TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ፦

ኢሕአዴግ "ዝርዝርና ብስል" ግምገማ አድርጊያለሁ ብሏል። አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት ሥራ አስፈጻሚው በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች እንዲታረሙ፣ ፓርቲዎቹም እርስ በርስ #ከመወነጃጀል እንዲቆጠቡ ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።

"የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሙሉ ልብ ሁሉም ወስደው በተመሳሳይ ሁኔታ ያለመፈጸም" ችግር በኢሕዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል መኖሩን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደደረሰበት አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። በጋራ የተወሰኑ ጉዳዮች እኩል ተግባራዊ አይሆኑም ብለዋል።

የሕግ የበላይነትን ማስከበር ፣ ለውጡን ተቋማዊ ማድረግ፣ "የለውጡን ምንነት ማስረዳት"፣ በ2012 "ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትኃዊ ምርጫ" ለማካሔድ መዘጋጀት፣ ደኢሕዴን ላሰራው "ሳይንሳዊ ጥናት" ድጋፍ ማድረግ ከኢሕአዴግ ውሳኔዎች መካከል ይገኙበታል።

Via #EshetBekele
@tsegabwode @tikvahethiopia