TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የድሬዳዋ የሰዎች ህይወት አለፈ።
በድሬደዋ ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ግንብ ፈርሶ በመኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በመብረቅ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
በቀበሌ 08 ልዩ ስሙ "ለገሃሬ ከመንገድ በላይ" ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ተደርምሶ በአቅራቢያው ባለው መኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ህይወታቸው ያለፈው የ12 አመት ፤ የ3 አመት እና የ2 ወር ህጻን ልጅ ሲሆን የልጆቹ ወላጅ እናት እና አንድ ወንድ ልጃቸው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ።
በልጆቹ አባት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በሌላ በኩል በቀበሌ 01 "መልካ ጀብዱ" ከቀኑ በዘጠኝ ሰአት በጣለው መብረቅ የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ግቢ ውስጥ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ መብረቅ በመውደቁ በአንደኛው ግለሰብ ላይ የሞት አደጋ ሲያስከትል በሌላው ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት በመድረሱ በማርያም ወርቅ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው ሚያዝያ 24 በድሬዳዋ የአንድ ድርጅት አጥር ፈርሶ በአደጋው የዘጠኝ ሰው ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።
በቀጣይ ቀናት ዝናብ ጥሎ የጎርፍ አደጋ ሊደርስ ስለሚችል ህብረተሰቡ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።
ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Update የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ባህርዳር ገባ። በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር አለም አቀፍ ኤርፖርት አየገባ ይገኛል። በስፍራው ፦ - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር - የጠ /ሚኒስትሩ…
#Update
የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርአት በባህር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን መፈፀሙን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ስቴም ፓወር ፣ ቪዛ እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ የተሳተፉ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የምርቃ መርኃግብር ተካሂዷል።
ስልጠናውን ከተከታተሉ 200 ሰልጣኞች ውስጥ በአጠቃላይ 70 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ለመጨረሻው ዙር ከደረሱ 20 ፕሮጀክቶች በአራት ዘርፎች ለአራት አሸናፊዎች የ25,000 ብር በድምሩ የ100,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አሸናፊዎቹ በግብርና፣ በጤና፣ በኢንጂነሪንግና በአገልግሎት ዘርፍ የተመረጡ ሲሆን በጤናው ዘርፍ ኢሶፕ የተሰኘ የፈጠራ ሃሳብ፤ በግብርናው ዘርፍ ደግሞ ፖሊተሪ ፋርሚንግ ላይ የቀረበ ፕሮጀክት አሸናፊ ሆኗል።
በኢንጅነሪንግ ዘርፍ የፕላስቲክ ኮዳን ወደ ፋይበር ፕላስቲክ የሚለውጥ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ ሎሃ የተሰኘ የኦንላይን ትምህርት አገልግሎት አሸናፊዎች ሆነዋል።
የስቴም ፓወር ሥራ አሥኪያጅና ቅድስት ገብረአምላክ አሸናፊዎቹ ከተበረከተላቸው ሽልማት በተጨማሪ ወደ አገልግሎት እስኪገቡ ድረስ በቀጣይ አንድ ዓመት ስቴም ፓወር ሙሉ የቴክኒክና የሞያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በሥራ ፈጠራ ክህሎት እና በመሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው ዙር ስልጠና በቀጣይ ሳምንታት ይጀምራል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም በቀጣይ የሚኖሩ ሁነቶችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መግለጫ ፦
- መንግስት ከዚህ በኋላ ከትግራይ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ውስጥ በ14 በመቶው ብቻ ድጋፍ ያደርጋል ፤ ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት ይሸፈናል። ከዚህ ቀደም 70% ሲሸፈን የነበረው በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ነበር።
- ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ በ3 መንገድ እየተሰራ ነው።
ሶስቱ መንገዶች ፦
• ሰላም በተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ህዝቡን በማወያየት መመለስ፣
• ሙሉ ሰላም ያልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ስነልቦናዊ ችግሮችን ለማቅለል ወደዘመድ እንዲሄዱ መርዳት
• ሰላም ካልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ለተፈናቀሉት ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያን ማዘጋጀት የሚሉ ናቸው።
- ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጨማሪ 4 ተቋማት ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
- ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ አልተቻለም በሚል የሚቀርቡ ክሶችና ወቀሳዎች ከአሁን በኋላ ተቀባይነት የላቸውም።
- እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተከፍተዋል።
- “በረሀብ የሞተ ሰው የለም”፤ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ተቋማት “እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ጉዳዩን እያስጮሁት” ነው። “ልክ እንደ የመን እና ሶሪያ እርዳታ ለማግኘት ጉዳዩን እየተደረገ ያለ ሩጫ ነው።
በሌላ በኩል ፦
በሀገሪቱ ያለው የተፈናቃይ ብዛት 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሲሆን 40 በመቶ ያህሉን ለመመለስ መታሰቡን ተጠቁሟል።
አጣየ በተመለከተ፦ አማራ ክልል ውስጥ ለ50ሺ ተረጂዎች ድጋፍ እንዲደረግ ችግሩ በተፈጠረበት ወቅት ወዲያውኑ መጠየቁን ተከትሎ ድጋፉ በማግስቱ (ቅዳሜ ተጠይቆ እሁድ) እንዲደርስ ተደርጓል።
ምንጭ፦ አል ዓይን

የUN ድጋፍ ለኢትዮጵያ !
UN በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል 65 ሚሊየን ዶላር ለቋል።
ድጋፉ በተለያዩ ምክንያቶች ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ምግብ ፣ የመጠለያ ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያስችላል።
የUN ድጋፍ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ከ16 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ይውላል። ከነዚህ ውስጥ 4.5 ሚሊዮን ገደማ በትግራይ ክልል የሚገኙ ናቸው።
ከድጋፍ ውስጥ 40 ሚሊየን ዶላሩ በትግራይ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን ቀሪው በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች ይውላል።
* የUN መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

"ከ20 እስከ 30 ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችን እናስመርቃለን"
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ወንድማማችነት እና እህትማማችንነትን ለማጎልበት በማሰብና አመርቂ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች ለማበረታት እገዛ ለማድረግ ስራዎችን ጀምሮ ነበር።
በፀጥታ ችግር እና በኮቪድ-19 ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች በመዘጋታቸው መስተጓጎል ተፈጥሮ የነበር ቢሆንም ከዚህ ቀደም እንዳሳወቅነው ለሁለት (የ2012) ተመራቂዎች ስጦታውን ማበርከት ተችሏል ።
ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ ውጤት ካላቸው እና ቤተሰቦቻችን አቅም ካጠራቸው መካከል ለመመረቂያቸው እንዲሆን ለ2 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው 10 ሺህ ብር ልከናል።
እቅዱ የነበረው ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮችን ገዞት ለመስጠት የነበር ቢሆንም አልተሳካም።
ምክንያት ?
የአቅም ውስንነት ተፈጥሮ ነበር።
በፀጥታ ችግር (በተለይ የትግራይ ቲክቫህ አባላት ባሉበት ትግራይ ክልል ጦርነት በመቀስቀሱ) ምክንያት እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መነሻ ጊዜ ሰዎች አንገብጋቢ መረጃ ለመለዋወጥ በሚፈልጉበት ወቅት ማስታወቂያ ስለማናሰራጭ / ሙሉ በሙሉ ማስታወቂያ ስለሚቆም ቃል የገባነውን ለማድረግ የአቅም ውስንነት ተፈጥሮ ነበር።
ቲክቫህ ቤተሰብ ከሚሰራጩት ውስን ማስታወቂያዎች ውጭ ምንም አይነት የተለየ ድጋፍ የሌለው መሆኑ ይታወቃል።
ዘንድሮ ?
ከ20 እስከ 30 የዩኒቨርሲቲ (2013) ተመራቂ ተማሪዎችን በተለይ ጥሩ ውጤት ያላቸውን የመመረቂያ አልባሳቶቻቸውን ሙሉ ወጪ ለመሸፈን እንሰራለን።
መነሻችን ደብረ ታቦር እና ወለጋ ያደረግን ሲሆን አሁን በሌሎች 4 ዩኒቨርሲቲዎች ይቀጥላል። የትኞቹን ዩኒቨርሲቲዎች የሚለውን በቀጣይ እንገልፃለን።
በዘንድሮው ቤተሰባዊ የስራ ለመሳተፍ @tikvahethiopiaBOT መልዕክት አስቀምጡ።
#TikvahFamily❤️

"የዘንድሮው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ አይከበርም" - አቶ ደስታ ሌዳሞ
የዘንድሮውን የፊቼ ጫምባላላ በዓል የኮሮና ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል ሲባል በአደባባይ እንደማይከበር የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።
ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳትና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባውም ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ገልጸዋል።
የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ የሆነው“ ፊቼ ጫምባላላ ” ከጥንት ጀምሮ ሲከበር የቆየ መሆኑን አስታውሰው፤ በዓሉ የተጣሉትን በማስታረቅ ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለሰው ልጆችና እንስሳት ክብር በመስጠት የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑን አስረድተዋል።
“ለበዓሉ ሲባል እንስሳት የማይታረዱበት በቀያቸው በእንክብካቤ የሚያሳልፉበት እንዲሁም ዛፍ የማይቆረጥበት በመሆኑም እለቱን ልዩ ያደርገዋል” ብለዋል።
በአሁን ወቅት በፍጥነት እየተዛመተና በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያሰከተለ ባለው የኮሮና ወረርሽኝ ተዕዕኖ ምክንያት በዓሉ እንደወትሮው በአደባባይ በመሰባሰብ እንደማይከበርም ገልጸዋል።
ሆኖም በዓሉ ባህላዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ዘንድሮ ሁሉም የብሄሩ ተወላጅ በየቤቱ ሆኖ የሚያከብረው መሆኑን አመላክተዋል።
ህብረተሰቡ የዘንድሮውን ፊቼ ጫምባላላ በአልን ሲያከብር እራሱን ከኮሮና ወረርሽኝ በመከላከል ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
በተለይ ከተጣላው ጋር ይቅር በመባባል እና ከመዋደድ ባሻገር እርስ በእርስ በመደጋገፍ እንዲሆንም አቶ ደስታ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዘንድሮው የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ “ፊቼ ጫምባላላ” በዓል ከንክኪ በራቀ መልክ ሚያዝያ 29 እና 30 እንደሚከበርም ጨምረው ገልፀዋል። #ENA
@tikvahethiopiaBOT

#Egypt
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ተሰምቷል።
ማክሰኞ ግብጽ የገቡት ልዑኩ ጄፍሪ ፌልትማን ትናንት ነው የግብጹን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን ያነጋገሩት።
አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካ በግድቡ ምክንያት ለተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማግኘት ውጤታማ ሚና እንድትጫወት ጠይቀዋል ተብሏል።
ግድቡ የሃገራቸው ህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ግብጽ የውሃ ፍላጎቷን የሚጎዳን ማንንም እንደማትቀበል እንዳስታወቁ ተሰምቷል።
በተጨማሪ ፌልትማን የግብጹን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነጋገሩ ሲሆን ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥንቃቄ ለሚፈልገው ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለመሻት ከልብ እንዳሰበበት ተናግረዋል።
ፌልትማን ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በቀጣይ እንደሚጎበኙ ዶቼ ቨለ አሶሼትድ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
@tikvahethiopiopia @tikvahethiopiaBOT

#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 4,914 የላብራቶሪ ምርመራ 663 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 2,050 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 260,802 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,822 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 205,458 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 748 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,237,826 ደርሷል።
#Purpose

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ምሽት በetv ቀርበው ስለህዳሴው ግድብ ከተናገሩት ፦
- DRC ኮንጎ አመራርነቱን ከተረከበች በኃላ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እስካሁን አንድ ጊዜ ለሶስትዮሽ ድርድር ተቀምጠዋል።
- የሶስትዮሽ ድርድሩ በሁለቱ ሀገራት ምክንያት (ግብፅ እና ሱዳን) ፍላጎት ማነስ ተቋርጧል።
- ኢትዮጵያ ሁል ጊዜም ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ መቀጠል ነው።
- ኢትዮጵያ ሁሌም የምትለውን ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ አቋም ላይ እንድረስ የሚል ነው። በዋናነት በሙሌቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንስማማ እያለች ነው።
- የሙሌት ስምምነቱን በተመለከተ ግን ሱዳን እና ግብፅ አጠቃላይ ስምምነቱን ካልደረስን ካልተፈራረምን በሚል ፣ ሌሎች አደራዳሪዎችን በመፈለግ ሂደቱን እያፈረሱት ነው።
- ኢትዮጵያ አጠቃላይ ስምምነቱ በሂደት ይመጣል ብላለች። በአንዴ የሚሆን አይደለም ጊዜ ይወስዳል። በበርካታ ጉዳዮች ላይ መነጋጋረ አለብን ብላለች።
- አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ዝናብ ነው፣ ብዙ ውሃ አለ፣ ከሚመጣው ውሃ እንኳን አብዛኛውን እየተያዘ አይደለም ፤ ሙሌቱ ላይ እንስማማ የሚል አቋም ነው ያለው በኢትዮጵያ በኩል። እነሱ ግን አልተቀበሉትም።
- ግድቡ የሚሰራው ሊሞላ ነው ፤ አምና የመጀመሪያው ሙሌት ሄዷል ዘንድሮ ሁለተኛው ይሄዳል፤ ይሄ በ2015 የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ ያለ ነው ፤ ነገር ግን ይሄንንም እየተቃወሙ ነው።
- ኢትዮጵያ ሙሌቱ እና አጠቃላይ ፕሮጀክቱ እንደማይጎዳቸው እየገለፀች ነው።
- አሁን በተለይ ሱዳኖቹ ጥያቄዎቻቸው የተመለሱላቸው ይመስላል ፤ ድብቅ ፍላጎታቸው ሌላ ቢሆንም፤አንዴ የአፍሪካ ህብረትን ሚና እያሳነሱ ሌላ አደራዳሪ እየፈለጉ፤ አንዴ ሚናዎችን እንዲበረዙ መሰናክሎች እየደረደሩ ነው።
- ኢትዮጵያ ወደሁለተኛው ሙሌቱ መሄዷ የማይቀር ነው።
@tikvahethiopia

ፌልትንማን ከኤርትራ ፕሬዜዳንት ጋር ተወያዩ።
በጁፍሪ ፌልትማን የሚመራው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ኤርትራ አስመራ ገብቷል።
የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ልዑኩን በደንደን የእንግዳ መቀበያ ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።
ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ከአሜሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን እንዳስረዱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።
አምባሳደር ፌልማን በበኩላቸው በአፍሪካ ቀንድ እየታዩ ባሉ ችግሮች ዙሪያ የአሜሪካ አስተዳደር ያለውን አመለካከትና እይታ ለፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳብራሩላቸው የኤርትራው ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ገልፀዋል።
የነበረው ውይይት 4:00 ሰዓት ገደማ የወሰደ እንደነበረ የተሰማ ሲሆን ከላይ ከተገለፀው መረጃ ውጭ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች እስካሁን ይፋ አልሆኑም።

'በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ሰዓት እላፊ ታወጀ'
ምክንያት ?
የካራት ከተማ አስተዳደር እንደሚለው ከዚህ ቀደም በተናጥል ሆነ በቡድን በመደራጀት የመንግሥትና የግለሰቦች ንብረት የመስረቅና የመቀማት ድርጊቶች የዕለት ተዕለት የሌቦች እና የዘራፊዎች ተግባር ሆኖ ቆይቷል።
የጸጥታ ኃይል ይህንን "አስጸያፊ መጤ ድርጊት" ለመመከት የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ከእነዚያ ሌቦች፣ ዘራፊዎችና ቀማኞችን በብዙ ጥረት በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርጓል፣ በማድረግም ላይም ይገኛል ብሏል አስተዳደሩ።
ነገር ግን ይላል ከተማው አብዛኛዎቹ እየተሰወሩና በድብቅ እየተደራጁ ጨለማን ተገን በማድረግ በሰፈር ውስጥ እና በቀበሌያት እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤቶች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የስርቆት ድርጊቶችን ቀጥለዋል ፤ ይህንን መንግስት ደርሶባቸዋል ሲል አስረድቷል።
በተጨማሪም "6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማወክ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠልሸት ሌት ተቀን እየሰሩ ያሉ ፀረሠላም ግለሰቦች እና ቡድኖች እንዳሉ መንግስት ደርሶባቸዋል፤ ክትትል እያደረገም ይገኛል" ብሏል።
በዚህ ምክንያት ነው በካራት ደረጃ መንግሥት ሁኔታውን በማጤን ለህብረተሰቡ ደህንነት ሲባል የሰዓት እላፊ ቁጥጥር ገደብ እንዲበጅለት የተወሰነው ብሏል።
የተጣሉ ክልከላዎችን ምንድናቸው ?
- ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማለዳ 11፡00 ሰዓት መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
- ማንኛውም ባለ 2 እና 3 እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማለዳ 12፡00 ሰዓት ማሽከርከር ተከልክለዋል።
- ማንኛውም ሆቴል፣ ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Konsso-Zone-Government-05-06

*Update
የኮቪድ-19 ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተባብሷል።
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የሚከተሉት ሪፖርቶችን ተመልከቷቸው፦
- ትላንት ህንድ ውስጥ 414,433 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ 3,920 ሰዎች ሞተዋል። ህንድ በየዕለቱ አስገንጋጭ ቁጥሮችን ሪፖርት ማድረጓን ቀጥላለች።
- ብራዚል ትላንት 72,559 ዜጎቿ ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን እና 2,531 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች።
- ትላንት ከፍተኛ ሞት የተመዘገበባቸው ሀገራት ስንመለከተ፦
• አሜሪካ 860
• ቱርክ 304
• ፖላንድ 510
• ኮሎምቢያ 399
• አርጀንቲና 398
• ሩሲያ 351 ይገኙበታል።
- የአፍሪካ አቀፍ ስርጭትም ተባብሷል፤ ትላንት 12,434 ሰዎች ቫይረሱ ሲያዙ 383 ሰዎች ሞተዋል። አሁንም ደቡብ አፍሪካ 1,590,370፣ሞሮኮ 513,016፣ቱኒዝያ 317,010፣ ኢትዮጵያ 260,802 ታማሚዎችን በሪፖርት በማድረቅ የቀዳሚዎችን ቦታ ይዘዋል።
ክትባት በሚመለከት አንድ ከዛሬ የቢቢሲ መረጃ፦
የሪስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን "ስፑትኒክ" የተሰኘው ሩሲያ ሠራሹ የኮቪድ-19 ክትባት ልክ እንደ 'ክላሽንኮቭ' የጦር መሳሪካ አስተማማኝ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ፑቲን ይህን ያሉት ከአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጋር በነበራቸው የቪዲዮ ኮንፍረንስ ነው።
ትናንት የአገሪቱ ጤና ተመራማሪዎች በአንድ ዙር ብቻ የሚሰጠውን እና 'ስፑትኒክ ላይት' የሚል መጠሪያ ስላገኘው ክትባት ውጤታማነት መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ከክትባቱ ጋር ያነጻጸሩት "ክላሽንኮቭ" የተሰኘው መሳሪያ ጋር ሲሆን መሳሪያው ፤ ይህ መሳሪያ የተፈበረከው በሩሲያ ሲሆን በመላው ዓለም ዝነኛ የጦር መሳሪያ ሆኖ ቀጥሏል።
የመረጃ ግብዓት የዎርልድሜትሮ ድረገፅ፣ቢቢሲ፣CDC አፍሪካ ናቸው።

አጭር መረጃ ስለኮቪድ-19 ኢትዮጵያ መተግበሪያ፦
የኮቪድ ኢትዮጵያ መተግበሪያ በውስጡ ስለኮቪድ ቁጥጥር ፣ ህክምና እና መከላከል ማወቅ ያለብንን በ7 ኮርሶች የያዘ ሲሆን ስልጠናው ፦
- የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶቦት በቤት ውስጥ እራሳችንን ለይተን ለራሳችን ማድርግ ስለሚገባን እንክብካቤ እና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ያሳውቃል።
- ስለኮቪድ-19 ክትባት ለማወቅ እና ስልጠና ለመውሰድ ይጠቅማል።
- ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ለማውቅ ይረዳል።
- ሰልጣኞች ስልጠና እንዳጠናቀቁ በሚመዘገቡበት የስልክ ቁጥር ባላቸው የቴሌግራም አድራሻ ስልጠናውን በአግባቡ ላጠናቀቁ እና የስልጠና መመዝኛውን ከ80 በመቶ በላይ ላስመዘግቡ በጤና ሚኒስቴር የተረጋገጠ የተከታታይ ሙያ ማጎልብቻ ነጥብ ያለው ሰርተፍኬት የሚላክላቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በየ3 አመት ለሚደረገው የሙያ ፍቃድ እድሳት ነጥብ ለመጠቀም ያስችላል።
- መተግበሪያውን በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከጫኑና ስልጠናዎች ካወረዱ በኋላ ኢንተርኔት የማይፍልግ ሲሆን ስልጠናውን የሚስብ እና ለመረዳት ቀላል ለማድረግ ቪድዮዎች ተካተውብታል።
- ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የኮቪድ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ይረዳል።
መተግበሪያውን ከየት ላግኘው ?
መተግበሪያውን በስልክዎ ለመጫንና ስልጠናውን ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ - https://bit.ly/3apv5J2
#MoH #EPHI
@tikvagethiopia @tikvagethiopiaBOT

እንኳን አደረሳችሁ! TIKVAH-ETHIOPIA እንኳን ለሲዳማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን! ይህን ዓለምን ያስጨነቀ ወረርሽኝን አሸንፈን የዓለም ቅርስ የሆነውን 'ፊቼ ጨምባላላ በዓል' በአደባባይ ተሰባስበን የምናከብርበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን #ተስፋ እናደርጋለን!! በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!…
እንኳን አደረሰን !
እንኳን ለሲዳማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ ከወዲሁ እንመኛለን።
ካለፈው ዓመት ጀምሮ በዓሉ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ እየተከበረ አይደለም።
የተሻለ ጊዜ መጥቶ ፣ ይህ አስከፊ ወረርሽኝ መፍትሄ አግኝቶ ሁሉም በደስታ እንደቀድሞ አደባባይ ተሰብስቦ የሚያከብርበት ጊዜ እንዲመጣ እንመኛለን።
በዓሉን በየቤታችሁ የምታከብሩ አባላት አስፈላጊውን የኮቪድ-19 ጥንቃቄ እየተገበራችሁ እንዲሆን አደራ እንላለን።
መልካም በዓል !
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia