TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቤልጂየም ድጋፍ : በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የ4 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጋለች።

ቤልጅየም በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ [ICRC] በኩል ነው በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 4 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ያደረገችው።

ቤልጂየም ከሰብዓዊ እርዳታ በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ ስለተፈፀሙ ወንጀሎች ገለልተኛ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አሳውቃለች።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ramadan

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ታሳቢ ያደረገው ፥ የአካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ፣ ማስክን በአግባቡ በማድረግ የመጀመሪያው ረመዳን የተርሃዊህ ሶላት በመከተል ሙከረማ እና በመዲነተል ሙነወራ ከላይ በፎቶው በምትመለከቱት መልኩ ተከናውኗል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ስርጭትን በተመለከተ ሀገር አቀፍ ጥናት ሊካሄድ ነው።

የጤና ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵየ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (CDC) እና የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመተባበር በሃገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በከተማ እና በገጠር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ጥናት ሊጀመር መሆኑን በዛሬው እለት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ አስታውቀዋል።

የጥናቱ ዋና አላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፣ በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የበሽታው ስርጭት በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ምን እንደሚመስል ጥናት በማካሄድ በሽታውን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ ላይ መፍትሄ ለማስቀመጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via EPHI
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ፈጣሪ በመቅረበ በይቅርታና በንስሃ የሚመላለሱ ልጆች ያስፈልጓታል" - ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከመጪው አርብ ጀምሮ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብር ሊጀመር መሆኑን ዛሬ አስታወቀ።

ጉባኤው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋትን፣ መጪው ሀገራዊ ምርጫንና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችን ምክንያት በማድረግ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብሩ አስፈልጓል ብሏል።

የጉባኤው ጠቅላይ ፀሀፊ የሆኑት ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ፥ እንደገለጹት ፀሎትና ምህላ የሀይማኖተኞች ችግር መፍቻ ነው፤ ሀገራችንም ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ፈጣሪ በመቅረበ በይቅርታና በንስሃ የሚመላለሱ ልጆች ያስፈልጓታል፡፡

የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብሩ ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ የሚታወጅ ሲሆን፤ ጸሎትና ምህላው ከሚያዚያ 8 ቀን ጀምሮም ለተከታታይ ሰባት ቀናት ይቆያል፡፡

ሚያዝያ 15 ላይ የመዝጊያ መርሀ ግብር እንደሚኖር ጠቅላይ ፀሀፊው አስታውቀዋል፡፡ ~ EPA

@tikvahethiopiaBOT
"...ግብፅ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት" - ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም

[አል ዓይን ኒውስ]

የግብፅ ባለሥልጣናት በመጪው የክረምት ወቅት ሊሞላ ለታቀደው ሁለተኛ ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ሀገሪቱ በመዘጋጀት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም ትላንት ለ “አል-አረቢያ” ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፥ ግብፅ ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ የግድቡን 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጽዕኖ ለመቀነስ በመስኖ መስክ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡

“ይሁን እና በዓባይ ውሃ ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት እንዳልተውን እናረጋግጣለን” በማለት በውሃ ክፍፍል ረገድ ግብፅ ያላት አቋም የጸና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም ፥ “በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የሁሉም ወገኖች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የምንጥር በመሆኑ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የተወሰነ የአቋም ለውጥ ማሳየት አለባት” ብለዋል፡፡

“መረጃ ከመለዋወጥ በፊት በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንፈልጋለን” ሲሉም ነው ኢንጂነር ሞሐመድ የሀገራቸውን አቋም የገለጹት፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#GERD #EthioSudan #Egypt #Sudan

ዛሬ ለአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ገለፃ ተደርጓል።

በኪኒሻሳ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የተካሄደውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ በተመለከተ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች ገለጻ አድርገዋል።

በዚህም ወቅት በኪንሻሳው ስብሰባ ውይይት የተደረገባቸውን ጉዳዮች እና የኢትዮጵያን ዕይታ በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

በዛሬው ገለፃ ዶክተር ኢ/ር ስለሺ ፥ ግብጽና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የአረብ አገሮች የውሃ ደህንነት ስጋት አድርገው የሚያቀርቡት ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። የአባይ ተፋሰስ አገራት ሁሉ አፍሪካዊ ሆነው ሳሉ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል የሚያራምዱት አቋም ተቀባይነት የሌለውና ሁሉም በአጽንኦት ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወቅታዊ የድርድር ሁኔታ በተጨማሪ ለአምባሳደሮቹ የኢትዮጵያ-ሱዳን ወቅታዊ የድንበር ሁኔታን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረጉ ስምምነቶች እና ባሉት የድንበር አሰራር ማዕቀፎች አማካኝነት በድርድር ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ገልጻለች።

* ዝርዝር መረጀው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ ! ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ። ህብረቱ ዶክተር አርከበ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ ማቅረቡን ነው ያመለከተው። የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር…
#DrArkebeOqubay

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ለዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ድጋፉን ሰጠ።

በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ህብረት ለUNIDO ዋና ዳይሬክተርነት እንዲወዳደሩ እጩ አድርጎ ላቀረባቸው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ድጋፍ መስጠቱን Africa-newsroom.com አስነብቧል።

የአፍሪካ የፋይናንስ ፣ ዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት ጉባኤ አባል ሚኒስትሮች ባካሄዱት ስብሰባ ዶክተር አርከበ ዕቁባይን ለUNIDO እጩ ሆነው መቅረባቸውን ደግፈዋል።

ጉባኤው ዶ/ር አርከበ በዘርፉ የልማት ፖሊሲዎች ላይ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሃሳብ አመንጪነትን አድንቆ ዘርፉን ቢመሩ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጡ አመልክቷል። ~ ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ መግለጫ ሲዳሰስ ፦

- በትግራይ ክልል ፥ በ8 ቡድን የተደራጀና በ8 የህወሓት ቡድን አመራሮች የሚመሩ ኃይሎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዘመቻ መደረጉን ተናግረዋል።

- በዘመቻው መከላከያ ማንኛውም ሀገሪቱ ያላትን ኃይል በሙሉ፣ ወታደራዊ አቅምን በሙሉ መጠቀሙን ገልፀዋል።

- በቅርቡ መቐለን እንቆጣጠራለን፣ አዲስ አበባ እንገባለን፣ የሚባለውን ነገር በነሱ አቅም ፈፅሞ የሚሞከር እና የሚቀመስ አይደለም ብለዋል። "ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቐለ እና አዲስ አበባ እይገቡም" ሲሉ ተደምጠዋል።

- ቡድኑ በምስራቅ አልያም በምዕራብ በኩል ወደ ሱዳን ለመውጣት ዝግጅት እያደረገ ነው /እየተሰባሰበ ነው ብለዋል። ዝግጅቱ እዚህ ኢትዮጵያ ባለው የህወሓት ቡድን ብቻ ሳይሆን በውጭ በሱዳን በኩልም ዝግጅቶችን አሉ ሲሉ ተናግረዋል።

- መከላከያ ሰራዊት በህግ የሚፈለጉት አካላት ተይዘው ህግ ፊት እስኪቀርቡ ድረስ ወይም እስኪጠፉ ድረስ ስራውን መከላከያው እንቅልፉን አይተኛም ብለዋል።

በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopian-National-Defense-Force-04-13
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,601 የላብራቶሪ ምርመራ 1,568 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,838 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 232,512 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,230 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 173,818 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 967 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ፔካ ሀቪስቶ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀርቪስቶ የተመራው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል። ፔካ ሀርቪስቶ ወደኢትዮጵያ ከመምጣታቸው ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው ፥ በቆይታቸው በአዲስ አበባ እንዲሁም ትግራይ ክልል ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልፀው ነበር። በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ቀውስም ፈጣን መፍትሄ እንደሚፈልግ ፅፈዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፔካ ሀቪስቶ : “በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ጥሰቶች አሁንም መሻሻሎች እየታዩ አይደለም”

[ALAIN , CNN]

የትግራይ ክልል የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱን ከቀናት በፊት ትግራይን የጎበኙት የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የፊንላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀቪስቶ ለCNN ተናግረዋል።

ልዩ መልእክተኛ ሀቪስቶ፥ “በትግራይ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ መሻሻሎች እየታዩ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሀቪስቶ በትግራይ ቆይታቸው ፥ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን ‘የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል’ን የመጎብኘት እድል እንደነበራቸው ያነሱ ሲሆን ሆስፒታሉ ጉዳት በደረሰባቸው ንጹሃን ዜጎች ተጨናንቆ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

More : https://telegra.ph/Al-AIN---CNN-04-13

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጥንቃቄ መልዕክት : እራሳችሁን ጠብቁ !

ኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ በየዕለቱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።

በዕለታዊ ምርመራ ከሚመረመሩት ዜጎቻችን መካከል በርካቶች በኮቪድ-19 መያዛቸው እየተረጋገጠ ነው።

የኛ መዘናጋት ለወረርሽኙ በአደገኛ ሁኔታ መጨመር አስተዋፆ እያደረገ ነው እና ዘውትር እንቅስቃሴያቸውን ጥንቃቄ የተሞላበት በማድረግ የሰው ልጆችን ህይወት እናትርፍ።

በተለይም ሰዎች ከሚሰበሰቡበት በመራቅ ፣ ሁል ጊዜም የአካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ ፣ ማስክ በማድረግ ፣ የእጆችን ንፅህና በመጠበቅ እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ሁሉ ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ እንታደግ።

ሁላችንም ኃላፊነታችንን ከተወጣን ወረርሽኙ እየተዛመተበት ያለውን ፍጥነት መቀነስ እንችላለን።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ ጥሪ : "በዝግ እንወያይ"

[Al AIN]

የሱዳን ጠ/ሚር ዶክተር አብደላ ሀምዶክ ለግብጽ ጠ/ሚር ሙስጠፋ ማድቦሊ እና ለኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ10 ቀናት ውስጥ “በዝግ እንወያይ” የሚል ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከ10 ባልበለጡ ቀናት ውስጥ ተገናኝተን የድርድሩን ሂደቶች እንገምግም” ብለዋል፡፡

“በ2015ቱ የመርሆዎች ስምምነት መሰረት ወደፊት ለመራመድ በሚያስችሉን አማራጮች ላይ ተወያይተን እንስማማ፤ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነታችንንም እናድስ” ሲሉም ነው ሃምዶክ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ጥሪው የቀረበው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉት ተደጋጋሚ የሶስትዮሽ ድርድሮች “ውጤታማ ሳይሆኑና ስምምነት ላይ ሳይደረስ ዓመታት በመቆጠራቸው” ነው፡፡

ሃምዶክ ለኢትዮጵያና ለግብጽ አቻዎቻቸው ጉዳዩን የተመለከተ መልዕክት ልከዋል፡፡

More : https://telegra.ph/Al-AIN-04-14

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"... ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ፤ ነገር ግን ዝግጁ አይደለንም ማለት አይደለም" - ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትለንት በሰጡት መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንደማታደርግ ፥ ጦርነት ማድረጉ ምንም እነደማያደርግ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራሉ አሁን ሱዳኖች ያያዙትን መሬት በንግግር መጨረስ ይቻላል ፥ እምነታችንም እሱ ነው ብለዋል።

ስንት ጊዜ ነው በመሬት ችግር ዘራፍ ብለን ተዋግተን ወጣቶችን የምናስጨርሰው ? ብለው የጠየቁት ሌ/ጄነራሉ ፥ የመሬቱን ጉዳይ በቀላሉ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መፍታት ይቻላል ፤ ግፋ ቢል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መፍታት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ወንድማማቾች መካከል የገባ ሶስተኛ ወገን አለ ፤ ከሱዳን ወንድሞቻችን ጋር በጋራ ሆነን ይሄን ሶስተኛ ወገን ለማውጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ነገር ግን ዝግጅ አይደለንም ማለት አይደለም፤ ኢትዮጵያን ለመከላከል እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምን ጊዜም ዝግጁ ነን" ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የማህበር ቤት ምዝገባ : የአ/አ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን በአማራጭ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ምዝገባ ነገ ይጀምራል። በምዝገባው የሚካተቱት ፦ - በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና 40 /60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡ - ስማቸው በምዝገባ ቋት የሚገኝ እና የቁጠባ ደብተር ሂሳብ…
የማህበር ቤት ምዝገባ ተራዘመ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የማህበር ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን አስታውቋል።

የማህበር ቤት ምዝገባ ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበዋል፡፡

የምዝገባ ጊዜው ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የተጠናቀቀ ቢሆንም ከተጠቃሚው ወደ ቢሮው በሚመጡ ጥያቄዎች በመነሳት ምዝገባው ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡

መመዝገብ እየፈለጉ በተለያዩ ምክንያቶች ቀኑ ያለፋቸው ተጠቃሚዎች የምዝገባ ጊዜው ከሚያዚያ 6 እስከ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ /Online/ በቢሮው አድራሻ aahdab.gov.et አማካኝነት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በምዝገባ ወቅት ችግር የገጠማቸውን የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ ከሚያዚያ 18-20/2013 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በቢሮው ቀርበው ቅሬታችውን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT
#Adwa

(ሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ/ም)

• "...በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን በሚል ነው ጥቃት የፈፀሙት፤ ...አንድ ሰው ሞቷል" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም

• "...በተኩሱ 8 ሰዎች ሞተዋል" - የአድዋ ነዋሪዎች

• "...ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" - የአድዋ ነዋሪ

• "...2 የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ 3 ጊዜ ተኮሱብኝ" - የጥቃቱ ሰለባ

• "...ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" - የጤና ባለሞያ

• "... ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል መጥተው እርዳታ እንደተደረገላቸው ነው ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል" - MSF

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-04-14

@tikvahaethiopiaBOT @tikvahethiopia