TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢፍጣር በደሴ እና በኮምቦልቻ :

በደሴ ከተማ የሙስሊም ወጣቶች ማኅበር የተዘጋጀው ልዩ ''የአብረን እናፍጥር'' የኢፍጣር መርኃግብር በደሴ ከተማ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል።

መርኃግብሩ ፍቅርንና አንድነትን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ይማም አህመድ ተናግሯል።

በኢፍጣር ዝግጅት ላይ የደሴ ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና አቅመ ደካሞች ታድመዋል።

በሌላ በኩል ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ዝግጅት ተካሂዷል።

ከተለያዩ አከባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ እና ለከተማዋ ማኅበረሰብ ነው የኢፍጣር መርኃግብሩ የተዘጋጀው።

ረመዳን የመተሳሰብና የመተዛዘን ወር መሆኑን የገለጹት የመርኃ ግብሩ አስተባባሪዎች የኢፍጣር ዝግጅቱ አብሮነትን ያጎለብታል ብለዋል።

መርኃግብሩ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን #አሚኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
' የካራማራው ጀግና ' የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ከባሕር ዳር ጋምቢ ሆስፒታል ወደ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው። የካራማራው ጀግና ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ግንቦት 08/2013ዓ.ም በደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል። አስከሬናቸው በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፍትሃት…
ብ/ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ተሰማ ፦

- በድሮው አስተዳደራዊ አወቃቀር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጥር 28 /1933 ዓ/ም ነበር የተወለዱት።

- እስከ ጄነራልነይ ማዕረግ ያደረሳቸውን ህይወታቸውን በውትድርና የጀመሩት በ1960 ዓ/ም ነበር።

- በሶማሊያ ወረራ ወቅት የ69ኛውን ሚሊሻ ብርጌድ በማሰልጠን በግንባርም አዋጊ ሆነው በመምራት ታላላቅ ጀብዶችን ለሀገራቸው የፈፀሙ ነበሩ።

- መስከረም 1970 ዓ/ም ላይ በድሬዳዋ ግንባር ወደውጊያ የገቡ ሲሆን ካራማራ፣ ጅግጅጋ፣ ደጋሀቡር እና ቀብሪደሃር (መጋቢት 1/1970) ከሶማሊያ ጦር ወረራ ነፃ አውጥተው በመቆጣጠር የምስራቁን ግንባር ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ ያደረገውን ብርጌድ መርተዋል።

- ከወታደራዊ ስራቸው ተጨማሪ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክ/ሀገሮችን አስተዳድረዋል።

- የፌዴራል መንግስት ተቋማትን መርተዋል።

- ለሀገራዊ አገልግሎታቸው የህበረተሰባዊ ኢትዮጵያ ታላቅ የክብር ኮከብ ኒሻን እና የየካቲት 66 አብዮት ኒሻን እና ሌሎች ሽልማቶችን አግኝተዋል።

- ባለትዳር እና የ7 ልጆች አባት ነበሩ።

#አሚኮ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ የማስጀመሪያ ዝግጅት በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው !

የአማራ ባህል ማእከል ግንባታ የማስጀመሪያ ዝግጅት በአዲስ አበባ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የአማራ ባህል ማዕከል በአዲስ አበባ መገንቢያ የሚሆን 42ሺ 200 ካ.ሜ ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተረክቧል፡፡

የባህል ማእከሉ የአማራን ሕዝብ ማንነትና ጸጋ በሚያሳይ መልኩ እንደሚገነባ ተገልጿል፡፡

ለባህል ማእከሉ ግንባታ እስካሁን ከ120 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የአማራ ልማት ማኅበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ገልጿል፡፡

የአማራ ልማት ማህበር አልማ የ2012 እና የ2013 ዕቅድ አፈጻጸም ጉባዔ በአንድነት ፓርክ እያካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

#ኢብኮ #አሚኮ

@tikvahethiopia
የ3 ዓመት ከ2 ወር ህፃን ያገቱት ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

በእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ሰኔ 15/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ገደማ የ3 ዓመት ከ2 ወር ሕጻን በማገት ተሰውረዋል፡፡

በዕለቱ ከቀኑ 11፡30 ገደማ ላይ የሕጻኑ ወላጆች በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ 8ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

ሪፖርት በሚያደርጉበት ጊዜ ከአጋቾች በኩል ለሕጻኑ ወላጆች ስልክ ተደውሎ 300 ሺህ ብር መክፈል ከቻሉ ሕጻኑ እንደሚመለስላቸው ይነግሯቸዋል፡፡

ፖሊስ ሕጻን በማገት ድርጊት የተሳተፉት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥ ሥር ለማዋል ስምሪት ያደርጋል ፤ በማኅበረሰቡ ጥቆማ አዴትና ሰባታሚት ተብለው ወደሚጠሩ አካባቢዎች ልዩ ስምሪት በማድረግ ትናንት ከቀኑ 9፡00 ላይ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር ማዋል ችሏል።

ከዋናው ተጠርጣሪ ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሌሎች ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ፖሊስ እንደገለፀው ፥ ተጠርጣሪው ከማቀድና ሁኔታዎችን አቀነባብሮ ድርጊቶችን ስለመፈጸሙ እንዲሁም ሕጻኑን አግቶ እንደተሰወረ አምኗል፡፡ ስለፈጸማቸው ድርጊቶች ሁሉ ለፖሊስ ቃል ሰጥቷል።

ተጠርጣሪው ዛሬ ጠዋት 4፡00 ላይ ፖሊሶችን ሕጻኑ ወደተደበቀበት ይልማና ዴንሳ መርቶ ወስዷል፤ በዚህም መሰረት 5፡15 ላይ ሕጻኑን ማግኘት ተችሏል።

የለበሰው ልብስ ከመቀየሩ ውጪ ሕጻኑ ምንም ጉዳት አልደረሰበትም።

የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመ በአራተኛው ቀን ሕጻኑ ለወላጆቹ እንዲመለስ ተደርጓል።

ምንጭ፦ #አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ። የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት እንዳሳወቀው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበዋል። ሌሎችም ጄኔራሎች እና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማትን እንዲመሩ በክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አገኘው ተሻገር ምደባ እንደተሰጣቸው አሚኮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
#UPDATE

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የክልሉን የጸጥታ መዋቅር ለማጠናከር በዛሬው እለት ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ብ/ጀ/ተፈራ ማሞ የልዩ ሃይል አዛዥ፣
2ኛ. ጀ/መሰለ በለጠ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
3ኛ.ኮሚ/ ቢሰጥ ጌታሁን ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽን፣
4ኛ. ኮሚ/ አርአያ ካሴ ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
5ኛ. ጀኔራል ማሞ ግርማይ ም/ አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
6ኛ.ጀኔራል ዘዉዱ እሸቴ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
7ኛ. ጀኔራል አበራ ተ/ዮሃንስ ም/አዛዥ ለአስተዳደር፣
8ኛ. ረ/ ኮሚሽነር መለሰ ደገፋዉ ም/ አዛዥ ለአስተዳደር፣
9ኛ. ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ልዩ ረዳት ፣ ሆነው ተመድበዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia
የተፈናቃዮች ጥሪ :

በወልዲያ ከተማ በአምስት መጠለያ ጣቢያዎች ከራያ ቆቦ እና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎች ይገኛሉ።

በወልድያ ከተማ የሚገኙት ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን #አሚኮ ዘግቧል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ሁሉም እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ወልዲያ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች የከተማው ህዝብ ላደረገላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ የሚደረግላቸው የሰበዓዊ ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የወልድያ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሙሀመድ ያሲን የከተማዋ ነዋሪዎችና ወጣቶች ተፈናቃዬቹን ለመደገፍ ላደረጉት ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባው ባለሀብቶችና የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ህወሓት በአፋር እና አማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ከ225 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው በሁለቱ ክልል መንግስታት መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።

አቶ መልካሙ ሹምዬ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ፤ ፓርቲው ለ3 ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ሲያካሂድ እንደቆየና የሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በአዲስ በማደራጀት ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት፦

👉 ዶ/ር በለጠ ሞላ - ሊቀመንበር
👉 አቶ መልካሙ ሹምዬ - ምክትል ሊቀመንበር
👉 ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ - የውጭ ግንኙነት ኃላፊ
👉 አቶ ዩሱፍ ኢብራሒም - የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ
👉 አቶ ክርስቲያን ታደለ - የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ክፍል ኃላፊ
👉 አቶ ጋሻው መርሻ - የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ
👉 አቶ ጣሂር መሐመድ - የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
👉 ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም - የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ
👉 አቶ ሐሳቡ ተስፋየ - አደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ አድርጎ የሥራ አስፈፃሚውን በአዲስ አደራጅቷል።

ከተመረጡት የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚዎች መካከል ሦስቱ አዲስ መሆናቸው ተገልጿል።

ፓርቲው ዛሬ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ማካሄድ መጀመሩን #ኢብኮ / #አሚኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው ፦
👉 የአማራ ክልል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
👉 የአፋር ክልል የትራንስፖርት እና መንገድ ቢቶ
👉 የፌዴራል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የአማራ ክልል የትራንፖርት እና የሎጀስቲክስ ባለስልጣን ምን አለ ?

- በአማራ ክልል አቅጣጫ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ የሕዝብ ትራንስፓርት የሙከራ ጉዞ  ወደ አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ሶስት (3) የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአማራ ክልል በኩል ጉዞ አድርገዋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ ጉዞ ጀምሯል።

- የአማራ ክልል መንግሥት ለማንኛውም የትራንፓርት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋል።

- የክልሉ ሕዝብ ለሰላማዊ እንቅስቃሴ በጎ አመለካከት ያለው በመኾኑ ጉዞው ላይ ችግር አያጋጥምም።

የአፋር ክልል የትራንፖርት እና መንገድ ቢሮ ምን አለ ?

- በአፋር ክልል በኩል በመጀመሪያው ቀን ብቻ ሁለት የሙከራ ጉዞዎች የተደረጉ ሲሆን ትራንስፖርት ከተጀመረ ዛሬ 6 ቀናት ተቆጥረዋል።

-  ክልሉ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲኾን ያግዛል።  መንግሥት ብቻ ሳይኾን ሕዝቡም ሰላማዊ አንቅስቃሴውን ይደግፋል።

- ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ይፋዊ የየብስ ትራንፖርት ጀምሯል።

የትራንፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ተቋርጦ የነበረው የየብስ ትራንፖርትን ለማስጀመር ሁለት የጥናት ቡድን በአማራ ክልል በኩል እና በአፋር ክልል በኩል በመላክ ጥናት ተደርጓል።

- በሁለቱም ክልሎች በኩል 19 የሙከራ ጉዞዎች ከአዲሰ አበባ ትግራይ ክልል እና ከትግራይ ክልል አዲስ አበባ ተደርጓል።

- ከዛሬ ጀምሮ  ይፋዊ የየብስ ትራንስፖርት ተጀምሯል።

የትግራይ ክልል የትራንፖርት ቢሮ ኀላፊዎች በአየር ትራንፖርት #መዘግየት ምክንያት በአዲስ አበባ በተሰጠው የጋራ መግለጫ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

#አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . . ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ? ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት…
ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?

" ሕገ መንግሥቱ #ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ክርክር እየተነሳ ይገኛል።

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ  መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡

በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡  በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል።

ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል። "

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ምን አሉ ?

" ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበት ሁኔታ አለ።

በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል።

391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል። በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊሆን አይችልም።

ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ  በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል።

የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመሆኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል።

ለምሳሌ ፤ የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች ተሻሽለዋል

ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ።

አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል ይገኝበታል።

ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው ነው።

ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ።

በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም ነው። "

#አሚኮ

@tikvahethiopia
#አብና🕯

" የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! "

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል።

የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ?

" የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም።

በጉዳቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ ተደርጓል።

በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። " #አሚኮ

@tikvahethiopia