TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AtoLidetuAyalew

ትላንት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉትን አቶ ልደቱ አያሌውን የኢዴፓ ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ፣ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባላት አቶ ኤርሚያስ ባልከው እና አቶ ኤርሚያስ ጋሹ በቢሾፍቱ ከተማ በታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት ከ 5 ደቂቃዎች ላልበለጠ ጊዜ አነጋግረዋቸዋል።

አቶ ልደቱ ስለ ሁኔታው የሚከተለውን ብለዋል ፦

"በቁጥጥር ስር ከዋልኩበት ጊዜ ጀምሮ ፖሊሶቹ በጥሩ ሁኔታ ይዘውኛል። ስርዓት ያላቸው ፖሊሶች ናቸው። እነርሱ የሚተኙበትን ፍራሸም ሰጥተውኛል። በአንዲት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ከአንድ ሌላ ሰው ጋር እገኛለሁ። ፖሊስ ቃሌን በአማርኛ ቋንቋ የተቀበለኝ ሲሆን ሰነዱ ላይ የተፃፈው ግን በኦሮምኛ ቢሆንም ፖሊሱን በማመን ፈርሜበታለሁ።"

ከዚህ በተጨማሪ ከፖሊስ የቀረበላቸው ጥያቄ "ከአቶ ጅዋር መሃመድ ጋር ያለህ ግንኙነት ምንድን ነው?" የሚል እንደሆነ ገልፀዋል። በመቀጠል የክስ ቻርጁ እንደተነበበላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ትንሽ አስጊ የሚሆነው የኮሮና ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው በአንዲት አነስተኛ እስር ቤት ውስጥ ከታሰሩ 35 እስረኞች ውስጥ አብዛኞቹ ምንም ዓይነት ራሳቸው ከቫይረሱ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ለፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ገልጠውላቸዋል።

አቶ ልደቱ አያሌው በመጪው ሰኞ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የፓርቲው ጠበቃ ከዋና ጸሃፊው ጋር በመሆን በቦታው ይገኛሉ ሲል ፓርቲው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#AtoLidetuAyalew

ኢዴፓ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በላከው ደብዳቤ አቶ ልደቱ አያሌው የአስም እና የልብ ህመም እንዳለባቸው በመግለፅ ፍፁም ለጤናቸው #አስጊ በሆነ ሁኔታ በቢሾፍቱ እስር ቤት ውስጥ መታሰራቸውን አሳውቋል።

ኢዴፓ የአቶ ልደቱ መርማሪን ጨምሮ አምስት (5) ፖሊሶች በእስር ቤቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አቶ ልደቱ እራሳቸው አረጋግጠውልኛል ብሏል።

ይህ ሁኔታ ከአቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ አንፃር ለኮቪድ-19 ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ቢሆንም ምንም አይነት ጥንቃቄ በማይደረግበት እስር ቤት ውስጥ አሁንም እንዲታሰሩ በመደረጉ ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል ሲል አስታውቋል።

ፓርቲው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከሰላማዊ የትግል መስመር ውጭ ለአንድም ቀን ተንቀሳቅሶ እንደማያውቅና በአመፅና በነውጥ ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይገነባል ብሎ እንደማያምን በደብዳቤው ገልጿል።

ነገር ግን መንግስት በህግ ማስከበር ስም ከሁከትና ብጥብጥ ጋር ግንኙነት የሌለውን የተለየ ሃሳብ በማራመዱ የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ልደቱን በግፍ አስሮታል ብሏል።

ኢዴፓ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፃፈውን ደብዳቤ መሉ ሃሳብ ከላይ ባሉት ምስሎች ማንበብ ትችላላችሁ።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AtoLidetuAyalew

ዛሬ የአቶ ልደቱ አያሌውን ጉዳይ የተመለከተው የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ወስኖላቸዋል።

ሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌውን ለማስለቀቅ የሚያስፈልገው የዋስትና ገንዘብ ተከፍሎ ከእስር መውጣታቸው እየተጠበቀ መሆኑን የኢዴፓ ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለBBC ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AtoLidetuAyalew

ዛሬ የኦሮሚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ የተፈቀደውን የዋስትና መብት የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ዋስትናቸው ይፈቀድላቸው በማለት ውሳኔ አሳልፏል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተፈፃሚ እንዲሆን ለቢሸፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ደብዳቤ የፃፈ ቢሆንም ደብዳቤው የደረሰው የፖሊስ መምሪያው ግን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ አክብሬ "አልፈታም" ብሏል።

የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ፥ፖሊስ መምሪያው የፍርድ ቤቱ የውሳኔ ወረቀት ከአዳማ አምጥተን ብንሰጥም በዚህ ወሳኔ አልፈታም ብሎናል በማለት ተናግረዋል።

"የአቶ ልደቱ አያሌው ጉዳይ በፍርድ ቤት እንደማይሆን ነገረናችሗል" አሉን ያሉት አቶ አዳነ ፥ ከዚህ በፊት ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ በአደራ ነው ያሰርሗቸው አደራ የሰጠኝ አካል እስካልነገረኝ ድረስ አለቅም ብሎናል ሲሉ አቶ አዳነ ተናግረዋል።

Via Awlo Media
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AtoLidetuAyalew

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት፦

"አቶ ልደቱ አያሌው በድንገት ከቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተወስደዋል። ፖሊስ አቶ ልደቱን ለምን ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰዳቸው እስካሁን ምንም መረጃ የለንም።

የዋስትና መብታቸውን ፖሊስ እንዲያከብር ለመነጋገር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጥቶን እየጠበቅን ባለንበት ሁኔታ ነው ዛሬ ከፖሊስ ጣቢያ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን የሰማነው።

አቶ ልደቱ ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረዳቸውም ፤ በአንድ ሚዲያ ግን አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ ጉዳይ ክስ እንደተመሰረተባቸው የሚያሳይ ዘገባ ወጥቶ ተመልክተናል። በእጅጉ በፍትህ ስርአቱ ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል።

አቶ ልደቱ ፖሊስ ወደ አዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዳቸው በኃላ ስለተፈጠረው ነገር ለማጣራት ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አዳማ እየተጓዝኩ ነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AtoLidetuAyalew

የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ በተቀሰቀሰ ሁከት ላይ ሁከቱን አስተባብረዋል ፣ በገንዘብም ረድተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከቀረበባቸው "ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት" የሚል ክስ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ብሎ ፈረደ።

ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ጥር 12 /2013 በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የውሳኔ ሂደት ፦

1ኛ መሣሪያው በሌላ ሕገ ወጥ መንገድ ያልተገኘና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በአቃቤ ሕግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ፤

2ተኛ ተከሳሹ መሣሪያውን የታጠቁት ያለ ፈቃድ መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መሆኑን የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ ከመውጣቱ ከብዙ ዓመታት በፊት እና የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት መሆኑ ስለተረጋገጠ፣ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቷቸዋል።

Via Sheger FM 102.1
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AtoLidetuAyalew

አቶ ልደቱ አያሌዉ ለሕክምና ወደ አሜሪካ እንዳይሔዱ በድጋሚ መከልከላቸዉን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አቶ ልደቱ ፥ ወደአሜሪካ ለመብረር አስፈላጊውን ሰነድ አሟልተዉ ትናንት ማታ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ተናግረዋል።

የኤርፖርቱን የመጀመሪያውን የፍተሻ ካለፉ በኃላ ከአየር መንገዱ የበረራ ሰነድ ወይም ቦርዲንግ ፓስ ወስደው ፣ ሻንጣቸውን ልከው የመጨረሻው ኬላ ሲደርሱ ግን «ሲስተሙ የፍርድ ቤት እግድ እንዳለብህ ያሳያል» በሚል ከጉዞአቸው መሰናከላቸውን ገልፀዋል።

ምንም የፍርድ ቤት እግድ እንደሌለባቸው ለማስረዳት ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ተናገረዋል።

አውሮፕላን ላይ የተጫነው ሻንጣቸዉ ወርዶ ለሊት 6 ሰአት ወደ ቤታቸዉ ቢመለሱም፣ ፓስፖርታቸው ግን እንዳልተመለሰላቸው አስታዉቀዋል።

አቶ ልደቱ ፥ የደረሰባቸዉን በደል በተለይ ለሕክምና እንዳይጓዙ መከልከላቸዉን «የሞት ፍርድ» ብለውታል።

አቶ ልደቱ ፥ ወደ ዉጪ ሀገር እንዳይሄዱ ሲከለከሉ የትናንቱ የመጀመሪያዉ እንዳልሆነ ሬድዮ ጣቢያው በዘገባው ላይ አስታውሷል።

@tikvahethiopiaBOT
#AtoLidetuAyalew

ዛሬ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ከሀገር እንዳይወጡ በፖሊስ የተላለፈውንና በፍርድ ቤት ጸንቶ የነበረውን እግድ ሽሯል።

ፍርድ ቤቱ እግዱን የሻረው ከፌደራል ፖሊስ እና ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች የቀረበሉትን ምላሾች ከመረመረ በኋላ ነው።

ፍ/ቤቱ እግዱን በዋነኛነት ውድቅ ያደረገው ሁለት ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው ፦

- የመጀመሪያው ፖሊስ በደብዳቤው የጠቀሳቸው አቶ ልደቱ ተከስውባቸው በነበሩባቸው ሁለት የወንጀል ጉዳዮች ነጻ መባላቸው ነው።

- አቶ ልደቱ በአቤቱታቸው ላይ የጠቀሱትን የልብ ህመም በሁለተኛ ምክንያትነት ያነሳው ፍርድ ቤቱ፤ አቤት ባዩ ወደ አሜሪካ ሀገር ሄደው ባይታከሙ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ዳስሷል። ይህ ሁኔታ አቶ ልደቱ በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን በህይወት የመኖር መብት የሚጥስ እንደሆነ ጠቅሷል።

ፖሊስ በአቶ ልደቱ ላይ ያወጣው የጉዞ እግድም የግለሰቡን እንደ ልብ የመንቀሳቀስ ህገ መንግስታዊ መብት የሚገድብ መሆኑንም ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ ምክንያትነት አንስቷል።

በእነዚህ ዋነኛ ምክንያቶች የጉዞ እግዱ እንዲሻር የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር/www.Ethiopiainsider.com" ድረገፅ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia