TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩ ታሰሩ !

በኮንሶ ዞን ከምርጫ ጋር በተያያዘ ልዩ ልዩ የወንጀል ድርጊቶችን ፈፀሙ ተብለው የተጠረጠሩ 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮንሶ ዞን ምርጫ ክልል ጽ/ቤት አስታወቀ።

የወንጀል ድርጊቱ ተባባሪዎች ናቸው የተባሉ 5 ሰዎች ላይ መጥሪያ ወጥቶባቸው ከህግ ፊት እንደተሰወሩ የተገለፀ ሲሆን በጠቅላላ 27 ሰዎች በወንጀል ድርጊት መጠርጠራቸው ተገልጿል።

ህብረተሰቡ ከህግ ፊት የተሰወሩትን 5ቱ ተጠርጣሪዎች በታዩበት አጋጣሚ ለፖሊስ አካላት ጥቆማ እንዲታደርግ ምርጫ ክልሉ ጠይቋል።

የወንጀል ድርጊት ፈፀሙ የተባሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ፦

- የምርጫ ጣቢያው አስፈፃሚዎችን ማስፈራራት፣

- የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮችንና ምርጫ ምልክት መቅደድ፣

- ዛቻ

- የግድያ ሙከራ እና በየምርጫ ጣቢያ የምርጫ ሁኔታን በማወክ የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል።

6ኛው አገራዊ ምርጫ ሂደት ለማደናቀፍ የተሰማሩ ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው ተጣርቶ፣ ክስ ተመስርቶባቸውና ለፍርድ ቤት የተላለፈ እንደሆነ ተገልጿል።

የምርጫ ክልል ፅ/ቤቱ ሂደቱ በአስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።

መረጃው ከኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ !

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው ፦

- የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከአሜሪካ እና ሩሲያ የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመታዘብ እንደሚመጡ አሳውቀዋል።

- ከአውሮፓ ህብረት 6 አባላትን የያዘ ቡድን፣ ከአሜሪካ 2 ተቋማት የተውጣጣ እና ከሩሲያና የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን የሚታዘቡ ባለሙያዎች ይመጣሉ ብለዋል።

- የአውሮፓ ህብረት ቀድሞ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ላይ የኢትዮጵያ አቋም አልተቀየረም።

- በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀፍሪ ፊልትማን ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ብለዋል።

- ጄፍሪ ፌልትማን ከምክትል ጠ/ሚር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በህዳሴ ግድብ ድርድር እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልፀዋል። ፌልትማን የድርድሩ ሂደት በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቋጭ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል ብለዋል።

- የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሲሼኬዲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚካሄደውን ሰላማዊ ድርድር ማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ ብለዋል።

- ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሲሼኬዲ ኢትዮጵያ ሳይመጡ በፊት በካይሮ እና ካርቱም ተመሳሳይ ውይይት ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኒጀር በነበራቸው ቆይታ፥ በሃገራዊ ምርጫ፣ በህዳሴ ግድብ ድርድር እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የተሳካ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvaahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'1 ሺ 442 ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በአደባባይ ይከበራል'

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ አብሮነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

1 ሺህ 442 ኛው የኢድ በዓል በአደባባይ እንደሚከበር ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት በኮቪድ-19 ምክንያት የኢድ አልፈጥር በዓል በመስጊድ እንዲከበር መደረጉን አስታውሰው ፤ ዘንድሮ መንግስት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች በሰጡት መመሪያ መሰረት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ከመስጊድ ውጭ በአደባባይ እንደሚከበር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ አሳውቀዋል።

በዓሉን በመከባበርና በሰላም ማክበር እንደሚገባ የተናገሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር፣ "ህዝበ ሙስሊሙ የተቸገሩ ወገኞችን በመደገፍ አብሮነቱን ሊያሳይ ይገባል" ብለዋል።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን በሰላም አክብረው መመለስ እና ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ማሳየት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ መረጃ ፦

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የዛሬው የአፍጥር ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ስርዓቱን ያዘጋጁ ወገኖችና የመንግስት አካላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ሊሰሩ እንደሚገባም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ኢድ አል ፈጥር'

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች ለ1,442ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን የተመኘው ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ የኢድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 3 ማታ ከታየች ነገ ረቡዕ ግንቦት 4 የኢድ አል ፈጥር በዓል ይሆናል።

ነገር ግን ጨረቃ ዛሬ ማታ ካልታየች በዓሉ ሀሙስ ግንቦት 5 ይሆናል ብሏል።

ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ፥ ሙስሊሙ ማህበረሰብና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዳራ በማለት በዓሉ የሰላም እና የፍቅር ይሆን ዘንድ ተመኝቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Update

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት የሆኑትን ፌሊክስ ቲሺኬዲን እና የልዑካን ቡድናቸውን በጠ/ሚ ጽ/ቤት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከፕሬዜዳንቱ እና ልዑካቸው ጋር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ የሆኑ መፍትሄዎችን በመፈለግ እንዲሁም በአሁኑ የህብረቱ ሊቀመንበር አመቻችነት በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የድርድር ሂደት ቁርጠኛ መሆኗን በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡

- የታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የትብብር እና የጋራ ልማት ተምሳሌት ሊሆን እንደሚችል እና በሁለቱም ሀገራት ላይ ምንም ጉዳት በማያስከትል መንገድ እንደሚከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ጽኑ አቋም አስረድተዋል፡፡

- በትብብር መርህ ማህቀፍ [ ዴክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ ] መሠረት ለሁሉም ወገኖች የሚጠቅም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት ደግመው ገልፀዋል።

#PMOffice

@tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !

1442ኛ የረመዳን ጾምን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ የኢፍጠር ስነ-ስርዓት ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

የኢፍጠር ፕሮግራሙ በሰላም እንዲከናወን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ከባምቢስ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና የሚካሄድ በመሆኑ በወቅቱ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎማ ቁጠባ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድርስ ዝግ መሆኑን ኮሚሽን ገልፆ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ፎቶ : ሶሻል ሚዲያ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Update

“ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ”

ከሜክሲኮ - ባምቢስ ባለው መስመር ታሪካዊ ነው የተባለውን የኢፍጣር ፕሮግራም ሊካሄድ ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቆ ምዕመናን፣ የፕሮግራሙ ታዳሚያን እየተጠበቁ ነው።

በሚካሄደው “ኢፍጣሮን ያጋሩ” ልዩ የአብሮነት የኢፍጣር እንዲሁም የዱዓ ዝግጅት ላይ ለሚገኙት ተሳታፊዎች ተከታዮቹ አጭር መልዕክቶች ተላልፈዋል ፦

- ማንኛውም ፕሮግራሙን ለመታደም የሚመጣ ግለሰብ ለፀጥታ አካላት ለፍተሻ ከመተባበር ባለፈ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።

- ሁሉም የፕሮግራሙ ታዳሚ የኮቪድ መከላከያ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፤ ሳኒታይዘርና ማስክ እንዳይለየው።

- ምዕመኑ የራሱን መስጋጃ በመያዝ እንዲተባበር።

- ከህጋዊ ሰንደቅ አላማ ውጭ ይዞ ወደቦታው መሄድ አይፈቀድም ፤ ተንኳሽ እና ሌሎች ወገኖችን ሊያስከፋ የሚችል ምንም አይነት ጥቅስ መያዝ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

- ከታሰበው ቁጥር በላይ ታዳሚ ሊገኝ ስለሚችል ለኢፍጣሩ የሚሄድ ሰው ከተቻለ የየራሱን ማፍጠሪያ ይዘን ቢመጣ መልካም ነው ተብሏል።

መልዕክቱ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች እና አስተባባሪዎች የተላከ ነው።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaaBot
ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ክፍያ አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያካሔደ ነው !

ኢትዮ ቴሌኮም ‹‹ቴሌብር ›› የተሰኘ ለማህበረሰቡ ምቹና ሁሉን አካታች የገንዘብ ማስተላለፊያ እና የመገበያያ ዘዴ የሆነውን የሞባይል ገንዘብ (mobile money service) አገልግሎት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እያካሄደ ይገኛል፡፡

አጭር መረጃ ስለ "ቴሌ ብር" አገልግሎት ፦

- የገንዘብ ማስተላለፊያ እና የመገበያያ ዘዴ የሆነው የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ደንበኞች ስልካቸውን በመጠቀም ብቻ ገንዘብ እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉና ግዢ እንዲፈፅሙ ያስችላል።

- "ቴሌብር" የክፍያ ስርዓት ደንበኞች ካሽ ወይም ቼክ ሳያስፈልጋቸው ዘርፈ ብዙ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ ያደርጋል።

- በሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም የትስስር መንገዶች ላይ ገንዘብ መላላክን፣ ለዕቃና አገልግሎቶች ግዢ የሚደረጉ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል።

- የትምህርት ቤት፣ የውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዲሁም ሌሎች መሰል ክፍያዎችን በስልክ መክፈል ያስችላል።

- በኢትዮ ቴሌኮም ለሚቀርቡ እንደ አየር ሰዓት ግዢ ላሉ አገልግሎቶች ክፍያን ለመፈፀም ያስችላል።

- ከሀገር ውጪ ካለው ዳያስፖራ ገንዘብ ለመቀበል፣ ገንዘብ ለመቆጠብ፣ ብድር ለማግኘት እና የባንክ አካውንት ከቴሌብር ጋራ እንዲተሳሰር የሚፈቅድ ነው።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ ?

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለ "ቴሌ ብር" ለመመዝገብ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ያለበት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው ወደ ቴሌብር ወኪሎች አልያም ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በማምራት መመዝገብ ይችላሉ።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia