TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የቻድ ፕሬዜዳንት ተገደሉ። ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡ ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው…
#update

“...ቻድን ማንም እንዲያስፈራራት አልፈቅድም” - የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት

የቀድሞ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ቀብር ስነስርዓት ዛሬ በትውልድ አካባቢያቸው አቅራቢያ ተፈፀመ።

የቀብር ስነስርዓቱ በትውልድ አካባቢያቸው ከመፈፀሙ ቀደም ብሎ በኒጃሚን በነበረ ስነስርዓት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቺሲዲኬ እና ሌሎችም ተገኘተው ነበር ፤ ምንም እንኳን አማፂያን የሀገራት መሪዎች በደህንነት ምክንያት በስነ ስርዓቱ ላይ እንዳይገኙ ቢያስጠነቅቁም።

ፕሬዜዳንት ማክሮን ፥ በስነስዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ “ቻድን ማንም እንዲያስፈራራት አልፈቅድም” ሲሉ ተደምጠዋል።

ለቻድ መረጋጋት እና አንድነት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀው፥ ነገር ግን ወታደራዊ ተተኪዎቹ ወደሲቪል አስተዳደር በሰላም እንዲመለሱ አሳስበዋል።

የቀድሞ የቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ባለፈው ሰኞ ዕለት በሃገሪቱ ሰሚናዊ ክፍለ ግዛት ከአማጽያኑ ጋር የሚዋጉትን ወታደሮች በውጊያው ግንባር ተገኝተው በመጎብኘት ላይ ሳሉ ቆስለው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።


@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NEBE

ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ከሃገሪቱ የምርጫ ህግና የስነ ምግባር አዋጅ በተጻረረ መልኩ "ለአመጽ የሚጋብዝና በግለሰቦች ወይም ቡድኖች ላይ ስጋትን የሚያጭር ቋንቋ" ን የሚጠቀሙ ፓርቲዎች እና እጩዎችን አሳስቧል።

ፓርቲዎች እና እጩዎች ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮች እና ድርጊቶች እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡ ህጉ የማይከበር ከሆነ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳስቧል።

* የምርጫ ቦርድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የመራጮች ምዝገባ ተራዘመ።

የመራጮች ምዝገባ መራዘምን አስመልክቶ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጥቷል።

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ቀን ማጠናቀቂያ ዛሬ መሆኑን ተከትሎ የስራ ሂደቱን ያጋጠሙትን ችግሮች መመርመሩን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ፦

1. የመራጮች ምዝገባ በግማሽ የአገሪቱ ክፍሎች ዘግይቶ በመጀመሩ

2. በጊዜው በተጀመረባቸው ቦታዎች የመራጮች ምዝገባ መረጃዎች እጦት እና በሌሎች ምክንያቶች ለመመዝገብ ጊዜ በመውሰዱ

3. የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቁ በቀሩት ጥቂት ቀናት በአንድ ምርጫ ጣቢያ 1500 ሰው ብቻ መመዝገብ በመቻሉ የተነሳ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በሚገኙ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ምዝገባ በመቋረጡ እና ተጨማሪ ምርጫ ጣቢያዎች በመክፈት ሂደት ክፍተት በመፈጠሩ ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ወስኗል።

በዚህም መሰረት ፦

1. የመራጮች ምዝገባ እጅግ ዘግይቶ በጀመረባቸው በአፋር እና በሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ ለሶስት ሳምንት ተራዝሟል ። ይህም ማለት የመራጮች ምዝገባ ግንቦት 06 ቀን 2013 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

2. የመራጮች ምዝገባ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች በተስተጓጎለባቸው ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ለሁለት ሳምንት ተራዝሟል ይህም ማለት የመራጮች ምዝገባ ሚያዝያ 29 ቀን 2013 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

3. የመራጮች ምዝገባ እስካሁን ድረስ ባልተጀመረባቸው እና የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ እና ቄለም ወለጋ የመራጮች ምዝገባን የማስጀመር እንቅስቃሴዎችን እየተደረገ ይገኛል።

4. 1500 ሰዎቸን መዝግበው በጨረሱ ምርጫ ጣቢያዎች ተጨማሪ ንኡስ ምርጫ ጣቢያዎችን መክፈት የሚቀጥል ይሆናል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ምን ያህል ዜጎች ለምርጫ ተመዘገቡ ?

እንደ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እስከ ትላትንና ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ 18 ሚልዮን 427 ሺህ 239 ዜጎች (18,427,239) የተመዘገቡ ሲሆን በ41,659 ምርጫ ጣቢያዎች ነው መራጮች እየተመዘገቡ የሚገኙት።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ETHIOPIA😷

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ወደ 250 ሺህ ተጠግቷል።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 6,581 የላብራቶሪ ምርመራ 1, 303 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 249,292 ደርሰዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,511 ደርሷል።

ትላንት 2,973 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ያገገሙ 188,080 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 968 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia
"...የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ የስራ ገበያን መሰረት ያደረገ ይሆናል" - MoSHE

በመጀመሪያ ዲግሪ በሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች ከአቅርቦት እና ገበያ አንፃር ያለባቸውን ችግር የሚዳስስ የስራ ገበያ ሁኔታ ጥናት እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት በ2014 የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ገበያን መሰረት ያደረገ የተማሪዎች ቅበላ ይደረጋል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት የምስረታ ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ምክር ቤቱ ከ200 በላይ የሙያ ማህበራትን ያካተተ ሲሆን በትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ አተኩሮ ይሰራል ነው የተባለው።

የም/ቤቱ መመስረት ለትምህርት ጥራትና አግባብነት ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው ከመሆኑ ባለፈ ከስርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ ተማሪዎችን ለማብቃት በጋራ መስራት እንደሚያስችል ተገልጿል።

ምክር ቤቱ በገለልተኝነት የሚሰራ ቢሆንም የትምህርት ጥራት እና አግባብነትን ለማረጋገጥ ከMoSHE ተባብሮ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ም/ቤቱ የምሩቃን ምዘና፣የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያና የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ሲመዘን ሚናውን እንደሚወጣ ተገልጿል።

ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር በመጀመሪያ ዲግሪ በሚሰጡ 211 የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ከአቅርቦትና ገበያ ጋር ያላቸውን ችግር ለመዳሰስ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

በቅድመ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች የስራ ገበያ ሁኔታ ጥናት መሰረት በቀጣዩ የ2014 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅበላ የሚከናወን ይሆናል። ~ ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

[ በ Purpose የቀረበ ]

- ትላንት በመላው ዓለም 891,268 ሰዎች ለቫይረሱ ታጋላጭ መሆናቸው ሲረጋገጥ ፤ 14,247 ሰዎች ሞተዋል።

- ህንድ ትላንት ብቻ 345,147 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች፤ በ24 ሰዓት 2,621 ሰዎች ሞተዋል።

- በብራዚል በ24 ሰዓት 2,866 ሰዎች ሲሞቱ፥ 65,971 አዲስ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርጋለች።

- በ24 ሰዓት በርካታ ሰዎችን ከሞቱባቸው ሀገራት መካከል : አሜሪካ 790 ፣ ፖላንድ 539 ፣ አርጀንቲና 556፣ ኢራን 380፣ ፔሩ 408፣ ዩክሬን 434፣ ሩሲያ 398 ፣ ፈረንሳይ 332 ፣ ጣልያን 342 ፣ ቱርክ 343 ፣ ኮሎምቢያ 420 ፣ ሜክሲኮ 498 ይጠቀሳሉ።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች 146,277,103 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 3,100,405 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል 124,075,915 አገግመዋል።

- በአፍሪካ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 4,525,278 የደረሰ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ በማስመዝገብ ደቡብ አፍሪካ በ1,572,985 ቀዳሚ ናት፣ ሞሮኮ በ508,530 ፣ ቱኒዝያ በ296,343 ፣ ኢትዮጵያ በ249,292 ይከተላሉ።

@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

የWHO ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለምን የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦት ለራሳቸው ብቻ የሚሰበስቡ ሃገሮች አጥብቀው ነቅፈዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ፥ በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ባወጡት ጽሁፋቸው ክትባቱን ማግኘት ለሚቸግራቸው ሃገሮች ለማቅረብ በዓለም የጤና ድርጅት አሰባሳቢነት በተቋቋመው በኮቫክስ አማካይነት የሚደረገውን ጥረት “ክትባት ለራስ ሃገር ብቻ መሰብሰብ" ሲሉ በገለጹት አድራጎት ጥረቱ እየተዳከመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ጥቂት ከበርቴ ሃገሮች የሚመረቱ ክትባቶችን የበለጠ ዋጋ ለሚከፍላቸው ከሚሸጡ ኩባኒያዎች ላይ ተቀራምተው በመግዛት የሚያግበሰብሱበት ሌሎች ትርፍራፊው የሚቃርሙበት ሁኔታ እየታየ ነው ብለዋል።

አያያዘውም ወረርሽኙን ለመዋጋት መፍትሄው ቀላል ነው ፣ ያም ማካፈል ወይስ አለማካፈል ከሁለት አንዱን የመምረጥ ጉዳይ ነው ሲሉ አሳስበዋል። አስከትለውም በዚያ ደግሞ የሚፈተነው ሳይንስ ወይም የኢኮኖሚ እና የኢንዱስትሪ አቅም ሳይሆን የሚፈተነው ማንነታችን ነው" ማለታቸውን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ምርጫ2013 አጭር ቁጥራዊ መረጃ ፦

[ በ www.ethiopiaindider.com የቀረበ ]

- እስከሚያዝያ 14 ቀን 2013 ድረስ ባለው ጊዜ 18,427,239 መራጮች ተመዝግበዋል። 41,659 ምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን እየመዘገቡ ይገኛሉ።

- በአዲስ አበባ ከተማ ይመዘገባል ተብሎ የሚጠበቀው ሰው 1,405,650 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1,234,802 ያህሉ መመዝገቡን ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል። (ከሳምንት በፊት ምርጫ ቦርድ ባወጣው መረጃ በአ/አ ለመራጭነት የተመዘገቡ ሰዎች 200,903 እንደሆነ መግለፁ አይዘነጋም)

- በአማራ ክልል ከ5 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አቶ አገኘሁ ተባገር ተናግረዋል ፤ በአማራ እስካለፈው ሳምንት የተመዘገበው መራጭ ብዛት 1 ሚሊዮን እንኳን የማይሞላ ነበር ብለዋል።

- በኦሮሚያ ይመዘገባሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰዎች ብዛት 16 ሚሊዮን 500 ሺ ሲሆን እስካሁን የተመዘገቡት 12,347,537 መሆናቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል። ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ውጭ ባሉ 17 ዞኖች ውስጥ ለመራጭነት ይመዘገባሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ 85 በመቶ ያህሉ መመዝገባቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ፣ የደህንነት እና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT
#UnitedStates

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትላንት ጄፍሪ ፌልትማን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ተደርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል።

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ላይ አገልግለዋል።

አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

አዲሱ የኃላፊነት ስፍራ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተፈጠረ ነው።

- በትግራይ ክልል ያለውን ቀውስ
- በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል ያለውን አለመግባባት በቅርበት ለመከታተል የታለመ መሆኑ ታውቋል።

አንቶኒ ብሊንከን ትላንት በሰጡት መግለጫ ፥ " አሁን ላይ አሜሪካን የሚያሳስበው ነገር ቢኖር የትግራይን ግጭትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያለው ተለዋዋጭ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለው የመጣ የድንበር ውጥረት እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ውዝግብ ነው" ብለዋል።

ጄፍሪ ፌልትማን ፤ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸውም የባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን ተያያዥ የሆኑትን ፖለቲካዊ፣ የደኅንነትና የሰብአዊ ጉዳዮች ምፍትሔ እንዲያገኙ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት አስታውቀዋል።

Via Al ALIN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...የፀጥታ ኃይሎች የጸጥታ ችግር ያለበት ቦታው የሚደርሱት ህይወት ከጠፋና ረብሻ ከተነሳ በኋላ ነው" - ዶክተር ራሄል ባፌ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የጸጥታ ሀይሎችና የደህንነት ተቋማት የሰው ህይወት ከጠፋ በኋላ የሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ስራ ሊታረም ይገባል ሲል አሳሰበ፡፡

ም/ቤቱ በወቅታዊ የሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ላይ፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ተቋም ወቅቱን የጠበቀ የቅድመ ማስጠንቀቂያ የሁኔታ ትንተና ለሚመለከተው አካል የማድረስና ከችግሮች ቀድሞ የመገኘት ግዴታና ኃላፊናቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌ፥ ለአሐዱ 94.3 ሬድዮ እንደተናገሩት የመከላከያ ሰራዊት ፣ ፌደራል ፖሊስ እና ሚሊሻዎችም የጸጥታ ችግር ያለበት ቦታው ላይ ቢደርሱም ህይወት ከጠፋና ረብሻ ከተነሳ በኋላ ነው ብለዋል፡፡

የመረጃ መረብ ደህንነት ኃላፊነት ችግሮች ሳይፈጠሩ ቀድሞ የመለካለል ስራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጸጥታ አላካትም ሆነ የሚመለከታቸው የደህንነት ተቋማት ግዴታና ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አለመሆናቸው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የጸጥታ ኃይሎች እና የሚመለከታቸው ተቋማት የሰው ህይወት ከጠፋ በኋላ የሚያደርጉት እሳት የማጥፋት ስራ እና ችግሩን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ሊታረም እንደሚገባ ማሳሰቡን አሀዱ ሬድዮ 94.3 ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Attention😷

"ከወደ ህንድ ሃገር በየ5 ደቂቃው 1 ሰው በ ኮቪድ 19 ምክንያት ህይወቱ ያልፋል" - አልጀዚራ

ሆስታሎች ሞልተው እድለኛ የሆኑት በየጎዳናው ኦክስጅን ታቅፈው የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማሉ::

እድል ያልቀናው ደግሞ ቤቱ ሆኖ የሞቱን ቀን እና ሰዓት ይጠባበቃል::

አሁን ላይ በሃገሪቱ የቫይረሱን በከፍተኛ ፍጥነት መዛመት ተከትሎ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መስጠት አልቻሉም። ከእንደዚህ አይነቱ ክስተት ካልተማርን እና እርምጃ ካልወሰድን የህንድ እጣ ፈንታ ነገ እኛ ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለንም::

ዛሬም በእጃችን ያለው መድሃኒት "መጠንቀቅ" ብቻ ነው።

እባካችሁ ሃላፊነት በመውሰድ ቀን ሳለማድረግ የሚገባንን ጥንቃቄ እንፈፅም።

ቤታችን እስኪንኳኳና የምንወዳቸውን እስኪነጥቀን አንጠብቅ፤ ካለተጠነቀቅን የጊዜ ጉዳይ እንጂ የሁላችንም ቤት መንኳኳቱ አይቀሬ ነዉ።

የመጀመሪያውን ፍርሃታችንን እና ጥንቃቄያችንን ልንመልሰው ይገባል። ኮሮና ቫይረስን በምናብ የተሳለ ተረት አናድርገው ፣ ሲደርስብን ብቻ ለመንቃት አንሞክር።

በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ የፊት ጭንብል እና ሳኒታይዘር አይለየን።

ነገን ለማየት ዛሬን እንጠንቀቅ፤ ብልህ ሰው ከሌላው ይማራል::

(በዶክተር ኃይለልኡል መኮንን)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የማህበር ቤት ምዝገባ ተጠናቀቀ።

ባለፉት 25 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበር ቤት ምዝገባ 12 ሺህ 609 ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የማህበር ቤት ምዝገባ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ቢሮው በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ነዋሪዎች በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር በማደራጀት የራሳቸውን ቤት እንዲገነቡ ምዝገባ ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል።

በምዝገባ ሂደትም ችግር የገጠማቸው ተመዝጋቢዎች ካሉ ቅሬታቸውን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለቢሮ ማቅረብ ይችላል።

መረጃው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ አለፈ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 8,869 የላብራቶሪ ምርመራ 1,663 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 250,955 ደርሰዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት 20 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,531 ደርሷል።

ትላንት 1,933 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ያገገሙ 190,013 ደርሰዋል።

አሁን ላይ 987 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለቲክቫህ አባላት በሙሉ ፦

እንደሚታወቀው ይህ ፕላትፎርም በመላው ኢትዮጵያ ከክልል እስከ ቀበሌ ፣ በውጭ ሀገር እንዲሁ ያሉ የቲክቫህ አባላት የእርስ በእርስ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት [የሚተገጋገዙበት] ነው።

ባለፉት 3 ዓመታት ሁሉም አባላት በያሉበትበመሆን የሚያዩትን የሚመለከቱትን እያሳወቁ ፤ ያሳሰባቸውን ጉዳይ እያስገነዘቡ/እያስጠነቀቁ ቆይተዋል።

በየጊዜው ሰላም ሆናል፣ በሁሉም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ግድያ ይቆማል ፣ መፈናቀል ያበቃል ፣ የደቦ ፍርድ ዳግም አናይም ፣ ሁሉም አካላት ያለባቸውን ችግር በሰላም ይፈታሉ ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች ሁሉ እየተባባሱ ዛሬ ደርሰዋል።

ጭራሽ ሁሉን በሚያስደነግጥ መልኩ ሚሊዮኖች በሚኖሩበት ትግራይ ክልል ሙሉ ጦርነት ተደርጎ ይህ ትውልድ በአይኑ አይቷል፤ ከ5 ወራት በላይ ኢንተርኔት ባለመኖሩ አብዛኛው የትግራይ ክልል ቲክቫህ አባላት በህይወት ይኑሩ ይሙቱ አናውቅም ፤ ሪፖርትም የለን፤ ዛሬ ጨለማ ውስጥ ነን።

በተለይ ባለፈው 2 ዓመት የቲክቫህ አባላት ለሀገር ሰላም እና ለእርስ በእርስ ግጭት እና እልቂት ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ አድርገው መልዕክት ሲያጋሩ ቆይተዋል ፤ ይህም በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ይፈታል ብለው በማሰብ ነበር።

ከዓመታት በፊት በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ሲቀርቡ የነበሩ መልዕክቶች የእርስ በእርስ ግጭት ይዘት ያላቸው ሳይሆን/የብሄር ጉዳይ የተካረረበት ሳይሆን ቀጥታ ከመንግስት ጋር የሚያላትም ነው ፤ ይህም አንድም ሳይጓደል መንግስት ሲፈፅም የነበረውን ግፍ አንዱ አካባቢ ያለው የቲክቫህ አባል ለሌላው ሲያሳውቅ ነበር።

ያ ሁኔታ ዛሬ እንደሌለ ሁላችሁም የምታውቁት ነው።

1/4
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የብሄር ጉዳይ እጅግ ተካሮ እጅግ አስፈሪ በሆነ ድባብ ውስጥ ከቶናል (ለዚህ ደግሞ መንግስት ፣ ተቃዋሚዎች፣ አክቲቪስቶች ፣ ተው ይሄ ነገር ወዳልተፈለገ አቅስጣጫ እየሄደ ነው ብለን ያልገሠፅን ካለን እኛም እንደ ዜጋ ኃላፊነቱን መውሰድ አለብን)።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚታየው የብሄር እና አንዳንዴ ደግሞ የሀይማኖት ጉዳይ መካረር ፥ አንዳንድ የቲክቫህ አባላት መልዕክት ሲልኩ ይህን ብናገር ሌላው ወገኔ እንዴት ይሆን እያሉ ስለሚሰጉ ጉዳዩን በዝምታ ያልፋሉ/በውስጥ አውርተው ይጨርሳሉ።

እያንዳንዱ ነገር ከብሄር እና ከዘር ጋር በመገናኘቱ ለመረጃ ልውውጥ አስጊ ፣ ለንግግር እና ሀሳብ ማቅረብ ጠንቅ ፥ሁሉም ነገር አስከፊ ሆኗል።

የብሄር ጉዳይ እጅግ በተካረረበት ፣ ሁሉም አቅጣጫ ተበደልኩ፣ ታፈንኩ፣ ጩኸቴ ተቀማ የሚለው ፖለቲከኛ እና ግለሰብ ባለበት ሀገር ላይ ስለሀገራዊ ስሜት ማውራት በራሱ የሚያስወግዝ ሆኗል።

የአንዱ ቦታ ቀውስ /ግድየ ጭፍጨፋ፣ ወደሌላው ተዛምቶ በዚህ ላይ የፖለቲከኞች ሴራ ተጎንጉኖ አሁን ካለው በላይ የእልቂት ምድር እንዳይፈጠር አባላቶቻች የቻሉትን ሁሉ ሲያደርጉ ሲጠነቀቁ ነበር።

ዛሬም ግን ግድያው ፣ ጭፍጨፋው፣ የዜጎች መፈናቀሉ ቀጥሏል። ሁሌም ደግሞ ተጎጂዎቹ ምንም የማያውቁ ንፁሀን ናቸው። የፖለቲካው መቆመሪያ እነሱ ንፁሃን ነብሶች ናቸው።

ፖለቲካው ምን ላይ እንዳለ እንኳን የማያውቁ ገበሬዎች፣ ህፃናት፣ ሴቶች፣ እናቶች ናቸው የሚሞቱት ፤ የነሱን ሞት ደግሞ አንዱ ሲያቃልል ፥ ለማድበስበስ ሲሞክር፣ ወይም ሁኔታውን ለማብራራት ሲሞክር (ግፍን ማብራራት ከየት እንደለመድነው አናውቅም) ፤ አንዱ ደግሞ ሆን ብሎ ተቆርቋሪ በመምሰል ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ሲያውል እያየም ነው።

ይይህ የሀገሪቱ ሁኔታ መቼ ነው ማብቂያው ? የሚለው የሁሉም አባላት ጭንቀት ነው።

2/4