የጆ ባይደን እና የአል ሲ ሲ የስልክ ውይይት :
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትናንት ሰኞ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ከሁለቱም ወገን የወጣ መግለጫ አመልክቷል።
ሁለቱ መሪዎቹ በውይይታቸው ግብጽ ከ #ኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ስለገባችበት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንስተው መወያየታቸውን ከፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አልሲሲ ከሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ጋዛ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም በግብጽ አሸማጋይነት ስለተደረሰው ተኩስ አቁምም ተወያይተዋል ተብሏል።
ከዋይት ሐውስ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በስልክ በተደረገው ውይይት ላይ "ፕሬዝዳንት ባይደን የአባይን ውሃ በተመለከተ ግብጽ ያላትን ስጋት እንደሚረዱ ገልጸዋል" ብሏል።
በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ባይደን በጉዳዩ ዙሪያ "የግብጽን፣ የሱዳንን እና የኢትዮጵያን ሕጋዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲገኝ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑን ገልልፀዋል ተብሏል።
በሁለቱ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ፥ ባይደን እና አልሲሲ "የሁሉንም ወገኖች የውሃ እና የልማት መብቶችን የሚያስከብር ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማድረግ ተስማምተዋል" ብሏል።
#BBC #Reuters
@tikvahethiopia

#AddisAbabaPoliceCommission
የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ228 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና ከ85 ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።
ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት አደረኩት ባለው ክትትል ነው ገንዘቡን በቁጥጥር ስር ያዋለው።
ገንዘቡን በቁጥጥር ስር የዋለው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው "መናኸሪያ ግቢ" ውስጥ ነው።
ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ 2 ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሲዘጋጁ ግንቦት 10/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሠዓት ገደማ በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ብርበራ በላስቲክ ተጠቅልሎ የተቀመጠ 205 ሺህ 512 የአሜሪካ ዶላር ተይዟል።
በተጨማሪ የተለያዩ የባንክ ሰነዶችና ፓስፖርት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሌላ መረጃ ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥናት ላይ ተመስርቼ አከናወንኩት ባለው ተግባር ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 11/2013 ዓ/ም በግምት 9 ሰዓት ገደማ ለህገ ወጥ ዝውውር የተዘጋጀ 23 ሺ 300 የአሜሪካ ዶላር ፣ 85 ሺ 600 የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም 17 የተለያዩ የኤ.ቲ.ኤም ካርዶች እና 29 የተለያዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር እንደያዘ ሪፖርት አድሯል።
በአጠቃላይ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ ነው።

#Moderna
ሞደርና የኮቪድ-19 ክትባቱ እድሜያቸው ከ12 እስከ 17 ባሉ ታዳጊዎች ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በጣም ውጤታማ ነው ሲል በዛሬው ዕለት ሪፖርት አድርጓል።
ሞደርና ከ3,700 በላይ በሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ12 - 17 ባሉ ታዳጊዎች ላይ ጥናት ማድረጉን ገልጿል።
በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የደረሰበትን የጥናት ውጤት ለአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር እና ለሌሎች የዓለም ተቆጣጣሪዎች በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ላይ አቀርባለሁ ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት በትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ።
የአሜሪካ ተርአዶ ድርጅት (USAID) 33 የቢሮ መኪኖችን እና 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ድጋፍ ማድረጉን ኢብኮ ዘግቧል።
የUASID ተወካዮች በጤና ቢሮ በመገኘት ከቢሮ ኃላፊዎቹ ጋር የቁልፍ እና የቁሳቁስ ርክክብ አድርገዋል።
መኪናዎቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በጤና ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
ድጋፉ በክልሉ ያጋጠመውን የመኪና እጥረት በማቃለል ረገድ አስተዋፆ አለው ተብሏል።
USAID በትግራይ በጤናው ዘርፍ ያጋጠመውን ጉዳት ለመለስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።
የትግራይ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ ፥" በትግራይ ብዙ መኪናዎች ጠፍተዋል፣ ተጎድተዋል። እንደ ምሳሌ ከ270 አምቡላንስ 50 አምቡላንስ ብቻ ነው እየሰራ ያለው። ከወረዳ ወረዳ ፣ ከወረዳ ሆስፒታል ከሆስፒታል ሆስፒታል የእናቶች ፣ የልጆች ሪፈራል አገልግሎት ተስተጓጉሏል፤ ከደረሰው ጥፋትና ጉዳት አንፃር ድጋፉ ትንሽ ነው፤ በጣም ብዙ ነው የሚያስፈልገው ፤ ነገር ግን ይሄም ትልቅ ውጤት ይኖረዋል ፤ በክልሉ ከነበረው የጤና ስርዓት አንፃር ስንመለከተው የጎደለው ብዙ ነው" ብለዋል።
ዶ/ር ፋሲካ በUSAID ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በክልሉ የአምቡላንሶች አለመኖር በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑን ገልፀዋል።
አቅም ያላቸው አጋር ድርጅቶች ፣ ያገባኛል የሚሉ አካላት ፣ ግለሰቦች ፣ ባለሃብቶች የክልሉን የጤና ስርዓት ለማስተካከል ከመድሃኒት ጀምሮ ሌሎች ትልልቅ እገዛዎችን በአቅማቸው እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።

ቻይና ለትግራይ ክልል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።
ቻይና ለትግራይ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና ለሌሎች የህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።
ድጋፉን የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ ካውንስለር ሊ ዩ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስረክበዋል።
ድጋፉ ፦
- ሰባት (7) የመተንፈሻ እገዛ የሚሰጡ መሳሪያዎች (ቬንትሌተሮች)፣
- 36 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)
- 1 ሺህ 500 የህክምና አልባሳትን
- የህክምና እርዳታ ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ያካተተ ነው።
ድጋፉ ከቻይና መንግሥትና ከቻይና ኩባንያዎች የተሰባሰበ ነው። #ENA

#Shire
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።
የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።
ከእርዳታ ሠራተኞች መካከል አንዱ ፥ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ብለዋል።
በአንዱ ካምፕ ውስጥ የሚኖር ክስተቱ በተፈፀመበት ወቅት የተደበቀ አንድ ግለሠብ ወታደሮች ሰብረው ገብተው ሰዎችን በዱላ መደብደባቸው ተናግሯል።
ይኸው ስሙ በሚስጥር እንዲያዝ የጠየቀው ግለሰብ ፥ ወታደሮች በምሽት መጥተው ካምፑን በመክበብ ዋናውን በር በመስበር ያገኙትን ሁሉ በዱላ መደብደብ እንደጀመሩ ገልጾ በወቅቱ የ70 ዓመት አዛውንት መደብደባቸውን እና አንድ አይነስውር አፍነው መውሰዳቸውን ተናግሯል።
እሱ ካለበት ፀሃዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ 400 ሰዎች መወሰዳቸውን አስረድቷል።
የመከላከያ ቃል አቀባይ፣ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት መልዕክት ቢቀመጥላቸውም ምላሽ አልሰጡም ብሏል ሮይተርስ።
የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ ቴዎድሮስ አረጋይ ፥ ጥቂት መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ክሱን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሮፖጋንዳ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።
ያንብቡ : telegra.ph/Shire-05-25

4G LTE በምስራቅ ኢትዮጵያ !
ኢትዮ ቴሌኮም ምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የሞባይል ኢንተርኔት በተሻለ ፍጥነት ማስጠቀም የሚችለውን 4G LTE Advanced የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ፦ ድሬዳዋ ፣ አይሻ እና ጭሮ ከተሞች እንደሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ÷ በምስራቅ አካባቢ ለሚገኙ ከ330 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።
ይህም የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሶስት (3) ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት እስካሁን በ103 ከተሞች የ4G ኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቧል ብለዋል ወ/ሪት ፍሬህይወት።
የሞባይል አገልግሎት አካታች በመሆኑና ከድህነት ለመውጣትና ለተሻለ ኑሮ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ድርጅቱ ከታሪፍ አንፃር ከሦስተኛው ትውልድ የአገልግሎት ታሪፍ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስታውቀዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ሪጅን ከ1.3 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት።
#ኤፍቢሲ

#ETHIOPIA🇪🇹
የግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ መግለጫ👆
"ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ" የተሰኘው የኩባንያዎች ጥምረት ኢትዮጵያ ውስጥ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት እድሉን በማግኘቱ ደስ እንደተሰኝ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
ጥምረቱ፥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት በሌሎች አገራት ያስመዘገበው ለውጥ በማምጣት ለባለአክሲዮኖች ቀጣይነት ያለው የኢንቨስትመንት ትርፍ እንደሚያስገኝ እምነት እንዳለው ገልጿል።
የሳፋሪኮም ፣ የቮዳኮም ግሩፕ ፣ የቮዳፎን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የሱሚቶሞ ም/ፕሬዜዳንትና CDC አፍሪካ ኃላፊ ያስተላለፉት መልዕክት በመግለጫው ላይ ተያይዟል።

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,823 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 282 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነ ተገኝተዋል ፤ በዚህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 269,782 ደርሰዋል።
በ24 ሰዓት ውስጥ የ9 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,093 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,717,481 ደርሰዋል።

#EuropeanUnion
የአውሮፓ ህብረት ኢንተርናሽናል ፓርትነርሺፕ ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይን ከህብረቱ የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ጋር በመሆን ከአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር መነጋገራቸውን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።
ውይይታቸው ትኩረቱን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዳደረገ ገልፀዋል።
ገንቢና ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ያሉት ኮሚሽነሯ፥ በትግራይ ያለውን ቀውስ ለማቆም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትብብርና የተቀናጀ አካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ከአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር ተስማምተንበታል ብለዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ ባለስልጣናት፣ በአማራ ክልል አስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅር መሪዎች፣ በወንጀል የተሳተፉ የTPLF መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ እና ለኢትዮጵያ መንግስት በምትሰጠው የምጣኔ ሃብትና የደህንነት ድጋፍ ዕቀባ መጣሏ ይታወሳል።
አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም ሌሎችም እንዳይከተሉ ስጋት ያደረባቸው አካላት በተለያየ አጋጣሚ ስጋታቸውን እያገለፁ ነው።
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ማዕቀብ ለማንም ጠቃሚ እንዳልሆነና በማገናዘብ የተወሰነ እንዳልሆነ፣ በቀጠናው ሽብርተኞችን በመከላከል ረገድ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው ጉዳቱም ለአሜሪካም ጭምር የሚተርፍ እንደሆነ አስገንዝባለች።
ኢትዮጵያ አማሪካ ውሳኔዋን ታጤነዋለች ብላ ተስፋ እንደምታደርግም አሳውቃለች።
በተጨማሪ የአገር ነፃነት እንዲሁም ሉአላዊት የማይታለፍ ቀይ መስመር መሆኑንና በገንዘብም የማይቀየር የህልውና ጉዳይ መሆኑም አስረግጣ ተናግራለች።

" ስፖርት ለኢትዮጵያ ህብረት "
በዛሬው ዕለት በመዲናችን አዲስ አበባ የ2013 የቤትኪንግ አሸናፊውን ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ተዘጋጅቶ ነበር።
ቴሌቶኑ ፥ "ስፖርት ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል ነው የተዘጋጀው።
በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የፌዴራሉ መንግስት ባለስልጣናት ፣ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው ነበር።
ክልሎች፣ ባለሃብቶች ፣ ባለድርሻ አካላት ለክለቡ ድጋፍ አድርገዋል።
እስካሁን የተጠቃለለ ሪፖርት ይፋ ባይሆንም ከ162 ሚሊየን ብር በላይ ግን ቃል መገባቱን አዘጋጆች አስታውቀዋል።
ዛሬ በመዲናችን የተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ግንቦት 20 በባህር ዳር፣ ግንቦት 21 በጎንደር ከተማ ይካሄዳል ተብሎ እቅድ መያዙን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገባ ያስረዳል።