TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።

እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።

#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች #የጸጥታ ችግር መከሰቱ ተገለጸ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞንና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በተከሰተው የጸጥታ ችግር በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

አሁን ለተከሰተው የጸጥታ ችግር መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢላ አሙማ አገሎ በተባለው ስፍራ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የከማሺ ዞን አመራሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት 4 የከማሺ ዞን አመራሮች #መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

በእነዚህ ታጣቂዎች ግድያ የተፈጸመባቸው የከማሺ ዞን አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ከተላኩ አመራሮች ጋር ከዚህ ቀደም ከክልሉ #ተፈናቅለው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደነበሩበት #በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ በአሶሳ ከተማ ተወያይተው ወደ ከማሺ ዞን በመመለስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል፡፡

በከማሺ ዞንና እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙት የሳስጋ፣ ድጋ፣ ሐሮ ሊሙ፣ ሊሙ፣ ቦጂ ብርመጂ ወረዳዎችና በሌሎች አከባቢዎች በተከሰተው በዚህ ግጭት ከነቀምቴ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ አሁን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል፡፡

በተከሰተው ችግር ሳቢያ በቤንሻንጉል ክልል ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ተፈናቅለው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ወሰን አካባቢ ወደሚገኙት የኦሮሚያ ወረዳዎችና ወደ ነቀምቴ ከተማ መሰደዳቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በአከባቢው የተከሰተውን ችግር #ለማረጋጋት የጸጥታ ኃይሎችና የአስተዳደር አካላት፣ የፌዴራል መንግስትና ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮው ገልጿል፡፡

በዜጎች ላይ ለደረሰው ጉዳት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ገልጿል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላላም ጃለታ በበኩላቸው፣ በአከባቢው የጸጥታ ችግር መከሰቱን አምነው፣ በከማሺ ዞን የሚገኙት ነዋሪዎች ጥቃት ይደርስብናል በሚል ፍርሃት የጉሙዝ ተወላጆች ቤታቸውንና ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ #እየተሰደዱ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ደግሞ ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እየተሰደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በርካታ የኦሮሞ ማህበረሰብና የጉሙዝ ተወላጆች ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሶማሊያ መዲና ሞቆዲሾ የተፈፀመውን የአሸባሪዎች ጥቃት አወገዙ፡፡ ዶ/ር ወርቅነህ ለሶማሊያ አቻቸው አህመድ ኢሴ አዋድ በላኩት መልዕክት በተሰነዘረው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት 53 ንፁኃን ሶማሊያውያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን እንዲሁም ከ 100 በላይ የመቁሰል አደጋ በመድረሱ የተሰማቸውን ጥለቅ #ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ይህ አሰቃቂና ጭካኔ የተሞላበት የሽብር ጥቃት የፈጸሙ አካላት በጥብቅ አውግዘው ጥቀቱ አሸባሪነት ከሶማሊያም አልፎም የአካባቢው ስጋት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ለሶማሊያ ፌዴራል መንግስትና ህዝብ #መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ🔝የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈፀመውን ግድያ ተቃውመዋል። ተማሪዎቹ በዜጎች ሞት የተሰማቸውን #ሀዘን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tiivahethiopia
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ🔝የተቋሙ ተማሪዎች ከሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈፀመውን ግድያ የተሰማቸውን #ሀዘን ገልፀዋል። በሻማ ማብራት ስነ ስርዓትም አከናውነዋል።

@tsegabwolde @tiivahethiopia
#Update የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ #በተደራጀ_ሌብነት ተሰማርተው የክልሉን የተፈጥሮ ሀብት የመዘበሩ አካላት በምርመራ ተለይተው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ #እርምጃ እንዲወሰድባቸው ወስኗል፡፡ በተጨማሪም ክልሉ በውስጥም ሆነ በውጭ የሚስተዋሉትን ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ከአጎራባች ክልሎችና ከፌዴራል መንግስት ጋር በመቀናጀት በአጭር ጊዜ እንዲያስቆም ወስኗል። ማዕከላዊ ኮሚቴው በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች በጠፋው የሰው ህይወት፣ እንዲሁም በደረሰው የአካል ጉዳትና መፈናቀል የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ገልጿል። የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም፣ አጥፊዎችን በህግ ለማስጠየቅ እና የፌዴራል መንግስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ለማስፈጸም በትጋት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጧል።

ምንጭ፡- የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ‼️
----------------------
በተማሪ ዩሴፍ ገ/መስቀል ሞት ምክንያት የደብረ ታብር ዩኒቨርስቲ የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ይገልፃል፡፡

ተማሪ #ዩሴፍ የአምስተኛ አመት የመካኒካል ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 14/2011ዓ.ም ከምሸቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በጥበቃ ሰራተኛ #በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል፡፡

የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ለቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እየተመኘ በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ዩኒቨርስቲው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በደረሰው የአውሮላን አደጋ የተሰማቸውን #ሀዘን ገለፁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በደረሰው ጉዳት ከልብ ማዘናቸውን እና ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች #መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

በተጨማሪም...

የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት፣ የአማራ ክልል መንግስት ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በአዘደጋው ተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ ሀዘናችን ጥልቅ መሆኑን እንገልፃለን!

በሀገራችን #ወጣቶች ህልፈት የተሰማን #ሀዘን ጥልቅ ነው። ልባችን ደምቷል!! ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የሀገራችን ህዝብ መፅናናትን እንመኛል።

ነብስ ይማር!!
#ቀይ_ባህር ወንድም እህቶቻችንን በላብን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
#ላሊበላ

" ' ቫይብሬሽን ትንሽ ነበረ የሚባለው ' ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉ ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው... ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለም ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷ አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት " - አቶ አበባው አያሌው

(በኢዮብ ትኩዬ)

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ስለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ጉዳት ደርሷል ስለሚባለው ጉዳይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአማራ ፤ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ዙሪያ በፋኖ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ሰሞኑን ተደረገ በተባለ የተኩስ ልውውጥ በቅርሱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፣ ከባድ መሳሪያ እየተተኮሰ በመሆኑ ከፍተኛ ንዝረት እንዳለ በዚህም ቅርሱ አደጋ እንተጋረጠበት የተለያዩ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያው ሲንሸራሸሩ ተስተውለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ " ቅዱስ ቅርሱ " አደጋ ላይ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፦
* በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ?
* ስለ ጉዳዩ የሚወጡት መረጃዎች ምን ያህል እውነተኛነት አላቸው ?
* አዲስ ስንጥቅ አለ ? የሚሉትን ጥያቄዎችና አጠቃላይ ስለጉዳዩ ያለው ማብራሪያ ምን እንደሆነ ለቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርቧል።

በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይስ የለም ? ተብሎ በመጀመሪያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው ኮሚቴ ተልኮ ተረጋግጧል ያሉትን ሁኔታ ከማብራራት ጀምረው እንደሚከተለው ገልጸዋል።

" ላሊበላ አካባቢ ግጭት ነበረ። ከዚያ በመነሳት ነው ' በጥይት ተመቷል ' ይሉ የነበረው " ሲሉ ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም 7 ሰዎች ያሉበት (ከደብሩ ካህናት 3 ሰዎች፣ ከላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት 3 ሰዎች፣ በቦታው ከሚገኝ የቅርስ ባለሥልጣን 1 ሰው) ኮሚቴ ተዋቅሮ ከ3፡00 እስከ 6፡40 ገደማ ዞረው ቅርሱን አይተዋል ብለዋል።

በዚህም የሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ኮሚቴ ፦
- ቤተ አማኑኤልን፣
- ቤተ ሊባኖስ፣
- ቤተ ገብርኤል ያሉባቹውን ቦታዎች ተመክተዋል ነው ያሉት።

አቶ አበባው አክለውም ፤ " ' በቤተ ገብርኤል አናቱ ላይ ጥይት አርፏል' የሚል ነው ወሬው እዛ ሲወራ የነበረው " ብለው፣ "ቤተ ገብርኤል ተወጥቶ ታይቷል። ጥይት ያረፈበት ምንም ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

2ኛው ደግሞ ' ቤተ ሊባኖስ አካባቢ ጥይት ተተኮሰ ' የሚል ነገር እንደነበር ገልጸው፣ " እዛም ላይ ምንም ምልክት የለም። እንዳውም ጥገና እየሰራንበት ነው። 'ቤተ አማኑኤል ላይ ደግሞ የመጠለያውን ብረቱን ጥይት መትቶታል' የሚል ነው፣ ምንም የተመታ የለም። በቦታው የነበሩ ጥበቃዎች አሉ ፣ የተመታ ነገር የለም፣ ግን ሲተኮስ #ቫይብሬሽን ስለነበረው ቃቃ ይል ነበር መጠለያው ከዚያ ውጭ ምንም ነገር የለም " ሲሉ ከኮሚቴዎቹ ያገኙትን ምላሽ አስረድተዋል።

ከሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ቀጥሎ የደቡብ ምዕራብ ግሩፕ ደግሞ ፦
- ቤተ መድኃኒዓለም፣
- ቤተ ማርያም፣
- ቤተ ጎለጎልታ ያሉበትን ቦታ እንደተመለከተ፣ እዚያ ሲባል የነበረው ደግሞ 'የቤተ መድኃኒዓለምን መጠለያ ብረቱን መትቶታል' የሚል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ " ጥይት ሲያርፍ ምልክት ይኖረዋል። ግን ዙረው አይተዋል። ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

አንድ ያሳዩአቸው የመጠለያው አናት ሸራ ከጎኑ ቀዳዳ አለ ' ተመትቶ ነው ' የሚል ነው፣ ያቺ ደግሞ ሸራ ቀዶ መግባትም ብዙም ትልቅ ችግር እንደማይኖረው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ጎለጎልታ፣ ቤተ ደናግል እንዲሁም ቤተ ጊዮርጊስ ምንም የተኩስ ምልክት እንደሌለ ተናግረዋል።

አክለውም ፣ ' ትንሽ #ቫይብሬሽን ነበረ ' የሚባለው ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉት ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው" ብለው፣ የአካባቢው ማኅበሰሰብ የደብሩ ካህናት ሆነው አጠቃለሁ የሚለውን ኃይል በግዝትም ቢሆን ወደ ቅርሱ እንዳይጠጋ ማድረግ፣ በመንግሥት በኩል ቅርስ ጥበቃም፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ምንም አይነት ታጣቂ ቡድን በአካባቢው እንዳይኖር ለማድረግ መስራት፣ ከዚያ ውጭ ደግሞ ቤተ ክህነትም ሆነ የመንግሥት አካላት መግለጫ ሲያወጡ ጠይቀው እንዲያወጡ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከኮሚትዎቹ ጋር መወያየታቸውን አስረድተዋል።

ኮሚቴው ቦታው ላይ ተገኝቶ ሳይመለከት የቆየበት ምክንያትን ሲያስረዱም አቶ አበባው ፤ " #ሀዘን ሆኖ ነው አካባቢው ያዘገየነው። ብዙ ሰው አልቋል። በቦታው ድንኳን አለ፣ እንዲያው በትኩሱ ተነሱና እዩ ከምንላቸው ብለን ነው " ብለዋል።

አክለው " ቅርስ ፖለቲካ አይሆንም፣ ያኔ የነበሩ ሰዎች ቅርሱን ለእኛ አውርሰውናል ሲሆን እንጠብቀዋለን እንጂ በእኛ የፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ቅርስን አናስገባም፣ ከፖለቲካም ከምንም በላይ ነው፣ መተኪያ የለውም፣ ይህን ማንም ማሰብ አለበት" ነው ያሉት።

" ከዚያ ውጭ ቀጣይ የምንሰራው ንዝረቱ ካለ ምን አስከትሏል የሚለውን ነው። እያንዳንዷን ስንጥቅ እናውቅምታለን። አዲስ ስንጥቅ ካለ እናሳውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።

ባደረጋችሁት ዳሰሳ አሁን አዲስ ስንጥቅ የለም? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት ምላሽ፣ "የላሊበላን ያሉትን ስንጥቆች ካህናቱም ያውቋቸዋል። እዚያ ያለው ጽሕፈት ቤት ኃላፊም ያውቀዋል። የእኛም ባለሙያ ያውቀዋል። አዲስ ስንጥቅ የለም ኢን ኬዝ ግን ቫይብሬሽኑ ስንጥቅ አስፍቶ ይሆን እንዴ? የሚለውን ለማረጋገጥ 3ዲ ስካን እናወጣለን። አሁን ያለውን እናያለን፣ እናነጻጽራለን እንጅ ላሊበላ ስንጥቅ በስንጥቅ ነው 22 ቦታዎች ተሰንጥቀው እየተጠገኑ ነው" ብለዋል።

አቶ አበባው በሰጡት አክለው ማብራሪያ፣ "ተመታ የሚባለው ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለምን ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷም አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት፣ እሷን ነው እያነሱ ሲበትኑ የነበረው ያ ደግሞ አጥሯ ላይ ግንብ ነው በ2012 ዓ.ም የተሰራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሁለተኛ ጥይት ያለችው ቤተ ደናግል ማርያም ጋ ኢህአዴግ ሰቆጣ ሲገባ የደርግ ወታደሮች እዛ ገብተው ነበር ይተኩሱ ነበር እሷም አለች" ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ስለጉዳዩ ምን ማብራሪያ እንዳላቸው የተደረግልው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ ጉዳዩን በተመለከተ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ቅዱስ ቅርሱ አደጋ ላይ እንደሆነና ልንታደገው እንደሚገባ ገልጸው ነበር።

የብፁዕነታቸው መግለጫ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አበባው፣ "አቡነ ኤርሚያስ ትልቅ ሰው ናቸው ግን ሰው ሊያሳስታቸው ይችላል። ሁሉም ልጆቻቸው ናቸው ፤ እዚያ ያሉት በኮሚቴው የተገመገመው ትክክል አልነበረም የሚል ነው ፤ እርሳቸውም ትንሽ ቹኩለዋል " ብለዋል።

አክለውም ፣ " በመንግሥት በኩልም ግጭት የለም በቦታው ላይ ማለት ትክክል አልነበረም ግጭት ነበረ በእርግጥ " ያሉት አቶ አበባው ፣ " እርሳቸው በተፈጥሯቸው የእውነት ሰው ናቸው ከመቆርቆር የተነሳ ሊሆን ይችላል። መቆርቆሩንም እንወደዋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia