አሳውቋል።

በዚህ መሠረት የሕገ-መንግሥቱ መግቢያ ላይ ያሉ የተወሰኑ ሐሳቦች ማለትም ፦

👉 የብሔር ብሔረሰቦች ሉዓላዊነት አንቀፅ 8፣

👉 የፌዴራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ፣

👉 ብሔራዊ አርማ፣

👉 #ብሔርን መሠረት ያደረገው አስተዳደራዊ ወሰን፣

👉 #መገንጠልን የሚደነግገው አንቀፅ 39፣

👉 የፖለቲካ ፓርቲን #በብሔር_ማደራጀት

👉 #የአዲስ_አበባ_አስተዳደርን በተመለከተ መሻሻል እንዳለባቸው #ሕዝቡ_ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል ብሏል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU አንጋፋው የ " #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ " በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል። ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ…
#AAU

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ #የአዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው ተሾሙ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ #ቻንስለር ተደርገው በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተሹመዋል።

ሹመቱ የተሰጣቸው፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆኖ እንዲቋቋም እንዲቋቋም በአዋጅ መጽደቁን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ተከትሎ ከተሾሙት ቻንስለር በተጨማሪ አዳዲስ የቦርድ አመራሮች የተሰየሙለት ሲሆን ፤ ቦርዱም ዩኒቨርሲቲውን በሃላፊነት ሊመሩ የሚችሉ ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንቶችን በቀጣይነት እንደሚሾም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

#Update

ቦርዱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬህይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia