TIKVAH-ETHIOPIA
የጭልጋና አካባቢው የፀጥታ ችግር : በአይከል እና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ነዋሪዎቹ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል። አይከል ከተማ ውስጥ ከሁለት ሳምንት በላይ መብራት የለም፣ ኔትዎርክ የለም ፣ ውሃ የለም። ችግር የተፈጠረው በአይከል ብቻ ሳይሆን በዙሪያ ባሉ አካባቢዎችም ጭምር ነው። አንድ ቤተሰቦቹ እዛው የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ በሳርጥያ፣ ወርቀየ ፣ እያሁ ማይርያ ቀበሌዎች…
#CommandPost
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ እና አካባቢውን ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።
በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ እና አካባቢው የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋት ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች አስታውቀዋል።
የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ዛሬ ማምሻውን በጎንደር ከተማ መግለጫ ሰጥተዋል።
በጭልጋና አካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ፦
- ከፌደራል መከላከያ ሰራዊት
- ከፌደራል ፖሊስ
- ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት
- ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ከዞኑ ፖሊስና የካቢኔ አባላት የተውጣጣ ነው ተብሏል።
ከክልከላዎች መካከል ፦
- ከዛሬ ጀምሮ ከጎንደር መተማ በሚወስደው ዋና መንገድ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ግራና ቀኝ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ ተጥሏል፡፡
- ከህጋዊ አካላት ውጪ በአካባቢው ከወረዳ ወረዳ እና ከቀበሌ ቀበሌ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከ ነው።
ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመለስ በፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ከመውሰድ ጀምሮ ተስተጓጉሎ የቆየውን የጎንደር መተማ መንገድ ለማስከፈት ዛሬ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተብሏል።
በጭልጋና አካባቢው ከሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ተፈጥሮ በነበረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ተገድቧል።
በፈጠረው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአካባቢው የደረሰውን ሰብአዊ ጉዳት የሚያጣራ ቡድን ከፌዴራልና ከክልል ተልኮ በዛሬው እለት ወደ አካባቢው መድረሱን ተገልጿል። #ENA
@tikvahethiopiaBOT