#Tigray
የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን የትግራይ ሪፖርት :
- በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት የተጎዱ ታዳጊዎችን ማግኘቱን ገልጿል።
- ገጠራማ አካባቢ በሚገኙ ክልኒኮች ክትትል ከተደረገላቸው ሕጻናት መካከል ሶስት እጅ የሚሆኑት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል።
- የእለት እርዳታ ከዋና ከተማዎች በዘለለ ወደ ገጠሪቱ የትግራይ ክፍል የሚደርሰው በአነስተኛ መጠን ነው።
- አንዳንድ ቤተሰቦች በቀን አንዴ ይመገባሉ ፤ በብዛት ዳቦ ብቻ ነው የሚበሉት።
- የዝናቡ ወቅት እየደረሰ ሲመጣ የሚካሄደው ጦርነት ገበሬዎችን ወደ ማሳቸው ከመሄድ በመከልከል ሁኔታው እየከፋ ሊመጣ ይችላል ሲል ገምቷል።
- የሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከቦታ ቦታ ቢለያይም ባለፉት ወራቶች አጣዳፊ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በትግራይ እየጨመረ መጥቷል። ብዙ ቤተሰቦች የሚገኙበት የምግብ ጥራት እና ብዛት መቀነሱ ብዙዎች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ መመገባቸውን በምክንያትነት ቀርቧል።
- የሰብአዊ ዕርዳታን ለማሳደግ እና ተደራሽነቱን ለማስፋፋት የሚጠይቅ አስቸኳይ ፍላጎት አለ።
MSF አሁን ላይ ምን እየሰራ ነው ?
ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን በአሁኑ ወቅት በዓዲግራት ፣ በኣክሱም ፣ በዓድዋ ፣ አቢ አዲ፣ ሽረ ፣ ሸራሮ ፣ ሁመራ እና ዳንሻ ከተሞች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ከ2021 መጀመሪያ ጀምሮ የተንቀሳቃሽ ቡድኖቹን እንቅስቃሴ ወደ ገጠር ከተሞች እና ተራራማ አካባቢዎች እያስፋፋ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MSFTigray
በትግራይ ገጠራማ አካባቢዎች ያሉ ዜጎች በክልሉ ባለው ቀውስና በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት በኩል ባለው ቸልታ ተጎድተዋል።
MSF በኣዲፍተው በተባለች መንደር ጊዜያዊ ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ከፍቷል።
የዚህ ክሊኒክ የሕክምና ባልደረቦች ትኩረትም የሚሰጡት በልጆች ፣ ነፍሰጡር ሴቶች እና የድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በትግራይ ገጠራማ አካባቢዎች ያሉ ዜጎች በክልሉ ባለው ቀውስና በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት በኩል ባለው ቸልታ ተጎድተዋል።
MSF በኣዲፍተው በተባለች መንደር ጊዜያዊ ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ከፍቷል።
የዚህ ክሊኒክ የሕክምና ባልደረቦች ትኩረትም የሚሰጡት በልጆች ፣ ነፍሰጡር ሴቶች እና የድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ !
ዶክተር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።
ዶክተር አብርሃም ላለፉት 6 ወራት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩትን ዶ/ር ሙሉ ነጋን በመተካት ነው በዋና ስራ አስፈጻሚነት የተሾሙት።
ዶ/ር ሙሉ ለምን ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ የተገለፀ ነገር የለም።
ዶ/ር አብርሃም የኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም ናቸው።
የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር "መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎት እመኛለሁኝ" ሲሉ ለዶ/ር አብርሃም መልካም ምኞታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።
ዶክተር ሙሉ ነጋ ባሳለፍነው ወርሃ ህዳር መባቻ ነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙት፡፡
ሹመቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ባጸደቀው ደንብ መሠረት የተሰጠ ነበር።
ሆኖም እስካሁን ድረስ የዶክተር አብርሃም ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለመሰጠቱ የተገለፀ ነገር የለም፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 23 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 5,733 የላብራቶሪ ምርመራ 785 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 729 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 260,139 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,795 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 203,408 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 777 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,215,934 ደርሷል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የደህንነትና_ፀጥታ_የጋራ_ግብረ_ኃይል_መግለጫ.pdf
422.9 KB
የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል መግለጫ :
- 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማደናቀፍ በህቡዕ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖችን ሴራ ማክሸፉን ገልጿል።
- በህቡዕ ተደራጅቷል በተባለው የአመጽና የግጭት ቡድኖች ላይ በተደረገ ክትትል ፦
• አደረጃጀታቸው፣
• አመራሮቹ፣
• ለጥፋት ተልዕኮው የተዘጋጁ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች፣
• የተለያዩ ቁሶች፣
• የገንዘብ ድጋፍና ዝውውር የተደረገባቸው ማስረጃዎች፤
• ተልዕኳቸውን የተመለከቱ የተለያዩ መረጃዎችና ማስረጃዎች ተጠናቅረው እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብሏል።
- በህቡዕ የተደራጁት ቡድኖቹ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የተደራጁ ናቸው።
- ቡድኖቹ ሀገራዊ ምርጫውን ለማደናቀፍ ያወጡትን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከአንድ አንድ የመንግሥት የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አባላት እና አመራሮች ጋር ምስጢራዊ የሆነ ግንኙነት በመፍጠር ኢላማ የተደረጉ ቁልፍ አመራሮችን ለይቶ በመግደል ሀገራዊ ትርምስ ለመፍጠር የሚያስችል ሴራ በመጠንሰስ በድብቅ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል ብሏል።
** ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል ፤ ያንብቡ !

ለትግራይ ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ዱቄት ተልኳል ?
በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መቐለ "ማይወይኒ" መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ከቀናት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የስንዴ ዱቄትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበት ቀን የታተመበት አጠራጣሪ ዘይት 'ቀይ መስቀል' አቅርቧል በሚል እንደማይጠቀሙ ገልፀው ነበር።
የቀይ መስቀል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን አሊ ፥ በመቐለም ሆነ በሌላ የትኛውም አካባቢ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት ምግብ እንደላቀርቡ እና እንደማያቀርቡ ገልፀዋል።
የጥርጣሬው መነሻ የሀገሪቱ ስንዴ አምራች ኩባንያዎች የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበትን ጊዜ ማሸጊያው ላይ የሚያትም ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ቀይ መስቀል ያቀረበው ስንዴ እና ዘይት የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት አይደለም ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን #ለቪኦኤ ፦
"የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን በአ/አ እና መቐለ ባለው ተረጋግጧል። እነዚህ ምልክቶች በወረቀት ተለጥፈው ነው የሚሄዱት እነዚህ ምልክቶች የሚያሳስቱ መስሏቸው ስለተጠራጠሩ አንወስድም ፤ ይሄ ተለጥፎ ነው የመጣው፤ ቀኑም ልክ አይደልም ብለዋል።
የእኛ ሀገር ዱቄት ይሄን ሁሉ መንገድ አጓጉዘን፤ ዱቄቶቹ ከቃጫ የሚሰሩ ናቸው ከማሌዢያ ወይም ከፊሊፒንስ የሚመጡ አይደለም ፤ እነዚህን ሲያዩ አንዳንድ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እነዚህን ነገሮች ተጠራጥረዋል።
መጠራጠራቸውን ትክክል ነው ፤ እነዚህ ነገሮች ይታዩ ፤ ይፈተሹ ተባለ ፤ ናሙናው ተወስዶ ታዩ ዱቄቱ በሙሉ ንፁህ ነው ፤ ለምግብነት መዋል ይችላል የሚል የፅሁፍ ማረገገጫ ነው ያገኘነው።
ዘይቶቹ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚያገለግሉ ዘይቶች ናቸው። ነገር ግን ምርመራ ሲደረግ የአዮዲን መጠናቸውን አነስተኛ ሆነው ነው የተገኘው"
ያንብቡ : telegra.ph/ERCS-05-05
@tikvahethiopia

ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚነት የተነሱት ዶክተር ሙሉ ነጋ በድጋሚ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት በይፋ አሳውቋል።
ሹመቱ ከሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ።
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)" እና "ሸኔ" በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ም/ቤቱ በአንድ ደምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጹድቋል፡፡
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)" እና "ሸኔ" በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ም/ቤቱ በአንድ ደምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጹድቋል፡፡
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የG7 ስብሰባ ዛሬ ተጀመረ። የG7 ስብሰባ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ቀውስን ጨምሮ በሌሎችም ጉዳዮች ይመክራል። የG7 ሀገራት ማለትም ፦ 🇺🇸አሜሪካ 🇯🇵 ጃፓን 🇬🇧ዩኬ 🇮🇹ጣልያን 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇨🇦ካናዳ 🇩🇪ጀርመን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሁለት ቀናት ስብሰባቸዉን ዛሬ ሎንዶን ዉስጥ ነው የጀመሩት። ሚንስትሮቹ ከሩሲያ ፣ ከቻይና እና ከኢራን ጋር የገጠሙትን ውዝግብ በኢትዮጵያ የትግራይ ቀውስ ፣…
G7_Foreign_and_Development_Ministers’_Meeting_Communiqué,_London.PDF
142 KB
የG7 ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ?
- አሁንም በትግራይ ያለው ሁኔታ ፣ የቀጠለው ግጭት እና የሰብዓዊ መብትና የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ በእጅጉ ያሳስበናል ብለዋል።
- የሲቪሎች/የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ፣ የሴቶች አስገድዶ መደፈር ፣ የወሲባዊ ብዝበዛ ሌሎችም ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን አውግዘዋል።
- የሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን መውደም እና መዘረፍ አውግዘዋል።
- በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እና የኤርትራ ስደተኞችን በግዳጅ ማፈናቀልን አውግዘዋል።
- በኢሰመኮ እና በUN የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር መካከል የተፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የተደረገውን ስምምነት በደስታ ተቀብለዋል።
- ሁሉም ወገኖች በፍጥነት ግጭት እንዲያቆሙ፣ የዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡ፣ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ህጎችንና የሚዲያ ነፃነት እና ተደራሽነትን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
- የሰብዓዊ ጥሰት እና ፆታዊ ጥቃቶችን የፈፀሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
- የውጭ ሀይሎች በትግራይ መኖራቸውን እጅግ የሚረብሽና መረጋጋት የሚያሳጣ መሆኑን ገልፀዋል።
- የኤርትራ ኃይሎችን ከትግራይ ለማስወጣት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የሰጡትን መግለጫ እንደሚቀበሉ ገልፀው፤ ነገር ግን ማስወጣቱ ገና አለመጀመሩ እንዳሰጋቸው ገልፀዋል። የኤርትራ ወታደሮችን የማስወጣት ሂደቱ መፋጠን አለበት ብለዋል።
- በትግራይ ክልል ሁሉን አቀፍ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።
- ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት/የግዛት አንድነት ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
- በመጨረሻም፦ በኢትዮጵያ ተአማኒ ምርጫና ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር ለማስቻል ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።
* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ…
'ሸኔ' ማንነው ?
በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም።
ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው ?
በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦
"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው።
እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም ፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን።
ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ 'ህወሓት' ተመዝግቦ ፣ ህጋዊ እውቅና ፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም ፤ ስለዚህ ስያሜው እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል ፤ አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት 'ኦነግ ሸኔ' / 'ሸኔ' ከሚባለው 'ሸኔ' የሚለውን መርጠናል።
እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል።
አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው ፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም።
ይሄ ተመዝግቦ ፣ ሰርተፊኬት ተሰጥቶት ፣ ህጋዊ ሰውነት ኖሮት በዚህ ስም ነው የሚጠራው ይባል የነበረ እንደ ህወሓት የለውም።
ያንብቡ : telegra.ph/Dr-Gedion-Timothewos-05-06

#Update የኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነስርዓት ነገ ይፈፀማል። በነገዉ ዕለት የቀብር ስነስራዓቱን አስመልክቶና ሙሉ ዝግጅቱ በድሮዉ ጊዮን ሆቴል አደባባይ ከተከናወነ በኃላ በካቴድራል ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው የሚፈመፅ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፥ የባህር ዳር ፖሊስ መምሪያ ያሰራጨው "የሀዘን ጥሪ" መልዕክት ያስረዳል። የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ትላንት…
#Update
የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ባህርዳር ገባ።
በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር አለም አቀፍ ኤርፖርት አየገባ ይገኛል።
በስፍራው ፦
- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር
- የጠ /ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
- ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች
- አዲሱ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ
- ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች መገኘታቸውን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኦሮሚያ_ክልል_ውስጥ_በሚገኙ_21_ፖሊስ_ጣቢያዎች_ላይ_የተደረገ_የክትትል_ሪፖርት_.pdf
364.4 KB
#Oromiya
"ሕግን የማስከበር እርምጃ ሕግን የተከተለ መሆን አለበት" - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንደሚያሳስበው ገለጸ።
ኮሚሽኑ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ያለውን የእስረኞችን አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለይም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቁጥጥር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ሌሎችም “በወቅታዊ ሁኔታ” (“haala yeroo”) የተያዙ የሚባሉ ብዛት ያላቸው እስረኞች ከሚገኙባቸውና ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሚቀርቡባቸው መካከል በ21 የተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉ ከእስረኞች እና የፖሊስ ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን፤ እንዲሁም የክትትሉን ግኝቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የክልሉ የሕግ አስከባሪ እና የአስተዳደር አካላት በማሳወቅ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እንደጠየቀ አሳውቋል።
ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው ብሏል።
* የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

ከኢሰመኮ ሪፖርት የተወሰዱ፦
- ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በ21 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ተደርጓል
- ክትትል ከተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች መካከል ከሚገኙ እስረኞች መካካል የተወሰኑት በፖሊሶች በሚያዙበት ወቅት (በተለይ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል) እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ድብደባ የተፈፀመባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
- እስረኞ በተፈፀመባቸው ድብደባ ጭንቅላታቸው፣ ፊታቸው ፣ አፍንጫቸው፣ ሆዳቸው ፣ እግራቸው፣ ጥርሳቸው ...ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ገና ያልዳነ ቁስል፣ ስብራት ወይም ደም በሰውነታቸው ላይ የሚታይና ለጊዜያዊ እና ቋሚ የአካል ጉዳት የተዳረጉ እስረኞች አሉ።
- በተወሰኑ ቦታዎች 'ኦነግ ሸኔ' አባል ወይም ደጋፊ በሚል የሚፈለጉ "ልጆቻችሁን አቅርቡ" በማለት አባት ወይም እናት ማሰር፣ "ባልሽን አቅርቢ" በማለት ሚስትን ማሰር ፣ ሰዎችን ያለአግባብ በማሰር "ኦነግ በሸኔ" አባል ናችሁ ብለን እንሰካሰል በማለት በማስፈራራት ገንዘብ የመጠየቅ ሁኔታዎች መኖራቸውን እስረኞች ተናግረዋል።
- በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ሴት እስረኞች አሉ፤ከነዚህ ውስጥ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ወይም ሌላ በወንጀል የሚፈለግ የተሰወረ የቤተሰብ አካል አቅርቡ ተብለው የታሰሩ ይገኙበታል፤ ከነዚህ ሴቶች የተወሰኑት ከ5 ወር እስከ 10 ዓመት የሚሆናቸውን ህፃናት ልጀች ይዘው የታሰሩ ናቸው።
- በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በወንጀል ጉዳይ ተሳታፊናቸው በሚ የታሰሩ እድሜያቸው ከ9 እስከ 18 ዓመት የሚሆናቸው ህፃናት አካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅለው በእስር ላይ ይገኛሉ።
- አብዛኛዎቹ ፖሊስ ጣቢያዎች ያሉት የማረፍያ ክፍሎች በእስረኞች የተጣበቡ ናቸው። የተወሰኑ እስር ቤቶች የከፋ መጨናነቅ በመኖሩ ቀን ውጭ በረንዳ ላይ ውለው ማታ ደግሞ በተራ ይተኛሉ።