TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ አበባ : እየተካሄደ ባለው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃግብር ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች እየተካፈሉ እንደሚገኙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ስለማሳወቃቸው ከአዲስ አበባ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። @tikvahethiopia
የኢፍጣር መርሃግብሩ በሰላም ተጠናቋል።

በአዲስ አበባ የተካሄደው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃግብር በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

የኢፍጣር መርሐግብሩ ሰላም ፣አንድነት ፣ፍቅር እና የመተሳሰብ የታየበት ሆኖ ተጠናቋል ብሏል አስተዳደሩ።

በተመሳሳይ ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲካሄድ የነበረው የኢፍጣር ፕሮግራም በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት 14 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 4,776 የላብራቶሪ ምርመራ 552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,074 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 263,672 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,911 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 212,567 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 694 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,360,752 ደርሷል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...በግድቡ ጉዳይ መስጋታችሁ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ልትታገሱ ይገባል" - አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ

[ Al Ain News Agency ]

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ግብጻውያን ሊታገሱ እንደሚገባ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት የስዊዝ ቦይ አካል የሆኑ የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ባስመረቁበት ወቅት ነው።

በግድቡ ጉዳይ “መስጋታችሁ ተገቢ ነው” ሲሉ ለግብጻውያን መልዕክት ያስተላለፉት አል ሲሲ ፥ “ነገር ግን ልትታገሱ ይገባል” ብለዋል ፤ ድርድር ጊዜ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል ሲሉ አክለዋል።

“መጣደፍ” አያስፈልግም ያሉት አል ሲ ሲ “በሃገራችሁ በመሪዎቻችሁም ጭምር ልትተማመኑ ይገባል” ሲሉም ተደምጠዋል።

"የግድቡ ድርድር ጉዳይ ጊዜ፣ ትዕግስት እና ጥንቃቄን" የሚፈልግ ነው ብለዋል።

መስጋቱ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም “ችላ የማይባሉ መብቶች አሉን” ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ከግድቡ ጋር በተያያዘ የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በማስታወስም እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ እንደላቸው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የስዊዝ ቦይ በ 'ኤቨር ጊቭን' መርከብ በተዘጋበት ጊዜ በአካባቢው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር “ከግብጽ የውሃ ድርሻ ላይ ማንም አንዲትንም ጠብታ ሊነካ” አይችልም ሲሉ ንግግር ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል በአይናችን አይተናል" - የደምቢ ዶሎ ነዋሪ

በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን በደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት ኃይል መገደሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የአካባቢ የመንግሥት ባለስልጣናት የወጣቱን መገደል አረጋግጠዋል። ወጣቱ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል።

የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የደምቢ ዶሎ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት፥ "ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና የ 'አባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ" ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል።

ጽ/ቤቱ፥ ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር 'በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል' ብሏል።

የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ ፥ ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ብለዋል።

"ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ገልፀዋል።

ወጣቱ ለፍርድ ሳይቀርብ ለምን መሰል እርምጃ ተወሰደበት ?

የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ ወጣቱ ለፍርድ ሳይቀርብ ለምን እርምጃ ተወሰደበት በሚል ከቢቢሲ ተጠይቀው ፥ ወጣቱ 'ወንጀለኛ መሆኑ ተረጋግጧል' ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም።

አንድ ደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-05-12

@tikvahethiopia
#እንዳትደናገጡ

1 ሺ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ግንቦት 5/2013 እንደሚከበር ትላንት መገለፁ ይታወሳል።

ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳሳወቀው በዓሉ በሚከበርበት እለት ለበዓሉ ድምቀት ከጧቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል።

ይህን ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካለት እንዲያውቁት ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !

በአ/አበባ ስታድዮም የሚደረገው የ1442ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች ፦

- ከ22 ወደ መስቀል አደባባይ
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከመስቀል ፍላወር አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኮካ ኮላ በከፍተኛው ፍ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከበርበሬ በረንዳ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቀድሞ ፈረሰኛ ፖሊስ በጌጃ ሰፈር ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ
- ከተ/ኃይማኖት በጥቁር አንበሳ ወደ ጎማ ቁጠባ
- ከአትላስ ወደ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ ናቸው።

አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ተባባሪ እንዲሆኑና በተገለፁት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መልዕክት ፦

- ህዝበ ሙስሊሙ ወደ ኢድ ሶላት ሲጓዝ ከዕምነቱ አስተምሮት ውጭ የሆኑ መልዕክቶች ፣ ከበዓሉ ዓላማ ጋር ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን ይዞ መምጣት የተከለከለ ነው።

- ምዕመኑ ለፀጥታ አካላቱ የፍተሻ ተግባር ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም እና ለማንኛውም ፖሊሳዊ አገልግሎት በአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም ይቻላል።

@tikvahethiopia
በእስራኤል እየሆነ ስላለው ጉዳይ ምን ማወቅ አለብኝ ?

- ከሰሞኑን በእየሩሳሌም የተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በSheikh Jarrah ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ለአይሁድ ሰፋሪዎች ሊያስለቅቁ ነው የሚል ስጋት መደቀኑ ነው።

- አል-አቅሳ መስጊድ ውስጥ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በፀሎት ላይ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ተጋጭተው በርካቶች ተጎድተዋል።

- ከአርብ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል ፤ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎችም ቆስለዋል።

- ከሰኞ ጀምሮ 53 ፍልስጥኤማውያንና 6 እስራኤላውያን ተገድለዋል። 13 ፍልስጥኤማውያን ህፃናት ይገኙበታል።

- ሀማስ ከ1500 በላይ ሮኬቶች ወደእስራኤል ከተሞች አስወንጭፏል፤ እስራኤል አብዛኛውን ብትከላከልም፤ አንዳንዱ ውድመት አድርሷል፤ የሰው ህይወት አጥፍቷል።

- ሀማስ የፈፀመው ጥቃት ከእስራኤላውያን በተጨማሪ አንድ የህንድ ዜጋ ገድሏል።

- የእስራኤል በመቶዎች ይቆጠራሉ የተባሉ የአየር ጥቃቶች በመፈፀም ጋዛ የሚገኙ የመኖሪያ ህንፃዎችን አውድማለች፤ የሰው ህይወት አጥፍታለች።

- የተለያዩ አለም ሀገራት እስራኤልን በፍልስጤማውን ተቃዋሚዎች ላይ እንዲሁም በአልአቅሳ መስጊድ የወሰደችውን እርምጃ ኮንነዋል።

- የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ውጥረቱ እንዲረግብ እየተማፀኑ ነው።

- ተመድ በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂዎች መካከል በጋዛ ሰርጥ የተነሳው ግጭት ወደ ለየለት ጦርነት እንዳያመራ ሰግቷል።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/East-Jerusalem-05-12

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia