TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...ከመንግስታቱ አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን" - ጓንጓ ወረዳ

መተከል ዞን አዋስነው በሚገኙት የአማራ ክልል ወረዳዎች ጃዊ፣ ጓንጓ ፣ ዚገም እና ቻግኒ ከተማ ላይ ያንዣበበው ከፍተኛ ስጋት ንፁሃንን አጉል መሰዋትነት እያስከፈለ ነው ሲል የጓንጓ ወረዳ አስታወቀ።

ቀጠና ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት በመሆኑ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩ ግልፅ ነው ብሏል የወረዳው ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ።

ወረዳው ፥ "ያለ ምክንያት እየተሰዋ ላለው ህዝባችን የ2ቱ ክልል መንግስታትና የፌዴራሉ መንግስት ዝምታ ባይገባንም አስቸኳይ የሰላም መፍትሔ የማይሰጥ ከሆነ ህዝባችን ላይ የሚደርሰው አደጋ የከፋ እንደሚሆን በተግባርም እየተመለከትን በመሆኑ ከሶስቱ መንግስታት አስቸኳይ መልስ እንፈልጋለን" ብሏል።

@tikvahethiopia
#COVID19Vaccine

ዛሬ መጋቢት 30 በኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ጀምረዋል።

ክትባቱን ለሁሉም የኃይማኖት አባቶች ለመስጠት ፕሮግራም እንደተያዘ ታውቋል።

PHOTO : EOTC TV & EBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Update

የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦

- በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

- በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ።

ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (#MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ።

@tikvahethiopia @TikvahUniversity
#ምርጫ2013

"...ከአገሪቱ የመክፈል አቅም አኳያ ክፍያው አነስተኛ አይደለም" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ

ለስድስተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ 200 ሺ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና ተከታትለው ወደ ሥራ ገብተዋል።

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከተሰማሩ አስፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት ''ክፍያው ያንሰናል'' በሚል ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳልተገኙ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ አስፈጻሚዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ስልጠና ተሰጥቷቸው በአ/አ ከተማ የምርጫ ጣቢያዎች ከተሰማሩት አስፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት ሥራ ባለመጀመራቸው የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ምርጫ ቦርድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሌሎች የምርጫ አስፈጻሚዎችን በመመልመል አገልግሎቱ በፍጥነት እንዲጀመር ማድረጉን ገልጸዋል።

ያልሰለጠኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ወደ ስለማይሰማሩ እንደ አዲስ ስልጠና በመስጠት የሰው ሃይል ማሰማራት ፈተና እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ይህም ቢሆን ግን የሰው ሃይል እጥረት ያለባቸው ቦታዎችን አዲስ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በማሰልጠን የሰው ሃይሉ እንዲሟላ መደረጉን ተናግረዋል።

ለምርጫ አስፈጻሚዎች የሚመደበው ክፍያ ለምርጫው ከተያዘው በጀት ከፍተኛ መጠን እንደሚይዝ ገልፀው፤ ከአገሪቱ የመክፈል አቅም አኳያ ክፍያው አነስተኛ አለመሆኑን አይደለም ብለዋል።

"በመሆኑም የምርጫ አስፈጻሚዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአገራዊ የኃላፊነት መንፈስ ሊወጡ ይገባል" ብለዋል።

አስፈጻሚዎቹ ኃላፊነታቸውን በትክክል በመወጣት ለኢትዮጵያ መጻኢ እድል ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።~ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የስልክ ውይይት :

[Deutsche Welle , Reuters, www.whitehouse.gov]

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ብሔራዊ የፀጥታ አማካሪ ጃክ ሰሊቫን የኢትዮጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ፀጥታን ያናጋዉ ግጭት እና ጥቃት እንዳሳሰባቸዉ አስታውቀዋል።

ዋይት ሐዉስ፥ የፀጥታ አማካሪዉ ከም/ጠቅላይ ሚንስትር እና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ትናንት በስልክ ባደረጉት ዉይይት በተለይ ትግራይ ክልል ዉስጥ የሚደረገዉ ግጭት እንዳሳሰባቸዉ አስታዉቀዋል።

ሮይተርስ ዋይት ሐዉስን ዋቢ እንድርጎ እንደዘገበው፥ 2ቱ ባለስልጣናት ትግራይ ዉስጥ ለተቸገረዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ስለሚቀርብበት ፣ ግጭቱ ስለሚረግብበት ፣ የዉጪ ወታደሮች ስለሚወጡበትና የደረሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደል በገለልተኛ ወገን ስለሚጣራበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።

ከትግራይ ክልል በተጨማሪም በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉት የጎሳ ግጭቶችና ጥቃቶች በዉይይቱ መነሳቱ ተጠቅሷል።

በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የገጠመችዉን ዉዝግብ ለማስወገድ የሚደረገዉ አካባቢያዊ ዉይይት መቀጠል እንዳለበት መወያየታቸውን ኃይት ሐውስ አሳውቋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በይፋዊ የማህበራዊ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ በትግራይ ያለው ሁኔታ እየተሻሻለ መሆኑንም በስልክ ውይይቱ ወቅት እንዳብራሩ ገልፀዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ታዛቢዎች በፍትሃዊነት እና በገለልተኝነት እንዲያገለግሉ በማሰብ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ድርድር ቁልፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈታ እንዳረጋገጡላቸው አስፍረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

#Purpose #Tikvah

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 341 የላብራቶሪ ምርመራ 39 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 56 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓት ከተደረገው 40 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 87 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 197 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 3 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 105 የላብራቶሪ ምርመራ 40 ሰዎች ላይ ቫይረዱ ተገኝቷል ፤ 16 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 809 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 244 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
#Attention😷

ባለፉት 24 ሰዓት 20 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,757 የላብራቶሪ ምርመራ 2,121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 617 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 223,665 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,078 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 166,752 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 892 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በአፋር እና ሱማሊ ክልል መካከል ያለው ውጥረት ፦ የአፋር ክልል መንግስት ፦ - በክልሉ "ሀሩቃ" በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። - በአርቡ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። - የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት "ገዋኔ"…
#UPDATE

የሱማሌ ክልል እና አፋር ክልል መንግስታት ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት መስማማታቸው ተገልጿል።

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ዛሬ በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ሰብሳቢነት ምክክር አድርጓል።

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተፈጠሩትን ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰላም ሚኒስቴር ማምሻውን አሳውቋል።

የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት አድርገዋል።

@tikvahethiopia
አንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት ናይሮቢ ውስጥ ባለሆቴል ህይወቱ አልፎ ተገኘ።

በኬንያ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት በናይሮቢ ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆነው ግለሰብ አንድ ሆቴል ውስጥ ነው ህይወቱ አልፎ የተገኘው።

ሟቹ እራሱን እንዳጠፋ የሚያስጠረጥሩ ምልክቶች መገኘታቸውንም ሲጂቲኤን አፍሪካን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ድህረገፁ አስነብቧል።

በሟቹ ክፍል ውስጥ ተገኘ የተባለው አነስተኛ ማስታወሻ እራሱን ስለማጥፋቱ የሚያስጠረጥር ቢሆንም የኬንያ ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ አመቱን በማክበር ላይ ይገኛል።

በ1946 ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ በረራ ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል ካይሮ (ግብፅ) ያረፈው።

ዛሬ ላይ በዓለማችን ካሉ አንጋፋ አየር መንገዶች አንዱ ለመሆን የበቃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 75ኛ አመቱን በማክበር ላይ ይገኛል።

እ.ኤ.አ በ 1946 ዓ.ም ወደ ግብፅ ካይሮ በረራ በማድረግ የተጀመረውን የ75 አመት የስኬት ጉዞውን በማስመልከት ትላንት ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ ካይሮ የሚደረገው በረራ ከመነሳቱ በፊት ደማቅ አሸኛኘት እንደተደረገለት ከአየር መንጉዱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን 550 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን #ለኢዜአ አስታውቋል።

በተደረገው መከላከል 67 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 "መልካ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።

በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች ሞተዋል።

ምክንያት ?

አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

ምክንያት ?

ገና ፖሊስ እያጣራው ነው።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።

ምክንያት ?

የኤሌክትሪክ ኮንታክት ነው ተብሏል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።

ምክንያት ?

እስካሁን አልታወቀም።

#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለ22 ዓመት ጅቡቲን የመሩት ፕሬዜዳንት ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ነው !

የጂቡቲ ህዝብ ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ዛሬ ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የጅቡቲው ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ለ5ኛ ጊዜ ለፕሬዜዳንትነት እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ዛሬ ከቀትር በኋላ ድምፃቸውን ሰተዋል።

ከ200 ሺህ በላይ ድምፅ ሰጪዎች የተሳተፉበት ምርጫ ምሽት ላይ ይዘጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የ73 አመቱ ፕሬዝዳንት ጌሌ ለ22 አመታት የጂቡቲን መርተዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ በር ላይ የምትገኘው ጂቡቲ አንድ ሚሊየን ገደማ ህዝብ ያላት ሲሆን የተለያዩ ሀገራት ወታደሮች የጦር ሰፈር ይገኙባታል።

#SRTV
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT