TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ዶክተር አብይ አህመድ⬇️

የዓለምን ሕዝብና የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ስቦ የሰነበተው ታሪካዊው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ የአሜሪካ ቆይታና ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለሁለት ተከፍሎ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአንድነት ጉዳይ እጅግ ስኬታማና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስደሰተ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ ሲመለሱ ችግር ገጥሟቸው የነበረ በማስመሰል በሚለቀቁት ሀሰተኛ ወሬዎች ሕዝቡ ለዶ/ር ዓቢይ ባለው ፍቅር የተነሳ ሲጨናነቅ ይታያል።

◾️በአውሮፕላኑ ውስጥ አብሬ ተጉዋዥ ስለነበርኩ ይህንን #ሀሰተኛ ወሬ እየሰማሁ ዝም ማለቱን ከውሸት ጋር እንደመተባበር እየቆጠረብኝ ኅሊናዬ ስላልፈቀደ ጉዞው ምንም ዓይነት እንከን ያልታየበት እጅግ የተረጋጋና ሰላማዊ ይልቁንም በከፍተኛ ደስታና ፍቅር የታጀበ ታሪካዊ ጉዞ እንደነበረ ለውድ የፌስቡክ ጉዋደኞቼ ለመግለፅ እወዳለሁ።

©Makonnen Semu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሻሸመኔ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች!

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ።

በአደጋውም እስካሁን በደረሰን ሪፖርት የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱም ታዉቋል። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።

ከአደጋው ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ህገወጥ ቡድኖች ከተማዋ ላይ ህገወጥነት፣ ብጥብጥ እና ግጭት ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል። በዚህ ሂደትም ቦንብ ይዞ ተገኝቷል በሚል #ሀሰተኛ_ወሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በቡድን ጥቃት በማድረስ የግለስቡ ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ይህ ድርጊት አስነዋሪና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ሰላም ወዳዱን የሻሸመኔ ከተማ ህዝብም ሆነ የሻሸመኔን ቄሮ የማይወክል የክፋት ተግባር ነዉ።

ግለሰቡ ላይ የተፈፀመዉን ግድያም አጥብቀን #እናወግዛለን። በተጨማሪም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሽከርካሪ በእሳት ጋይቷል። ተሽከርካሪው ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል #የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ ነዉ። ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጥ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ሰላም ወዳዱ የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥረት ከተማዋ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች።

በዛሬዉ ዕለት በተፈጠረዉ ችግር በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦችንም ህዝቡ እና ፖሊስ በመቀናጀት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

©አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀላባ ከተማ‼️

በደቡብ ክልል ሀላባ ከተማ ትናንት በተሰራጨ #ሀሰተኛ_ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች በከተማው በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ላይ #ጉዳት ማድረሳቸውን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት በከተማው #የማቃጠልና የንብረት #ማውደም ድርጊቱ የተፈጸመው ሌንዳ በር እና ዋጃ በር በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ በሚገኙ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት ላይ ነው፡፡ በስፍራው ነበርኩ ያሉ እንድ የከተማው አዛውንት ጥቃቱ የተጀመረው በድራሜ ከተማ መስኪድ መቃጠሉንና ኢማም መገደሉን የሚገልጹ ወሬዎች ከተናፈሱ በኋላ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በቤተክርስቲያናቱ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ መመልከታቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የጀርመን ድምፅ ራድዮ በሥልክ ያነጋገራቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ #ዓለሙ_ሌንቢሶ ደግሞ በከተማው በተሳሳተ ወሬ የተነሳሱ ወጣቶች አንድ ቤተክርስቲያን በእሳት ያቃጠሉ ሲሆን በሌሎች ሰባት ቤተክርስቲያናት ላይ ደግሞ ንብረቶችን የማውደም ድርጊት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እጅ ከፍንጅ የተያዙ 20 ግለሰቦችን ጨምሮ 63 ተጠረጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቆሙት ሃላፊው የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽነርም ጥቃቱን ለመከላከል ጥረት ባለማድረጋቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምንጫቸው ባልተረጋገጡ ወሬዎች በመነሳሳት የሚፈጸሙ የደቦ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ በቅርቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቀደም ባሉት ጊዚያት ደቦ እርሻን በህብረት ለመሥራት ይውል እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን ጸብም በደቦ እየሆነ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia