#ጥንቃቄ_ይደረግ
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ የትንሳኤ በዓል ሲከበር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
በተለይ በምግብ ማብሰል ወቅት የኤሌክትሪክ ሃይል ጫና ሊፈጥር የሚችል የሶኬት አጠቃቀም እና የጋዝ ስሊንደሮች አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል።
በተጨማሪ ሕብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት የከሰል፣ የሻማና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለበት መክረዋል።
የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን በትንሳኤ በዓል 1 ሺህ 112 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 27 ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ 19 አምቡላንሶችና ሌሎች አደጋን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት 9 ወራት በአዲስ አበባ ከደረሱ 249 የእሳት አደጋዎች መካከል 42ቱ በኤሌትሪክ ንክኪ የተከሰተ ሲሆን የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ያስታወሱት አቶ ጉልላት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ የ50 ሰዎች ሕይወት ማትረፍ መቻሉን አመልክተዋል።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 249 የእሳት አደጋ እንዲሁም 111 ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መካከል 313 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሆን 47ቱ ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተከሰቱ ናቸው ብለዋል።
በአጠቃላይ በደረሱ አደጋዎች ከ299.5 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት የወደመ ሲሆን በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተደረገ ርብርብ ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።
አደጋዎች ሲያጋጥሙ በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ ይችላል። (ENA)
@tikvagethiopia

#ምርጫ2013
• ''...የክፍያ መዘግየት ትልቅ ሀገራዊ የሆነ ሂደትን ማዛባት የለበትም" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ
• "...በ47 ቀን የሥራ ውላችን መሰረት በ2 ዙር ማግኘት የሚገባንን ክፍያ ሳናገኝ 3ኛ ዙር ደርሷል" - የደሴ ምርጫ አስፈፃሚዎች
በደሴ ከተማ የሚወዳደሩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ሰብሳቢ መንግስቱ አመንዴ ከዚህ ቀደም የመራጮች ምዝገባ በተለያዩ ምክንያቶች ከ15 ቀናት በላይ ዘግይቶ ከጀመረ በኋላ አሁን ደግሞ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥራ በማቋረጣቸው ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ከተቋረጠ 3 ቀናት እንዳለፈው ለቪኦኤ ተናግረዋል።
የምርጫው ቀን የሚኖረው ውስንነት ችግሩ እንዲፈታ በጹሑፍም በቃልም አመልክተናል ሲሉ ገልጸዋል።
ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለተፎካካሪዎች ደግሞ በግልባጭ ምርጫ አስፈጻሚዎች በጻፉት ደብዳቤ 400 የሚደርሱ የደሴ ከተማ የሚገኙ ሥራ አስፈጻሚዎች በ47 ቀን የሥራ ውላቸው መሰረት በሁለት ዙር ማግኘት የሚገባቸውን ክፍያ ሳያገኙ ሶስተኛ ዙር መድረሱን ገልጸዋል።
ምርጫው እንዳይስተጓጎል ያለምንም ክፍያ ሥራቸውን ሲሰሩ መቆየታቸውን ዘርዝረው ቅሬታቸውን በአከባቢያቸው ላለ የሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ጠቅሰዋል።
ክፍያ ካልተፈጸማቸው በሥራ ገበታቸው ለመገኘት አእንደሚቸገሩ አሳስበዋል በማመልከቻቸው።
የምርጫ ቦርድ የኮሚውኒኬሽን ጉዶዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት ሥራቸውን ያቆሙ ስለመኖራቸው የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ገልፀዋል።
ክፍያ ባለመፈጸሙ ምክንያት አንዳንድ ክፍተቶች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊዋ በተባለው ልክ ግን ሥራቸውን ትተው ሄደው ዘግተዋል የሚል ሪፖርት እንዳልደረሳቸውና እንደዚያም ያደርጋሉ ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/VOA-04-29
@tikvahethiopiaBOT

ዛሬም ውጊያ ላይ የሚገኙት የጤና ባለሞያዎች !
የሀገራችን የጤና ባለሞያዎች ዛሬም ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል በአይን ከማይታየው እና ከማይዳሰሰው ኮቪድ-19 ጋር እየተዋጉ ነው።
እኛ ብንዘናጋ ፣ ብንሰላች እነሱ ግን ከወረርሽኙ መነሻ ጊዜ አንስቶ ሳይደክሙ ከፊት መስመር ተሰልፈው ለእኛ ጤና እየተዋጉ እና እየተዋደቁ ናቸው።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለአሀዱ ሬድዮ ሰጥቶት በተመለከትነው መረጃ መሰረት በግል እና በመንግሥት ተቋማት ለማኅበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ፦
- 1 ሸህ 302 የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።
- 30 የጤና ባለሞያዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።
የጤና ባለሙያዎች ምቹ ባልሆነ ቦታ እና በቂ የህክምና ቁሣቁስ ባልተሟላበት መስራታቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ነው የተባለው።
ለጤና ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከከተማ አስተዳደር እና ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁናዊ ሁኔታን በተመለከት የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ቢሮው ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ ያሳወቀ ሲሆን ወረርሽኙን ለመከላከል የወጣው መመሪያ በተቋማት ፣ ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እንዲሁም በትምህርት ቤቶች በሚፈለገው ልክ እየተተገበረ አይደለም ብሏል።
ከላይ የተያያዙት ፎቶዎች ባለቤታቸው ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው ሲሆን ከፋይል ውስጥ የተወሰዱ ናቸው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#AtoLidetuAyalew
ዛሬ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ከሀገር እንዳይወጡ በፖሊስ የተላለፈውንና በፍርድ ቤት ጸንቶ የነበረውን እግድ ሽሯል።
ፍርድ ቤቱ እግዱን የሻረው ከፌደራል ፖሊስ እና ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች የቀረበሉትን ምላሾች ከመረመረ በኋላ ነው።
ፍ/ቤቱ እግዱን በዋነኛነት ውድቅ ያደረገው ሁለት ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው ፦
- የመጀመሪያው ፖሊስ በደብዳቤው የጠቀሳቸው አቶ ልደቱ ተከስውባቸው በነበሩባቸው ሁለት የወንጀል ጉዳዮች ነጻ መባላቸው ነው።
- አቶ ልደቱ በአቤቱታቸው ላይ የጠቀሱትን የልብ ህመም በሁለተኛ ምክንያትነት ያነሳው ፍርድ ቤቱ፤ አቤት ባዩ ወደ አሜሪካ ሀገር ሄደው ባይታከሙ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ዳስሷል። ይህ ሁኔታ አቶ ልደቱ በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን በህይወት የመኖር መብት የሚጥስ እንደሆነ ጠቅሷል።
ፖሊስ በአቶ ልደቱ ላይ ያወጣው የጉዞ እግድም የግለሰቡን እንደ ልብ የመንቀሳቀስ ህገ መንግስታዊ መብት የሚገድብ መሆኑንም ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ ምክንያትነት አንስቷል።
በእነዚህ ዋነኛ ምክንያቶች የጉዞ እግዱ እንዲሻር የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር/www.Ethiopiainsider.com" ድረገፅ አስነብቧል።

ምርጫ ጣቢያዎች ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ ይዘጋሉ !
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው አጭር መግለጫው ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነ አስታውሷል። በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተደነገገው መሰረት የመራጮች ምዝገባ በብሔራዊ በአላት ቀናት እንደማይከናወን ገልጿል።
በመሆኑም ፦
- ነገ ሚያዝያ 22 ቀን 2013 ዓ.ም የስቅለት በአል በመሆኑ፣
- ሚያዝያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሰራተኞች ቀን በመሆኑ
- ሚያዝያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የፋሲካ በአል በመሆኑ ምርጫ ጣቢያዎች ዝግ ሆነው እነደሚውሉ ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።
ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ይከፈታሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የገዛ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተገደሉት መምህር ቀጀላ ታሲሳ :
(በጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
• "...ቁጥራቸው በርከት ያሉ ባሉት የመንግስት የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ ኃይሎች የመኖሪያ ቤት አጥሩን ከበው ግድያ ፈፅመዋል።" - ወላጅ እናት ወ/ሮ አጊቱ ቡልቻ
• "...በጫካ የሚንቀሳቀስ ሸማቂ ቡድን 'አባቶርቤ' በሚል የመለመላቸው ግድያውን ሳይፈጽሙት አይቀርም" - የቄለም ወለጋ ዞን የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ በራሱ ቤት የተገደለው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ቀጄላ ታሲሳ ጉድያ እያነጋገረ ነው።
መምህር ቀጄላ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉበት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ደምቢዶሎ ያቀኑት ባለፈው ቅዳሜ መሆኑንና እሁድ ማታ በገዛ ቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡
የመመህሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ አጊቱ ቡልቻ እንዳሉት ልጃቸው የ9 ወር እርጉዝ የሆነችውን ባለቤቱን ለመጠየቅና በዓልን አብሯት ለማሳለፍ ከሚማርበት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ እለት መምጣቱን ይናገራሉ፡፡
እሁድ ማምሻውን 1 ሰዓት ከ 30 ገደማ “ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው” ባሉት የመንግስት የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ የመኖሪያ ቤት አጥሩን ከበው ግድያ መፈጸማቸውንም ተናግረዋል፡፡
የቄለም ወለጋ ዞን የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሰማ ዋሪዮ ጉዳዩ እንደሚባለው አይደለም ይላሉ፡፡ በጫካ የሚንቀሳቀስ ሸማቂ ቡድን “አባ ቶርቤ” በሚል የመለመላቸው ግድያውን ሳይፈጽሙት እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡
More https://telegra.ph/DW-04-29

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !
በአዲስ አበባ ከባእድ ነገሮች ጋር ተቀላቅሎ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከ3 ሺህ 300 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ፣ 480 ኩንታል በርበሬ፣ 1 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ለቂቤ መከለሻ የሚውል የአትክልት ቅቤና የፓልም ዘይት እንዲሁም 6 መቶ ኪሎ ግራም ማር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
በአራት ክፍለ ከተሞች (በአዲስ ከተማ ፣ ቂርቆስ ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ እና ኮልፌ ቀራንዮ) ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሲያካሂድ በነበረው ክትትል በዚህ ህገወጥ ድርጊት ላይ የተሳተፉ በ24 ድርጅቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ተሳታፊ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገልጿል።
በቁጥጥሩ ወቅት ቅቤን ለመከለስ አገልግሎት የሚውሉ የአትክልት ቅቤ፤ ፓልም ዘይት እንዲሁም በርበሬ ለመከለስ የሚሆን ከደረጃ በታች የሆነ ለሰው ምግብነት የማይውል የበርበሬ ተረፈ ምርት፤ የሻገተ በርበሬ ተገኝቷል።
በተጨማሪም ቤቶቹ ለምግብ ማምረት ስራ ፍቃድ የሌላቸው እና ከፍተኛ የሆነ የንፅህና ጉድለት ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል።
ህብረተሰቡ በበዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ያለው ባለስልጣኑ አጠራጣሪ ነገር ሲገጥም በነፃ የስልክ መስመር 8482 ላይ በመደወል ጥቆማ ማድረስ ይቻላል ተብሏል።
ምንጭ ፦ ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

TIKVAH-ETHIOPIA
የጭልጋና አካባቢው የፀጥታ ችግር : በአይከል እና አካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ነዋሪዎቹ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል። አይከል ከተማ ውስጥ ከሁለት ሳምንት በላይ መብራት የለም፣ ኔትዎርክ የለም ፣ ውሃ የለም። ችግር የተፈጠረው በአይከል ብቻ ሳይሆን በዙሪያ ባሉ አካባቢዎችም ጭምር ነው። አንድ ቤተሰቦቹ እዛው የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ በሳርጥያ፣ ወርቀየ ፣ እያሁ ማይርያ ቀበሌዎች…
#CommandPost
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ እና አካባቢውን ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ።
በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ እና አካባቢው የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋት ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች አስታውቀዋል።
የኮማንድ ፖስቱ አመራሮች ዛሬ ማምሻውን በጎንደር ከተማ መግለጫ ሰጥተዋል።
በጭልጋና አካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ፦
- ከፌደራል መከላከያ ሰራዊት
- ከፌደራል ፖሊስ
- ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት
- ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ከዞኑ ፖሊስና የካቢኔ አባላት የተውጣጣ ነው ተብሏል።
ከክልከላዎች መካከል ፦
- ከዛሬ ጀምሮ ከጎንደር መተማ በሚወስደው ዋና መንገድ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ግራና ቀኝ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ ተጥሏል፡፡
- ከህጋዊ አካላት ውጪ በአካባቢው ከወረዳ ወረዳ እና ከቀበሌ ቀበሌ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከ ነው።
ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመለስ በፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ እርምጃ ከመውሰድ ጀምሮ ተስተጓጉሎ የቆየውን የጎንደር መተማ መንገድ ለማስከፈት ዛሬ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተብሏል።
በጭልጋና አካባቢው ከሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ተፈጥሮ በነበረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ተገድቧል።
በፈጠረው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአካባቢው የደረሰውን ሰብአዊ ጉዳት የሚያጣራ ቡድን ከፌዴራልና ከክልል ተልኮ በዛሬው እለት ወደ አካባቢው መድረሱን ተገልጿል። #ENA

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ
ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚሞቱባት ዜጎቿ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ፣ የቫይረሱ ተጋላጮችም በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6,198 የላብራቶሪ ምርመራ 1,130 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ትላንት 1,492 ሰዎች አገግመዋል። አሁን ላይ 945 ሰዎች በፀና ታመዋል።
በአጠቃላይ 256,418 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ የታየዙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3,658 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 197,916 ሰዎች አገግመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia

"...ውይይቱን በተመለከተ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጩት ዘገባ የውይይቱን ይዘት በትክክል ያንፀባረቀ አይደለም" - የእንግሊዝ ኤምባሲ
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ በአምባሳደሩ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ውይይት በተመለከተ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጩት ዘገባ የውይይቱን ይዘት በትክክል ያንፀባረቀ አይደለም ብሏል።
በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አላስቴር ማክፌል እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ተገናኝተው ውይይት አድርገው ነበር።
የሁለቱን አመራሮች ውይይት በተመለከተ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቢሲ፣ ፋና ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች በሰሩት ዘገባ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ከአምባሳደሩ ጋር ተወያዩ ብለዋል።
በተጨማሪ በቅርቡ በትግራይ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ በሀገሪቱ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ሂደት እና ለቀጠናው ሰላም እና ደህንነት አስተዋፅኦ ያበረከተ ነው ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል ሲሉ ዘግበዋል።
ይህንን ተከትሎ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ በትዊተር ገፁ ላይ የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ የሁለቱን ሀገራት ውይይት አይወክልም ብሏል።
ኤምባሲው፥ አምባሳደሩና ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ባደረጉት ውይይት ዩናይትድ ኪንግደም በትግራይ ያለው ግጭት እንደሚያሳስባት ለኢታማዦር ሹሙ ገልፀዋል ብሏል።
በተጨማሪ ለችግሮች የፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ እና ግጭት እንዲቆም፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ኤምባሲው መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዛሬ ምሽት የመከላከያ ሰራዊት ጥዋት ባወጣው ዜና ላይ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ይቅርታ ጠይቋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-04-29

የህክምና (Medicine) ብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
ከመጋቢት 20-24/2013 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የህክምና (Medicine) ተመዛኞች ከሚያዚያ 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et/hple/ ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት እንደምትችሉ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115324185 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።
የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ሆኗል።
በመሆኑም ተማሪዎች ከታች በተገለጸዉ የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ ይችላሉ።
ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።
• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- https://result.neaea.gov.et/Home/Placement
• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
#MoSHE

ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ስንዴ እየቀረበ ነው ?
የትግራዩ ጦርነት በርካቶችን ህይወት አሳጥቷል፤ አካል አግድሏል፣ ወላጅ ከልጅ ፤ ልጅ ከወላጅ አለያይቷል።
በርካታ ሺዎችም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ አስቀርቷል።
ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በተለያዩ ከተሞች ተጠልለው ይገኛሉ።
በርካታ ዜጎች ተፈናቅለው ከተጠለሉበት የትግራይ ከተሞች አንዷ ደግሞ የትግራይ መዲና መቐለ ናት።
በመቐለ ሺዎች ተፈናቃይ ወገኖች ይገኛሉ።
በከተማው ካለውና ተፈናቃዮች ከሚገኙባቸው መጠለያዎች አንዱ ማይወይኒ የሚባል ሲሆን በርካቶች ይገኙበታል።
በዚህ መጠለያ ካም ያሉ ተፈናቃዮች ከሰሞኑን በቀይ መስቀል የቀረበን እርዳታ አንቀበልም ማላታቸውን ተሰምቷል።
ምክንያት ? ተፈናቃዮች እየቀረበ ያለው እርዳታ ዘይት እና ስንዴ የመጠቀሚያው ጊዜ አልፎበታን የሚል ነው።
ለተፈናቃዮቹ ቅሬታ እስካሁን በይፋ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በኩል የተሰጠ ምላሽ እና ማብራሪያ ባይኖርም ፤ ተፈናቃዮቹ ግን የቀረበውን እርዳታ አንቀበልም ብለዋል።
ምናልባት በዚህ ጉዳይ ምላሽ ከተገኘ ተከታትለን መረጃውን እንለዋወጣለን።