TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ ኢትዮጵያ ላይ ይወድቅ ይሆን ? ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

የቻይናው 5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ መሬት ለመምዘግዘግ ምድርን በመሽከርከር ላይ ይገኛል።

5 ቢ ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ ከሆነበት ከሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. እንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት በመሬት ዙሪያ እየተሸከረከረ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት አስታውቋል።

ኢንስትቲዩቱ እንዳስታወቀው በመሬት ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅበት ጊዜ 90 ደቂቃ ሲሆን ፍጥነቱም በስዓት 28 ሺህ ኪ.ሜ ይደርሳል ነው ያለው።

እንቅስቃሴው መደበኛ ያልሆነ ሲሆን ከፍታው ከምድር ዝቅ ሲል እስከ 170 ኪ.ሜ. ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 370 ኪ.ሜ. ይደርሳል ተብሏል።

ሎንግ ማርች ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል ?

በኢትዮጵያ ላይ ስብርባሪው የማረፍ እድል አለው የለውም የሚለውን እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው ሮኬቱ መሽከርከሩን አቁሞ ወደ ከባቢ አየር መግባት እና ወደ መሬት መምዘግዘግ ከጀመረበት ቅጽበት አንስቶ ነው፡፡

ከዚህ ጊዜ እንስቶ ስብርባሪው ወደ መሬት ለመድረስ የሰዓታት ጊዜ ስለሚኖረው ቦታው እንደታወቀ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል።

ባሉበት አካባቢ ስብርባሪው እንደሚደርስ ከታወቁ በእግርም ሆነ በተሽከርካሪ የሚደረግ እንቅስቃሴን መገደብ፤ ጠንካራ ከለሳ ወይም የላይ ሽፋን ባለው ስፍራ ስር መሆን፣ ድንገት ስራ ላይ ከሆኑ ሔልሜት ማድረግ እና የመሳሰሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ ይገባል ሲል ነው ኢንስትቲዩቱ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ https://telegra.ph/Fana-Broadcasting-Corporate-05-08

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጠ !

ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ ከፍተኛ አቤቱታ የቀረበበት በሶማሌ ክልል እየተከናወነ ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

በሂደቱ ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቲታዎችን አውርበዋል።

ቅሬታ ያቀረቡት ኦብነግ፣ ነጻነት እና እኩልነት፣ ኢዜማ እና የግል እጩ ተወዳዳሪ፣ ሲሆኑ ህጋዊ ያልሆነ የምዝገባ ሂደትን የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲታዩ ነበር።

ቦርዱ በሚዲያ ሞኒተሪንግ ክፍሉ ተሰበስቦ ቀርቦለት ምስሎቹን እና ቪዲዮዎች መመልከቱን ገልጿል።

ቦርዱ ያሉትን ሁኔታዎች በመመርመር በሱማሌ ክልል የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት ምዝገባ እንዲቆም ወስኗል።

* የምርጫ ቦርድ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ምን ያህል መራጮች ተመዘገቡ ?

እስከሚያዚያ 29/2013 ዓ.ም ድረስ 31,724,947 መራጮች በ43,017 የምርጫ ጣቢያዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

• ኦሮሚያ - 14,301,855
• አማራ - 5,205,011
• ሶማሌ - 3,844,129
• ደቡብ - 3,496,892
• አፋር - 1,712,991
• ሲዳማ - 1,329,490
• አዲስ አበባ - 1,212,073
• ጋምቤላ - 272,810
• ድሬዳዋ - 177,519
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 155,913
• ሐረሪ - 16,264

እስካሁን ባለው ከተመዝጋቢዎቹ መካከል 54% ወንዶች ሲሆኑ 46 % ሴቶች ናቸው።

ምንጭ ፦ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት መገለጫ ሲዳሰስ !

[በጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ/DW]

የመግለጫው ዋነኛ ጉዳዮች የነበሩት፦

- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር
- የሱዳን ወረራ እና ያልተገባ ጫና
- 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ

የታላቁ የህዳሴ ግድብን ግንባታ በተመለከተ ግብፅ በውሃ ላይ ምንም አበርክቶ ሳይኖራት እያሳደረች ያለው ጫና ተገቢነት እንደሌለው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አሁንም ድርድሩን በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ማስቀጠል እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

አምባሳደር ዲና የሁለተኛው ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ግብፅና ሱዳን በሙሌቱ ላይ ስምምነት ካልደረሱ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁ አምባሳደሩ ተከታዩን ምላሽ ነው የሰጡት፦

"በ3ቱ ሀገሮች በ2015 በሱዳን ካርቱም በተፈራረሙት የመርሆች መግለጫ መሰረት የግድቡ ሙሌት የግድቡ የስራ ሂደት አካል ነው። ስለዚህ የውሃ ሙሌቱ የግድቡ አካል ነው። ግድብ ከገነባህ ውሃ መሙላትህ እርግጥ ነው፤ ያ ነው ሊሆን የሚችለው ፤ በመጀመሪያው ዙር የግድቡ ሙሌት የሆነውም ይኸው ነው። አሁንም ተስፋ የምናደርገው በአሞላሉ እና በሂደቱ ላይ እንደምንስማማ ነው።"

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብን አስመልክቶ ሱዳን ከሰሞኑ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ላይ የባለቤትነት ጥያቄን ማንሳቷን አውግዘዋል።

በተለይ የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ አስፈፃሚነት ውስጥ መግባቱን አሳይቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩ አሁንም #በሰላም እንዲፈታ ግፊት ማድረጓን ቀጥላለች ብለዋል።

ምርጫ 2013 በተመለከተ አምባሳደር ዲና ፥ ከትላንት ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መስማማቱን አሳውቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/MFA-Ethiopia-05-08

@tikvahethiopia
'ከሟቾቹ መካከል 14ቱ ከኦሮሚያ ክልል ናቸው'

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ31 ዜጎቿ ህይወት በኮቪድ-19 ያለፈ ሲሆን ከሟቾች ውስጥ 14ቱ ከኦሮሚያ ሪፖርት የተደረጉ መሆኑን ከክልሉ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦ ባለፉት 24 ሰዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው 5,393 የላብራቶሪ ምርመራ 637 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 262,217 አድርሶታል።

ትላንት 1,444 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 208,314 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 50 ሺህ 030 ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ፤ 749 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

የኮቪድ-19 ክትባትን በተመለከት ፦ ክትባት የወሰዱ ዜጎች 1,290,828 መድረሳቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
'የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን ተከታተሉ'

ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትላትን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity እንዳሳወቀው የዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች በምን መልኩ በምርጫ ይሳተፉ ? በሚለው ላይ እስካሁን በሚኒስቴሩ ደረጃ ምንም የተወሰነ ውሳኔ የለም።

ነገር ግን የተለያዩ ኒቨርሲቲዎች በውስጥ ማስታወቂያ ከምርጫው በፊት 1 ሳምንት ከምርጫው በኃላ 1 ሳምንት ተማሪዎቻቸውን እንደሚበቱ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ሌሎች ደግሞ በውስጥ ማስታወቂያቸው "ከምርጫው በፊት ተማሪዎች ይበተናሉ" ስለሚባለው ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደለ እንዲሁም የሚናፈሰው መረጃም ውሸት እንደሆነ በመግለፅ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እያሳበቡ ይገኛሉ።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆናችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ተማሪዎች በምን መልኩ ነው በምርጫው የሚሳተፉት ? ለሚለው ጉዳይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር / ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ መረጃ ሲላክልን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

እስከዚያው ግን በተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች ላይ ሆነ የፌስቡክ ገፆች ላይ የሚወጡትን የተለያዩ መረጃዎች በመቀባበል ሳትረበሹ #በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታችሁን እየቀጠላችሁ ይፋዊ የሆነውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ትጠብቁ ዘንድ አደራ እንላለን።

አዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመዳቢ ተማሪዎች በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት በጠየቅ እናሳውቃለን። በተጨማሪም የ2013 ሀገር አቀፍ ፈተና ሂደትን ከትምህርት ሚኒስቴር ጠይቀን እናሳውቃለን።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሉበርካታ የተጣረሱ መረጃዎች እንዳትደናገሩ።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
በአ/አ በአንድ ግለሠብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተደበቀ ከ4 ሺ በላይ የተለያዩ ጥይቶች እና አንድ ሽጉጥ ተያዘ !

ዛሬ ምሽት የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በአንድ ግለሠብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተደበቁ ከ4 ሺህ በላይ የተለያዩ ጥይቶች እና አንድ ሽጉጥ ተይዟል።

ፖሊስ እንዳለው የተደበቀው ጥይት እና ሽጉጥ የተያዘው በህዝብ ጥቆማ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅንጅት በተሰራ ስራ ነው።

የከተማዋን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ እኩይ አላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የጦር መሳሪያዎችን በህገ ወጥ መንገድ ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ በህዝብ ጥቆማ እና በፀጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሚገኙ ፖሊስ ያስታወሰ ሲሆን ለዚሁ ሀገርን የማፍረስ አላማ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተጠርጣሪ ነው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጎፋ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተያዘው ሲል አሳውቋል።

ግለሰቡ በመኖሪያ ቤቱ ደብቆ ያስቀመጣቸው ፦
- 3007 የማካሮቭ ሽጉጥ፣
- 1320 የብሬን፣
- 05 የክላሽንኮቭ በአጠቃላይ 4 ሺህ 332 ጥይቶች እንዲሁም አንድ የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በተጨማሪም ባዶ የጥይት ማሸጊያ ሳጥኖች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል ገልጿል።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብሏል።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አጠራጣሪ የሆነ ነገር ሲያጋጥመው በመረጃ የስልክ ቁጥሮች 0111110111 ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ደውሎ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ቻይናው ሮኬት ማርች 5B"

ቻይና ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ስብርባሪዎች በሕንድ ውቂያኖስ ላይ ማረፋቸውን አስታውቃለች።

የሮኬቱ አብዛኛዎቹ ክፍሎች ወደ ምድር በሚምዘገዘጉበት ወቅት ተቃጥለው አየር ላይ የቀሩ ሲሆን አንዳንድ ስብርባሪዎች ግን በታሰበው ቦታ ላይ ማረፋቸውን የቻይና ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ማርች 5ቢ ምንድነው ?

'ማርች 5ቢ' ለሮኬቱ የተሰጠው ስያሜ ነው። ሮኬቱ ባሳለፍነው ወር መገባደጃ ላይ ነበር ቻይና በሕዋ ላይ ለመስራት ላሰበችው ማዕከል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ይዞ የተወነጨፈው።

18 ሺህ ኪሎ ግራም ይመዝናል። በአስርት ዓመታት ውስጥ ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደ ምድር የሚወድቅ ግዙፍ ቁስ ነው ተብሎ ነበር።

የዚህ ሮኬት ስብርባሪ አካላት ደግሞ በትክክል መቼ እና የት እንደሚወድቁ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም መባሉ ስጋት ፈጥሮ ነበር።

ቻይና እየተወቀሰች ነው ፤ ለምን ?

ቻይና እየተወቀሰች የሚገኘው የሮኬቱን ስብርባሪዎች መውደቂያ ቦታ እና ትክክለኛ ሰአት መቆጣጠር አለመቻሏ ግድየለሽነቷን የሚያሳይ ነው በሚል ነው።

አገሪቱ ግን ስብርባሪዎቹ ዓለማቀፍ የውሃ ክልል ውስጥ እንደሚወድቅ አውቅ ነበር ብላለች።

ቻይና ለምንድነው የራሷን ከህዋ ጣቢያ ምትገነባው ?

በአሁኑ ጊዜ በህዋ ምህዋር ላይ የሚገኘው ብቸኛው ዓለም አቀፍ የህዋ ምርምር ጣቢያ፣ በእንግዝኛ ምሕጻሩ አይኤስኤስ (ISS) ነው።

ቻይና በዚህ ጣቢያ ውስጥ አልታቀፈችም።

ለዚህም ነው ቻይና በአውሮፓውያኑ 2022 የራሷ የህዋ ጣቢያ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየሰራች የምትገኘው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፀጥታ ኃይሎች ምረቃ : * ፌዴራል ፖሊስ ! ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ ምልምል የፖሊስ አባላት አስመርቋል። በጦላይ ወታደራዊ ማስልጠኛ ማዕከል ሰልጥነው በዛሬ እለት ለምርቃት የበቁት 6 ሺህ 431 ምልምል ፖሊሶች ናቸው። ከእነዚህ መካከል 792ቱ የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት መሆናቸው ታውቋል። * የአማራ ክልል ፖሊስ ! የአማራ ክልል…
የቀጠለው የፀጥታ ኃይሎች ምረቃ ፦

ዛሬ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ልዩ ኃይል ፖሊሶችን አስመርቋል፡፡

በተጨማሪ የልዩ ኃይል ፖሊሶች መኪና አሽከርካሪዎችም ተመርቀዋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT