TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Philippines

"ክትባት እስካልተገኘ ድረስ ትምህርት ቤቶች አይከፈቱም!" -ፕሬዘዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ

የፊሊፒንስ ፕሬዘዳንት የሆኑት ሮድሪጎ ዱቴርቴ በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ዘላቂ እና አስተማማኝ መፍትሄ እስካልተገኘለት ድረስ እንደማይጀመረ አሳውቀዋል።

ፕሬዘዳንቱ ሰኞ ዕለት በተሰራጨ የቴሌቪዥን መልዕክታቸው #ክትባት እስካልተገኘ ድረስ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንደማይልኩ ገልፀዋል።

አክለውም የተማሪዎች ደህንነት ባልተጠበቀበትና ለዚህ ወረርሽኝ ክትባት ባልተገኘበት ሁኔታ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ችግሩ ይባብሰዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በፊሊፒንስ እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ 15,588 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ መኃል 921 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 3,598 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot