TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ_ይደረግ #ኮሌራ

በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን በሚገኘው አሚባራ ወረዳ የኮሌራ በሽታ ተከስቶ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 128 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

🗞ቀን ሰኔ 25/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ እስካሁን 17 ሰዎች በኮሌራ ሞተዋል፤ በኮሌራ ተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 871 ደርሷል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችልም ትንብያዉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና #እንዲጠነቀቅ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በአብዛኛዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጥሩ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ትንበያዉ የሚያመለክት ሲሆን ይህም ለግብርናዉ የስራ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ታምኖበታል፡፡ ቀድመዉ የተዘሩ እና በእድገት ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የሚገኘዉ እርጥበት በጎ ሚና አለዉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ለቋሚ ተክሎች የዉሓ ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላለቸዉና ለአርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች የግጦሽ እና የመጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

በቀጣይ የሚኖረዉ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተፋሰሶች ላይ ለዉጥ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ በአብዛኛዉ የተከዜ፣ የኦሞ ጊቤ የአባይ፤ የላይኛዉና የመካከለኛዉ አዋሽ እና አፋር ደናክል ተፋሳሾች ከፍተኛ እርጥበት ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
ፎቶ: ፋይል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል!

በቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ በአብዛኛው የአባይ፣ የተከዜ፣ የባሮ ኦኮቦ፣ የኦሞ ጊቤ፣ የላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የአዋሽ የላይኛውና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች፤ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ ሸበሌ፤ የላይኛው አፋር ደንከል፤ ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን እንዲሁም ታችኛው አዋሽና ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄና ክትትል እንደሚያስፈልግ ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከነሃሴ 5/ 2011 እስከ ነሃሴ 14 /2011 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት ስምጥ ሸለቆዎች፣ ተፋሰሶች አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል እንዲሁም መጠነኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ትንበያው ይጠቁማል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-15-2
#ጥንቃቄ_ይደረግ

"ሱሉልታን ከአ/አ የሚያገናኘው መንግድ በጎርፍ በመሙላቱ መኪናዋች ቆመዋል።" #TIKVAH_ETHIOPIA #AHMUU

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን ለ 'አፍሪካ ዋንጫ' ማለፋን ተከትሎ በርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን ደስታቸውን ለመግለፅ ተሰባስበው አደባባይ እየወጡ ነው ፥ ይህ ሁኔታ አሁን እጅግ ከፍተኛ እና አሳሳቢ ደረጃ የደረሰውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሊያባብሰው ስለሚችል ጥንቀቄ ሊደርግ ይገባል።

ይህ መልዕክት በስልካችሁ የደረሳችሁ የቲክቫህ አባላት ሰዎች ከተሰባሰቡበት ቦታ እንድትረቁ / የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ አጥብቀን አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ጥንቃቄ_ይደረግ

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ የትንሳኤ በዓል ሲከበር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።

በተለይ በምግብ ማብሰል ወቅት የኤሌክትሪክ ሃይል ጫና ሊፈጥር የሚችል የሶኬት አጠቃቀም እና የጋዝ ስሊንደሮች አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል።

በተጨማሪ ሕብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት የከሰል፣ የሻማና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለበት መክረዋል።

የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን በትንሳኤ በዓል 1 ሺህ 112 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 27 ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ 19 አምቡላንሶችና ሌሎች አደጋን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 9 ወራት በአዲስ አበባ ከደረሱ 249 የእሳት አደጋዎች መካከል 42ቱ በኤሌትሪክ ንክኪ የተከሰተ ሲሆን የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ያስታወሱት አቶ ጉልላት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ የ50 ሰዎች ሕይወት ማትረፍ መቻሉን አመልክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 249 የእሳት አደጋ እንዲሁም 111 ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መካከል 313 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሆን 47ቱ ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተከሰቱ ናቸው ብለዋል።

በአጠቃላይ በደረሱ አደጋዎች ከ299.5 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት የወደመ ሲሆን በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተደረገ ርብርብ ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።

አደጋዎች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ ይችላል። (ENA)

@tikvagethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ !

እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ከውዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።

በብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በሚያዚያ ወር ትንበያ መሰረት ፦

- በኦሮሚያ፣
- በጋምቤላ፣
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- በአማራ
- በመከለኛውና እ ምዕራብ ትግራይ ክልል ፣
- በደቡብ ክልል መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል።

በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ከዝናቡ መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

በብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ትንበያ መሰረት በቀሪው የበልግ ወቅት ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች መለየታቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ_ይደረግ ! እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ከውዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ። በብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በሚያዚያ ወር ትንበያ መሰረት ፦ - በኦሮሚያ፣ - በጋምቤላ፣ - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ - በአማራ - በመከለኛውና እ ምዕራብ ትግራይ ክልል ፣ - በደቡብ ክልል መደበኛ እና…
#ጥንቃቄ_ይደረግ !

የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ትንበያ መሰረት በቀሪው የበልግ ወቅት ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ያላቸው አካባቢዎች ፦

- በኦሮሚያ ክልል ፦ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ የጎርፍ ስጋት መኖሩን ተጠቁሟል፤

- በሶማሌ ክልል ፦ ሸበሌ ፣ አፍዴር፣ ሊበን፣ ዶሎ ፣ ፋፋን፣ ሲቲ፣ ዳዋ አንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊኖር እንደሚችልም ተገምቷል፤

- በደቡብ ክልል ፦ በሀዲያ ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በዳውሮ ፣ በሰገን፣ በስልጤ፣ ጉራጌ አንዳንድ አካባቢዎችም የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል፤

- በሲዳማ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ ስጋት አለ።

- በድሬዳዋ ከተማና የገጠር ቀበሌዎች የጎርፍ ስጋት አለ።

ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የዝናብ መጠን መጨመርን ተከትሎ የጎርፍ ስጋት አለ።

ለጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ለሆነ ማህበረሰብ የቅድመ ጥንቃቄ እና ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ፎቶ : ፋይል
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia